የአገር የመከላከያ ሰራዊት ኦፊሰሮችን ወደ መቀሌ መላካቸው ተሰማ ። የጦር መኮንኖቹ ለህወሃት ከፍተኛ አመራሮች ግልጽ ጥያቄ ያቀረቡ አቅርበዋል። ጥያቄያቸውን ህግን ስለማክበርና ለፌደራሉ ህገመንግስት እንዲታዘዙ መሆኑ ታውቋል።

ለዝግጅት ክፍላችን መረጃውን ያደረሱን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ወገኖች እንዳሉት ወደ መቀሌ ያመሩት የመከላከያ አመራሮች አብዣኞቹ የክልሉ ተወላጅ ሲሆኑ በህዝብ ዘንድም ተወዳጅ፣ በሰራዊቱ ውስጥ በአመራር ሰጪነታቸውና በዲሲፒሊናቸው የሚከበሩ ናቸው።

ህወሃት ህገመንግስቱን አክብሮ እንዲንቀሳቀስ ለማሳሰብ ወደ መቀሌ ያመሩት ኦፊሰሮች መልዕክቱን አድርሰው ወደ ስራቸው የተመለሱ ሲሆን፤ ህወሃት ” ልምክረበት” ማለቱ ተሰምቷል። የአገር መከላከያ ሰራዊት ህገመንግስት የማስከበር ሃላፊነትና የአገር ሰላም የማስጠበቅ ግዳጅ እንዳለበት የተቀበለ መሆኑ ለህወሃት በግልጽ የተነገረ ተነግሯል። የመረጃ ምንጮቹ እንዳሉት ህወሃት ይህንን ተግባራዊ የማያደርግ ከሆነ በተከታታይ ህግ እንዲያከበር የሚያስችል እርምጃ ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ ማሳሰቢያ ተሰጥቶታል።

Related stories   የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አገር ለማተራመስ በህቡዕ የተደራጁ በርካታ ግለሰቦችን ከነመዋቅራቸውና መስሪያዎቻቸው በቁጥጥር ስር አዋለ፤

ምክርና ማስጠንቀቂያ የተሰጠው ህወሃት ” ልምክርበት” የሚል ምላሽ መስጠቱን፣ በዝርዝር የያዘው አቋም ግን ምን እንደሆነ ለጊዜው እንዳልሰሙ የመረጃው ሰዎች ገልጸዋል። መከላከያ አደራውን መወጣት በሚያስችለው አግባብ መሰረት ስለሚወስደው እርምጃም አላብራሩም። ይሁን እንጂ መንግስት ሸምቀቆውን ሊያጠብቅ እንደሚችል ጠቁመዋል።

የትግራይ ቲቪና የድምጸ ወያኔ መዘጋት ድንጋጤ መፍጠሩን በስቶክሆልም የሚኖር የህወሃት ደጋፊ ለዝግጅት ክፍላችን ሃሳቡን ሰጥቷል። የመከላከያ ኦፊሰሮች ወደ መቀሌ መሄዳቸውን እንደሚያውቅ ያስታወቀው ይኸው አስተያየት ሰጪ እንዳለው መንግስትም ሆነ ህወሃት ወደ ጦርነት ይገባሉ የሚል እምነት እንደሌለው ይገልጻል። ይሁን እንጂ አንዳን እቀባዎች እንደሚደረጉ ያምናል። መረጃም አለው።

Related stories   ዶክተር አብራሃም በላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ!

ነገሮች ካልተቀየሩ በመጪው አንድ ወር ጊዜ የአየር በረራ ሊዘጋ እንደሚችል የማለከተው የስቶክሆልም ነዋሪ የህወሃት ታላላቅ የንግድ ተቋማት ላይም በተመሳሳይ የገንዘብ ዝውውር ላይ ገደብ እንደሚጣል መስማቱን ያክላል። በየብስ እንዳሻው የማይነቀሳቀሰው ህወሃት የአየር ጉዞ ማዕቀብ ከተጣለበት ችግሩ እንደሚጠናበት ይገምታል። ይህ ተግባራዊ ከሆነበት ህወሃት ወደ ጦርነት ሊያመራ እንደሚችል መረጃ ካለው ተጠይቆ፣

” ትግራይ ባለው መከላከያ ላይ ጥይት ይተኮሳል? አማራ ክልል ሄደው ይዋጋሉ ወይስ አፋር ክልልን ይወራሉ?” ሲል ይጠይቅና ” እንደሚገባኝ ከህወሃት ውስጥ በቅርቡ ሃይል ይወታል፤ ይህ ሃይል ነገሮችን ይቀይራል። መንግስትም ከዚህ ሃይል ጋር የሚሰራ ይመስለናል” ሲል የሚገምተውን ተናግሯል። መንግስትም በሃወሃት በኩል ያሉ ጥርጣሬዎችን ሊያስወግድ እንደሚገባው እንደሚያምን ይገልጻል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *