በኢትዮጵያ ተጨማሪ 561 ሰዎች ላይ ቫይረሱ መገኘቱ ሲረጋገጥ 7 ሰዎች ደግሞ ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ ህይወታቸው ማለፉን የጤና ሚኒስቴርና የሕብረተሰብ ጤና ተቋም አስታወቁ።

ማክሰኞ ሐምሌ 14/2012 ዓ.ም በወጣው ዕለታዊ የኮሮናቫይረስ ሪፖርት ላይ እንደተመለከተው በ6 ሺህ 544 ሰዎች ላይ በተደረገ ምርመራ 561 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

የወረርሽኙ ሁኔታ ሪፖርት ላይ እንደተገለጸው በሽታው ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ማለትም 409 ሰዎች የተገኙት በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ሲሆን፤ 52 ከጋምቤላ፣ 25 ከኦሮሚያ፣ 16 ከትግራይ፣ 12 ከድሬዳዋ ፣ 11 ከደቡብና የተወሰኑ ሰዎች ከሌሎች ክልሎች ተገኝተዋል።

ዕለታዊው መግለጫ ከዚህ በተጨማሪም ከዚህ በፊት በወረርሽኙ መያዛቸው ተረጋግጦ የህክምና ክትትል ሲደረግላቸው ከነበሩ ሰዎች መካከል ተጨማሪ 158 ሰዎች ከበሽታው በማገገማቸው እስካሁን በኢትዮጵያ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥርን 5448 አድርሶታል።

በቫይረሱ ምክንያት ሰባት ሰዎች የሞቱ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ አራቱ በአስከሬን ላይ በተደረገ ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን በዚህም በአገሪቱ ከበሽታው ጋር በተያያዘ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 180 ደርሷል።

ኢትዮጵያ እስካሁን 342 ሺህ 866 ናሙናዎች ላይ ምርመራ በማድረግ በአጠቃላይ 11 ሺህ 072 ቫይረሱ ያለባቸውን ሰዎች አግኝታለች። ቢቢሲ ከጤና ጥበቃ ወስዶ እንደዘገበው

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *