“Our true nationality is mankind.”H.G.

በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ሁሉም ኢትዮጵያዊ የማህበራዊ የጤና መድን ተጠቃሚ ይሆናል

የጤና ሚኒስቴር በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ሁሉንም የኢትዮጵያ ሕዝብ የማህበራዊ የጤና መድን ተጠቃሚ ለማድረግ ዕቅድ መያዙን አስታወቀ። የጤናው ዘርፍ የአሥር ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ ላይ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ውይይት አድርገዋል።

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ መሪ ዕቅዱን ባቀረቡበት ውቅት እንደተናገሩት በዘርፉ በርከታ ተግባራት ቢከናወኑም አሁንም የሕዝቡ ፍላጎት ብዙ ነው። “ዛሬም የጤናው ዘርፍ አናሳ ተደራሽነት፣ የአገልግሎት ጥራት ጉድለት፣ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ስርጭት ዘርፉን እየተፈታተኑት ይገኛሉ” ይላሉ።

ከዚህ ባለፈ አጠቃላይ የጤናው ስርዓት ከተለዋዋጭ ሁኔታዎች ጋር አብሮ ያለመሄድ፣ የአገልግሎት ፍትሃዊነት መጓደልና አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ሙያተኞች ያሉበት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ ሚኒስትሯ ገለጻ የጤናው ዘርፍ የግብዓት እጥረት፣ የመሰረተ ልማት እና የመረጃ አያያዝ ችግሮች አሉበት።

በቀጣዮቹ አስር ዓመታት የሚተገበረው መሪ የልማት ዕቅድ በዋናነት እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ ያለመ መሆኑን ዶከትር ሊያ ገልጸዋል። በዕቅዱ መሰረትም የኢትዮጵያዊያን የዕድሜ ጣሪያ አሁን ካለበት 65 ወደ 70 ዓመት ከፍ እንዲል ማድረግ አንዱ ነው።

Related stories   የዘረኝነት ጥግ “እናት ነኝ የሌሎች ህፃናት ወላጆችን ግን ገደልኩ”

የጨቅላ ሕጻናት ሞት አሁን ካለበት ከ1 ሺህ ሕጻናት 33 ሞት ወደ 12 ማውረድ እንዲሁም ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች የሚከሰትን ሞት ለመቀነስ መታቀዱን ሚኒስትሯ አብራርተዋል።

ከዚህ ጎን ለጎን አሁን ያልተጀመረውን የማህበራዊ ጤና መድን ሽፋን 100 ፐርሰንት ማድረስ እንዲሁም የማሕበረሰብ አቀፍ ጤና መድን ሽፋን አሁን ካለበት 49 በመቶ ወደ 100 ፐርሰንት ለመሳደግ መታቀዱን አስታውቀዋል።

“ሚኒስትሯ አክለውም መሰረታዊ የጤና አገልግሎት ሽፋንን አሁን ካለበት 44 በመቶ ወደ 80 በመቶ ማሳደግና አሁን 8 በመቶ ላይ ያለውን የጤና በጀት 15 በመቶ ለማድረስም ታቅዷል” ብለዋል።

Related stories   የዘረኝነት ጥግ “እናት ነኝ የሌሎች ህፃናት ወላጆችን ግን ገደልኩ”

“ዕቅዱን ከማሳካት በሻገር ስለፍትሃዊነቱም መጨነቅ ያስፈልጋል” ያሉት ደግሞ በጤና ዘርፍ ፍትሃዊነት ላይ ማብራሪያ የሰጡት ፕሮፌሰር የማነ ብርሓነ ናቸው።

እንደ እሳቸው ገለጻ ዕቅዱን ከመተግበር ጎን ለጎን በክልሎች መካከል ያለውን የፍትሃዊነት ልዩነት ማስተካከል ይገባል።

በተጨማሪም በተማረውና ባልተማረው፣ በገጠርና በከተማና መሰል ጉዳዮች ላይ ያለውን ልዩነት ማጥበብ አንዱ የፍትሃሚነት ማረጋጋጫ መንገድ ነው ብለዋል።

ሌላው በዕቅዱ ዙሪያ ሙያዊ አስትያየታቸውን ያቀረቡት ዶክተር ተግባር ይግዛው “በነዚህ ዓመታት ጠንካራ የጤና ስርዓት መገንባት ያስፈልጋል” ይላሉ። ጠንካራ የጤና ስርዓት ለመገንባትም ዋናውና ቀዳሚው ነገር ጠንከራ የሰው ሀብት መገንበት ግድ መሆኑን አመልክተዋል። በእዚህም የጤናው ዘርፍ የሰው ሀብት ብቁና ጥራት ያለው ከመሆን ባለፈ በቁጥርና በተደራሽነት ማደግ እንዳለበትም መክረዋል።

Related stories   የዘረኝነት ጥግ “እናት ነኝ የሌሎች ህፃናት ወላጆችን ግን ገደልኩ”

“የጤናው ዘርፍ በመንግስትና በግል አጋርነት ፋይናንስ ቢደረግ ለዕቅዱ ስኬት ይረዳል” ያሉት ደግሞ ፕሮፌሰር ዳመነ ኃይለማሪያም ናቸው። ፕሮፌሰር ዳመነ እንደሚሉት መንግስት ብቻውን የጤናውን አገልግሎት ተደራሽ ማድረግ ስለማይችል ዘርፉን ከማስተባበር ባሻገር ከግል ዘርፍ ጋር በቅርበት መስራት እንዳለበት ተናግረዋል። ” ውድ የሚባለውን ሕክምና መንግስት መሸፈን ቢችል ግለሰብ ደግሞ ርካሽ የሆነውን መሸፈን አያቅተውም ” ብለዋል ።

እንደአስፈላጊነቱ ዜጎች ነጻ ሕክምና የሚያገኙበት ዕድል ቢሰፋ መልካም መሆኑን የጠቀሱት ፕሮፌሰሩ ፣ የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በዓመት ከ50 እስከ 80 ሚሊዮን ብር ነጻ ህክምና መስጠቱን በምሳሌነት መጥቀሳቸውን ኢዜአ ዘግቧል። የአሥር ዓመቱን መሪ የልማት ዕቅድ አስመልክቶ በየዘርፉ ውይይቱ ማድረጉ ቀጥሏል።

#FBC

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0