የውሃ ሙሌት የጀመረው የህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን መብት መሆኑንንና የውሃው ባለቤት መሆኗን ለዓለም ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ የአምስት ቀናት የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ መጀመሩ ይፋ ሆነ። ዜጎች ዘመቻውን በይፋ መቀላቀል እንዳለባቸውና ማንም ማንንም ሊቀሰቅስ እንደማይገባ ተመለከተ።
አባይ ለኢትዮጵያ በሚል መሪ ቃል ለአምስት ቀናት የሚቆየው ዘመቻ  የፊታችን ዓርብ ድረስ የሚቀጥል ነው፡፡ በዘመቻው ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ግድብ ላይ ያላትን መብት በተመለከተ የማስገንዘብ ስራ እንደሚሰራም ታውቋል። ዘመቻው ሃቅ ላይ የተመረኮዘ ግንዛቤ ከመስጠት ባሻገር ግብጽ በህዳሴው ግድብ ላይ ስታመርትና ስታሰራጭ የነበረውን ጊዜ ያለፈበት አሳሳች ትርክት ማምከንን ዓላማ አድርጓል።
በዚሁ መሰረት በተለይ በትዊተር ላይ እየተካሄደ ባለው በዚሁ ዘመቻ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ምንም ዓይነት ልዩነት ሳይገድባቸው ስለ አባይ እና የህዳሴ ግድብን በተመለከተ መረጃዎችን ማሰራጨታቸውን ጀመረዋል።
በርካቶችም ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ስላላት መብት ጥብቅና በመቆም መረጃወችን ለቀረው ዓለም እያደረሱ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የናይል ወንዝ 86 በመቶ ምንጭ ሆና ሳለ እና መቶ በመቶ በራሷ ወጪ የህዳሴ ግድብን እየገነባች ቢሆንም ለወንዙ ምንም አይነት ውሃ ከማታዋጣው ግብጽ ጋር ግን በጋራ ጥቅም በማመን ለረጅም ዓመታት ድርድሮችን ስታደርግ ቆይታለች፡፡ ድርድርን ማደናቀፍ ብቻ ሳይሆን ግብጽም ኢትዮጵያውያን በአባይ ወንዝ ላይ ምንም አይነት ግድብ ለመገንባት አቅም እንዳይፈጥሩ የአበዳሪዎችን በር ከማዘጋት ጀመሮ መልኩን በሚቀያይር ደባ ስትፈጽም ቆይታለች። አሁንም ገፍታበታለች። ግብጾች ኢትዮጵያን የማዳከምና ገጽታዋን የማጠልሸት ዘላቂ ግብ በመያዝ በመስራት ላይም ይገኛሉ፡፡
ኢትዮጵያውያኑም ከራሳችን ከሚመነጭ ውሃና ከራሳችን በተዋጣ ገንዘብ የምንገነባው የህዳሴ ግድብ ግንባታውም ሆነ አፈጸጻሙ ለሌላ ፈቃጅና ከልካይ ፍላጎት የሚተው አይደለም በሚል ኢትዮጵያ የያዘችውን ፍትሃዊ አቋም በእነዚህ ቀናት የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻዎች ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ግንዛቤ በመፍጠር ላይ ይገኛሉ።
እየንዳንዱ ግብጻውያን በአባይ ወንዝ ላይ አንድ እንደሆኑ ሁሉ ኢትዮጵያዊያንም በተባበረ ክንድ የግብጽን ደባ ለመመከትና ዓለም የያዘውን የተንሸዋረረ አቋም ከማስቀየር አንጻር ይህንን ዘመቻ በትጋት መቀላቀል እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ተመልክቷል።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *