“Our true nationality is mankind.”H.G.

በጥናትና ምርምር በመመሥረት የአማራ ክልልን ምጣኔ ሀብት ለማሻሻል የሚሠራ የሽግግር ማዕከል ተመሠረተ

Amhara is one of the nine ethnic divisions (kililoch) of Ethiopia, containing the homeland of the Amhara people. Previously known as Region 3, its capital is Bahir Dar.

የአማራ የኢኮኖሚ የሽግግር ማዕከል ትናንት ሐምሌ 12 ቀን 2012ዓ.ም የምሥረታ ጉባኤውን አካሂዶ ሰባት አባላት ያሉት ሥራ አስፈጻሚ ሰይሟል፡፡ የሺግግር ማዕከሉ የክልሉን ሕዝብ ምጣኔ ሀብታዊ ችግሮች ለመፍታት የሚያስችል ሙያዊ አስተዋጽኦ ለማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ከ200 በላይ የአማራ ምሁራን የመሠረቱት ለትርፍ ያልተቋቋመ ነው፡፡
በጉባኤው እንደተገለጸው በጥናትና ምርምር በመታገዝ የክልሉን ምጣኔ ሀብታዊ ችግሮች ለመፍታትና የምጣኔ ሀብት ሽግግር ለማምጣት ማዕከሉ ይሠራል፡፡
ክልሉ የተለያዩ ተፈጥሯዊ ፀጋዎች ቢኖሩትም ፀጋዎቹን አልምቶ ለመጠቀም የሚያስችል አደረጃጀትና አሠራር ባለመኖሩ የክልሉ ሕዝብ ሕይወት ከመሻሻል ይልቅ በየጊዜው ፈተናዎች እየበዙበት እንደመጣ በመሥራች ጉባኤው ውይይት ተመላክቷል፡፡
የአማራ ኢኮኖሚ ሽግግር ማዕከል መሥራችና የሥራ አስፈጻሚ አባል ዶክተር ለጤናህ እጅጉ እንደተናገሩት ማዕከሉ የተመሠረተው ከላይ የተገለጸውን የአደረጃጀትና የአሠራር ክፍተት ለመሙላት ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታዬ ያለውን የምሁራን ንቁ ሀገራዊ ተሳትፎ በዕውቀት፣ በጥበብና በምርምር በመደገፍ በክልሉ የሚታየውን ሁለንተናዊ የምጣኔ ሀብት ችግር ለመቅረፍ የሽግግር ማዕከሉ የድርሻውን እንደሚወጣ ተመላክቷል፡፡
የአማራ የኢኮኖሚ የሽግግር ማዕከል በሁለት ዓበይት ክፍሎች 30 የሚደርሱ ፕሮጀክቶች እንዳሉት ዶክተር ለጤናህ ተናግረዋል፡፡ በዚህ ወቅትም ምጣኔ ሀብታዊ ሽግግር ማምጣት የሚያስችሉ 18 ፕሮጀክቶች የመኖራቸውን አስታውቀዋል፡፡
የአማራ ኢኮኖሚ ሽግግር ማዕከል ሕጋዊ ሰውነት ለማግኘት የሚያስችሉ የዝግጅት ሥራዎችን ማጠናቀቁን የገለጹት ዶክተር ለጤናህ ጎን ለጎንም በበርካታ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተሳትፎ እያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታን በሚመለከት ግብጽ የምታራምደውን ተገቢ ያልሆነ እንቅስቃሴ በመቃወም በመላው ዓለም ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ከ47 ሺህ በላይ የድጋፍ ፊርማ መሰብሰቡንም ዶክተር ለጤናህ አስታውቀዋል፡፡ ፊርማውን ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለማስገባት እየተሠራ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው
(አብመድ)

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ፋኦ በትግራይ ክልል ለአርሶ አደሮች የእህል ዝርያዎችን ማሰራጨትና እንስሳቶችን መከተብ ጀመረ
0Shares
0