“Our true nationality is mankind.”H.G.

ከመስከረም 30 በሁዋላ መንግስት የለም በሚል ሲቀሰቅሱ የነበሩት አቶ ልደቱ አያሌው በቁጥጥር ስር ዋሉ

አቶ ልደቱ አያሌው በፌዴራል ፖሊስ አማካኝነት ዛሬ ሐምሌ 17/2012 ዓ.ም ረፋድ ላይ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ። የኢዴፓ መስራቹና ፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌው በቁጥጥር ስር የዋሉት በቢሸፍቱ ከተማ በተፈጠረ ብጥብጥ ተሳትፎ አድርገሃል በሚል መሆኑን መረጃው ያሳያል።
በቁጥጥር ስር ያዋላቸው የፌዴራል ፖሊስ ሲሆን ወደ ቢሸፍቱ ከተማ ለመውሰድ ፖሊስ በዝግጅት ላይ መሆኑን አቶ ልደቱ ለአውሎ ሚዲያ ተናግረዋል።
ዛሬ ጠዋት ወደ ፌዴራል ፖሊስ ቢሮ ያመራሁት በስልክ ተደውሎ መጥሪያ ወጥቶብ በህግ እየተፈለግህ ነው ስለተባልሁ አልተደበቅሁም የምፈለግበት ጉዳይ ምንድን ነው የሚለው ለማረጋገጥ በሔድሁበት ነው ብለዋል። አቶ ልደቱ በቀጣይ እሁድ ወደ አሜሪካን ሀገር ለህክምና ቀጠሮ ስላላቸው ለመጓዝ ትኬት ቆርጠው እየተጠባበቁ እንደነበርም አሳውቀውናል።
የመጥሪያ ደብዳቤው እንደሚያመለክተው አቶ ልደቱ አያሌው በሚኖሩበት በቢሾፍቱ ከተማ የተፈጠረውን ብጥብጥ በማስተባበርና በገንዘብ በመደገፍ ተጠርጥረው እየተፈለጉ የነበረ ቢሆንም ፖሊስ ወደ ፍርድ ቤት በአስገዳጅ ሁኔታ በ48 ሰዓታት ውስጥ እንዲያቀርባቸው ከአካባቢው ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተሰጥቶታል። አቶ ልደቱ አያሌው በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል እንደሚያምኑ በተለያዩ ጊዚያት የተናገሩ እና ሶስተኛው አማራጭ በሚል ሀሳባቸው የሚታወቁ ቢሆንም አሁን ግን አመፅ በመምራትና በገንዘብ በመደገፍ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ናትናኤል እንደዘገበው

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   የመ/ሰራዊትን መለያ ለብሶ ከሱዳን ወደ ወልቃይት ሊገባ የነበረ የትህነግ የሽብር ሃይል ተደመሰሰ፤
0Shares
0