Share and Enjoy !

Shares

ለለውጥ ግንባሩን በመስጠት ” አልሞተም” የተባለው ሃጫሉ ሁንዴ ተኩሰው የገደሉት ቅጥር ነብሰ ገዳዮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጠቅላይ አቃቤ ህግ አዳነች አቤቤ አስታወቁ። ቅጥር ነፍሰ ገዳዮቹ ለፖሊስ በሰጡት የእምነት ቃል ኦነግ ሸኔ ግድያውን እንዳቀነባበርና እርስ በርስ ሲያወሩ ትግርኛ የሚነጋገሩ ሰዎች እቅዱን በጋራ ይነድፉ እንደነበር ይፋ አድርገዋል።

ወ/ሮ አዳነች እንዳሉት ዋናው ተኳሽ ጥላሁን ያሚ የሚባል የገላን አካባቢ ነዋሪ ሲሆን በአካባቢው ነዋሪዎች ጥልሽ ተብሎ ይጠራል። ሁለተኛው ተባባሪ አብዲ አለማየሁ ሲሆን ሶስተኛው ተባባሪ ከበደ ገመቹ ለጊዜው ተሰውሮ በፖሊስና በህዝብ እየታደነ ነው።

እቅድ አውጪዎቹ ደጋግመው እንዳገኟቸውና ግድያውን እንዲፈጽሙ ሲያግባቡዋቸው እንደነበር ያስታወቁት ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳዮች የእመነት ክህደት ቃላቸውን ሲሰጡ ” በርካታ የሚገደሉ ሰዎች አሉ። ይህ የሚሆነው የፌደራል መንግስት እየወደቀ ስለሆነ ኦሮሚያን ለመታደግ ነው። እናንተም ትጠቀማላቹህ” ብለው አግባብተዋቸዋል። አሳምነዋቸዋል። ይሁን እንጂ ሃጫሉ መሆኑንን አልነገሯቸውም።

Related stories   ስብሃት ነጋ የትህነግን የውጪ አገር ሃብትና ንብረት "ለትግራይ ሕዝብ ጥቅም ሲባል" ይፋ እያደረጉ ነው

በማሳመኑ ስራ ከኦነግ ሸኔ በተጨማሪ በትግርኛ የሚነጋገሩ ሰዎችም እንደነበሩ ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳዮቹ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። ለጊዜው የተሰወረው ከበደ ገመቹ ህዝብ ቀደም ሲል እንዳደረገው ሁሉ ከጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር እንዲውል ጥረት እየተደረገ መሆኑን አዳነች አቤቤ አስታውቀዋል። አያይዘውም ካሁን በሁዋላ ኢትዮጵያን ማፈራረስ እንደማይፈቀድና ህዝብ ልጆቹን ከአፍራሽ ቅስቀሳና ወንጀል እንዲጠብቅ መክረዋል። ጥሪ አስተላልፈዋል።

መንግስት ጠንካራ አቋም መያዙን ይፋ ያደረጉት ጠቅላይ አቃቤ ህጓ ህዝብ እያደረገ ላለው ወንጀለኞችን የማጋለጥ ድጋፍ ምስጋና አቅረበዋል። ህግ የማስከበሩ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጫ ሰጥተዋል።

ለሃዘን እንኳን ጊዜ ያልተሰጠው ሃጫሉ ከሞቱ በላይ አስከሬኑ ያጓጓቸው ያካሄዱበት የፖለቲካ ንግድ እጅግ እንዳሳዘናቸው ቤተሰቦቹ በተደጋጋሚ ቢገልጹም በውጭ አገር ዛሬ ድረስ ሃጫሉ አዲስ አበባ መቀበር ነበረበት የሚል ድምጽ እያሰሙ ነው። የታሰሩ ይፈቱ የሚል ጥያቄ አንግበው ሰላማዊ ሰልፍ የሚያካሂዱት ወገኖችን ድምጽ በማስተጋባት አፍቃሪ ህወሃት ሚዲያዎች ለሃጫሉ ሞት ግተቆርቋሪና ፍትህ ጠያቂ ሆነው 24 ሰዓታት እየወተወቱ ነው።

Related stories   ፈቃድ የሌላቸው ግለሰቦችና ተቋማት በጥምቀት በዓል ድሮን መጠቀም እንደማይችሉ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

ቀውደም ሲል ሃጫሉ ሲታሰር ሲገረፍና ሲሰቃይ አንድም ድምጽ ያላሰሙ፣ እንዲያውም ሲያወግዙትና ሲያስፈራሩት የነበሩ ሚዲያዎች ዛሬ ላሃጫሉ ሞት ፍትህ ጠያቂ መሆናቸው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ” ሃፍረት የተቀባ” መሆኑንን የሚያረጋግጥ መሆኑንን ሌሎች ወገኖች እየገለጹ ነው። ” ለምሰማው አፈርኩ” የሚሉ ዜጎች ” በዚህ መስሉ ዘገባ መሰላቸታቸውንም ደጋግመው እየገለጹ ነው።

ህወሃት የሃጫሉን ሞት አስመልክቶ ባወጣው ” ደረት የሚያስደቃ መግለጫ” ሃጫሉን ደፋር ታጋይ፣ የለውጥ አርበኛ ሲል አሞግሶ መንግስት እንደገደለው ይፋ ተናግሯል። ይሁን እንጂ ሃጫሉን ሲገርፈው፣ ስያስረውና ሲያሰቃየው እንደነበር እንዲሁም ሃጫሉ በቅርቡ እንዳለው መኪና፣ ቤት፣ በቂ ገንዘብ እንስጥህ በማለት ከትግሉ ራሱን እንዲያገል ከህወሃት ምልጃ ስለማቅረቡ ያለው ነገር የለም።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *