ሚኒስትሯ በቲውተር ገጻቸው ይፋ እንዳደረጉት የ9 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት አልፏል። ይህም በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 197 አድርሶታል።

በተመሳሳይ ዜና በትናንትናው እለት 139 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 5 ሺህ 645 መድረሱም ተገልጿል።

ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን 357 ሺህ 58 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 11 ሺህ 993 ደርሷል።

አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 6 ሺህ 89 ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 65 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

እስካሁን በኢትዮጵያ 5 ሺህ 645 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገገሙ፤  የ197 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 2 ሰዎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ይታወሳል።

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *