የኮሮና መግለጫየኮሮና መግለጫየኮሮና መግለጫየኮሮና መግለጫየኮሮና መግለጫየኮሮና መግለጫየኮሮና መግለጫየኮሮና መግለጫየኮሮና መግለጫየኮሮና መግለጫየኮሮና መግለጫባለፉት 24 ሰዓታት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በተሰባሰቡ 5 ሺህ 139ናሙናዎች ላይ በተደረገ ምርመራ 282 ሰዎች ላይ የኮሮናቫይረስ መገኘቱ ተገለጸ።

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና የሕብረተሰብ ጤና ተቋም ዛሬ ባወጡት ዕለታዊ የወረርሽኙ ሁኔታ ሪፖርት ላይ እንደተገለጸውከዚህ በፊት በወረርሽኙ መያዛቸው ተረጋግጦ የህክምና ክትትል ሲደረግላቸው ከነበሩ ሰዎች መካከል ተጨማሪ 239 ሰዎች ከበሽታው በማገገማቸው እስካሁን በኢትዮጵያ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥርን 4152አድርሶታል።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል 179ኙ ከአዲስ አበባ፣ 75ቱ ከድሬዳዋ፣ 15ቱ ከጋምቤላ፣ 7ቱ ከትግራይ፣ 2ቱ ከኦሮሚያ፣ 2ቱ ከአፋር፣ 1 ከቤኒሻንጉልና 1 ከሲዳማ ክልሎች ናቸው።

ዕለታዊው መግለጫ ከዚህ በተጨማሪም በዛሬው ዕለት ከበሽታው ጋር በተያያዘ ሞት አለመመዝገቡን አመልክቷል።

በኢትዮጵያ እስካሁን 281 ሺህ 069 ናሙናዎች ላይ ምርመራ ተደርጎ በአጠቃላይ 7 ሺህ 402 ቫይረሱ ያለባቸውን ሰዎች ተገኝተዋል።

ቢቢሲ አማርኛ

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *