ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 7 ሺህ 334 የላብራቶሪ ምርመራ 704 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው ። ቁጥሩ  ከፍተኛው ሆኖ መመዝገቡን  የጤና ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል። እስካሁን በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 10 ሺህ 207 ደርሷል።

እለታዊ ሪፖርቱ እንዳመለከተው 551 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 39 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 30 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣26 ከጋምቤላ ክልል ፣  3 ሰው አፋር ክልል፣ 3 ሰዎች ከሐረሪ ክልል፣ 10 ሰዎች ከድሬ ደዋ አስተዳደር፣ 3 ሰዎች ከሶማሌ ክልል፣ 21 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 11 ሰዎች ከሲዳማ ክልል፣5 ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል  እንዲሁም 2 ሰዎች ከደቡብ ክልል ተመዝግበዋል።

3 ሰዎች ህይወታቸው በቫይረሱ ምክንያት አልፏል። በዚሁ መሰረት ሕይወታቸው ያለፉ ዜጎች ቁጥር 170 እንደደረሰ ለመረዳት ተችሏል። በተመሳሳይ 196 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 5137 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን 331 ሺህ 266 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 10 ሺህ 207 ደርሷል።

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *