ከስልሳ ሺህ በላይ የሶማሌ ተወላጆች ይኖሩባታል በሚባለው የሜኖሴታ ግዛት ” ኢትዮጵያ ትወደም” በሚል የተነሳውን አድማ  እንደሚደግፉ ፍንጭ የሰጡት እንደራሴ ኢላሃን ኦማር እጃቸውን እንዲሰበስቡ ለማሳሰብ የኮሚኒቲው አመራሮች ለፊታችን ቅዳሜ ስብሰባ መጥራታቸው ተጠቆመ። ወይዘሮዋ በሚገኙበት ስብሰባ ይህንን ጥሪ የማይቀበሉ ከሆነ በቅርቡ ለሚያካሂዱት ምርጫ ችግር ይገጥማቸዋል።

Image may contain: 1 person, textቀደም ባሉት ሳምንታት የግዛቷ የኦሮሞ ኮሙኒቲ አምስት ተወካዮች ከሶማሌ ተወላጆች የኮሚኒቲ አመራሮችን ” ድጋፍ አድርጉልን” ሲሉ ጥያቄ አቅርበው እንደነበር በማስታወስ ለኢትዮ ጎልጉል መረጃ የሰጡ እንዳሉት በስብሰባው ጥያቄው ውድቅ ተደርጓል። ይልቁኑም ብሄርን መሰረት ያደረገ ግድያ፣ ዘረፋና ንብረት ማውደም ሊወገዝ እንደሚገባ አሳስበዋል።

Related stories   ኢትዮጵያ በወታደራዊ ኃይል ጥንካሬ ከአፍሪካ 6ኛ ከዓለም 60ኛ ሆነች

በኮሙኒቲ ደረጃ ይህ አቋም ቢያዝም የግዛቷ እንደራሴ ወ/ሮ ኢላሃን በግላቸው ለጽንፈኞች ድጋፍ ለመስጠት ያሳዩት አዝማሚያ ቅሬታን አስነስቶባቸዋል።ለምርጫ ቅስቀሳ ስራ አስኪያጃቸው የከፈሉት የአንድ ሚሊዮን ዶላር ጉዳይ ምርመራ እንዲካሄድበት እየተጠየቀ ባለበት በአሁኑ ሰዓት ከህወሃት ጋር አብሮ ለሚሰራው ኦነግ ሸኔ ድጋፍ ለመስጠት መከጀላቸው በጄል ኦጋዴን የተፈጸመውን ግፍ፣ በሶማሌ ተወላጅ ሴቶች ላይ የተካሄደውን አስገድዶ መድፈር፣ በክልሉ ላይ የተፈጸመን ምዝበራና ዓለምን ጉድ ያሰኘ ግፍ መልሶ እንዲመጣ መተባበር እንደሆነ ነው ነገ ቅዳሜ የሚነገራቸው።

Related stories   ኢትዮጵያ የአሰብን ወደብ በዶላር ሳይሆን በብር የኪራይ ውል የምትጠቀምበት ስምምነት ጫፍ እየደረሰ ነው

ይህንን ተጋራዊ የማያደርጉና የመላው ሶማሌ ብሎም ኢትዮጵያዊያንን ልብ ከሰበረው የህወሃትና የኦነግ ሸኔ ጥምረት ውስጥ ተሳታፊ በመሆን ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የሚደረገው ማናቸውም ዓይነት ድጋፍ ወይዘሮዋን በመጪው የዳግም ምርጫ ሩጫቸው ላይ ዋጋ እንደሚያስከፍላቸው በግልጽ እንደሚነገራቸው መረጃውን የሰጡ አስታውቀዋል። ህወሃትን መተባበር አቶ ሙስጣፌ በሶማሌ ክልል የሚሰሩትን ለውጥ ማደናቀፍ መሆኑንንም ጭምር እንዲረዱ ሰፊ ውይይት ለማድረግ ቀጠሮ መያዙን ያወሱት የመረጃው ምንጭ ” ላሃን ኦማር በቂ መረጃ በማግኘት ለመተባበር ቃል ከገቡበት መንገድ እጃቸውን እንደሚያወጡ እናምናለን” ብለዋል።

Related stories   እነ ጃዋር " በዛሬው ቀጠሮ የእምነት ክህደት ቃል ለመስጠት ዝግጁ አይደለንም" ሲሉ የመማከሪያ ጊዜ ጠየቁ

በሜኖሴታ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የሶማሌ ተወላጆች ድጋፍ እንደሰጡ መገለጹን አስመልክቶ ለተጠየቁት ” ሃሰት፣ በጣም ትንሽ ሶስትና አራት የማይሞሉ” ሲሉ መልሰዋል። አስቀድሞ ለሁሉም የሶማሌ ተወላጆች መልዕክት መተላለፉንና ያም ተግባራዊ መደረጉን ተናግረዋል።

በተመሳሳይ ለሶማሊ ላንድ ባለስልጣናት አስፈላጊው መረጃ በመስጠት በዛ በኩል ምንም ዓይነት ክፍተት እንዳይኖር በቂ መግባባት ላይ መደረሱንም ምንጩ ተናግረዋል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *