“Our true nationality is mankind.”H.G.

ሰበር ዜና ” የሕዳሴው ግድብ ተሸጠ” v “አባይ በአገሩ በክብር ተከተረ “

ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ብሎ የሚጠራው ቡድን ” የአባይ ግድብ ተሽጧል” ሲል በይፋ በተደጋጋሚ አስታውቋል። በተለይም ራሳቸውን ከፖለቲካ አመራር ወደ ፌስቡክ አክቲቪስትነት ያሳደጉት አቶ ጌታቸው ረዳ ከቀናት በፊት ” እኛ ወይስ አብይ ለግብጽ እንቀርባለን” ሲሉ በድጋሚ የግድቡን ለግብጽ መሸጥ ሲያስተጋቡ ተደምጠዋል።
እኚሁ በየደቂቃው በፌስቡክና በዩቲዩብ ምሽግ የሰሩት የህወሃት ቃል አቀባይ ” የህዳሴው ግድብ ተሽጧል” በማለት ሲወተውቱና የማጠልሸት ዘመቻቸውን ቢያጠናክሩም ትናንት በይፋ ኢትዮጵያዊያን ደስታቸውን ገልጸዋል። እልል ብለዋል። ከትግራይ ሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ህዝብ የደስታ ስሜቱን አንጸባርቋል።
Image may contain: 3 people, suit, text that says 'thank you'
በድርድር መስመር ለማስያዝ፣ በተግባር ስራውን ብልሽቱን አርቆ በማጣደፍ ለተሰራው ስራ ህዝብ ምስጋናውን በአደባባይ ሲገልጽ፣ በምስልና በርችት ስሜቱን ሲቀያየር ያረፈደው ” ተሸጠ” የተባለው አባይ አገሩ ውስጥ ተከትሮ በክብር ሃይቅም፣ ወንዝም መሆኑ ይፋ መደረጉን ተከትሎ ነው።
ከሚቲሪዮሎጂ ጋር በመናበብ አባይ ተፈጥሯዊ ጉዞውን ሳይቀይር የሚፈለገው ውሃ መያዙን መንግስት ይፋ ሲያደርግ ” ተሸጠ” ሲሉ የነበሩ ሃይሎች ምን አዲስ ዘመቻ እንደሚጀመሩ ባይታወቅም አንዳንዶች ደስታቸውን ሲገልጹ ታይተዋል። ፋና የሚከተለውን አስፍሯል።
የታላቁ የህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ።
የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የአፍሪካ ህብረት ዓባላት ቢሮ መሪዎች በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያካሄዱትን ውይይት አስመለክቶ መግለጫ አውጥቷል።
በመግለጫው በቀጣናው የታየው ወቅታዊ የዝናብ እና የፈሰስ መጠን መጨመር ግድቡን ለመሙላት ሁኔታዎችን አመቺ አድርጓል፡፡
የግድቡን የመጀመሪያ የውኃ ሙሌት እና ዓመታዊ የሥራ ክንውን አስመልክቶ፣ ኢትዮጵያ ሚዛናዊ እና ሦስቱም ሀገራት በፍትሐዊነት ከ ዓባይ ወንዝ እንዲጠቀሙ የሚያስችል ድርድርን ለማካሄድ ባላት አቋም ትቀጥላለች ብሏል ፅህፈት ቤቱ።
ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከተገኘው ከፍተኛ የዝናብ መጠን የተነሣ፣ የግድቡ የመጀመሪያ ዓመት የውኃ ሙሌት ተጠናቋል ያለው ፅህፈት ቤቱ ውኃው በግንባታ ላይ ያለውን ግድብ አልፎ እየፈሰሰ እንደሚገኝ አስታውቋል።
በትናትናው ዕለት የተካሄደውን የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበርና የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ስሪል ራማፎሳ በቪዲዮ ኮንፈረንስ የተካሄደውን ስብሰባ መርተውታል።
በስብሰባው ላይም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ፣ የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ እና የግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ተሳትፈዋል።
በተጨማሪም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ መሃመትን ጨምሮ የቢሮው አባላት የሆኑት የኬንያ፣ የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና የማሊ ሀገራት መሪዎች እና ተወካዮችም ታድመዋል።
ውይይቱን ተከትሎም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ፥ በደቡብ አአፍሪካው ፕሬዚዳንት ስሪል ራማፎሳ አመቻችነት ለአፍሪካዊ ችግር አፍሪካዊ መፍትሄ የሚለውን ለማጠናከር ፍሬያማ ውይይት አካሂደናል ብለዋል።
በግድቡ ውሃ አሞላል ዙሪያም ቴክኒካዊ ውይይቶችን ቀጥሎ ለማካሄድ የጋራ መግባባት ላይ ለደረሱት የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ እና ለግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲም አድናቆታቸውን ገልፀዋል።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ቻይና በአፍሪካ ኅብረት አሸማጋይነት የሚካሄደውን የህዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር እንደምትደግፍ ገለጸች
0Shares
0