… በዶክተር አምባቸው ላይ የፈፀምኩትን ስህተት በጠቅላይ ሚንስትር አብይ ላይ መድገም አልፈልግም። ሰው ተሰባሪ ነው! እግዚአብሄር ክፉውን ነገር ያርቅ እንጂ ዶክተር አብይ አንድ ነገር ቢሆኑ ወይም ከስልጣናቸው ተነስተው አገሪቱ ወድ ትርምስ ብታመራ “አያሳዝንም ወይ” እያልኩ ሳንጎራጉርና በፀፀት ራሴን ስገርፍ መኖር አልፈልግም። ለዚህ ነው “አብይን የምደግፈው ለራሴ ስል ነው” የምለው! “ድጋፍ በሚሻበት ሰአት ለምን ከጎኑ አልቆምኩም?” የሚል የጥፋተኝነት ስሜት ሳይሰማኝ አልጋየ ላይ መውደቅና የሰላም እንቅልፍ መተኛት ስለምፈልግ ነው አብይን የምደግፈው!


አብይን የምደግፈው አዎ ለራሴ ስል ነው! ከፀፀት ለመዳን፤ ከህሊና ወቀሳ ለመትረፍ ስል! ዶክተር አምባቸው መኮንን ከተገደለ በሗላ የተሰማኝን ስሜት እኔ ነኝ የማውቀው። የክልሉ ፕሬዝዳንት ሆኖ በሀላፊነት በቆየባቸው ሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ በውጥረት ተከቦ በርካታ በጎ ስራዎችን አከናውኗል። ጥሩ ስራ ሲሰራ አንድም በጎ ቃል ትንፍሽ አላልኩም ነበር ።ኦሮሚያ ክልል ሄዶ ስለልዩ ጥቅም አወራ ሲባል ግን እሱን ለመተቸት ማንም አልቀደመኝም ።
አሁን የአምባቸውን ምስል ፌስቡክ ላይ ባየሁ ቁጥር ፀፀቱ ይገርፈኛል። እሱን ተችቼ የፃፍኩትን ፅሁፍ ከፌስቡክ ገፄ አጥፍቸዋለሁ። የጥፋተኝነት ስሜቱ ግን ከህሊናየ ሊጠፋ አልቻለም። ይህ ፀፀቴ በጠቅላይ ሚንስትር አብይ እንዲደገም አልፈልግም። ዶክተር አብይ ወደስልጣን ከመጡ በሗላ ተዘርዝረው የማያልቁ በርካታ ለውጦችን ያመጡ ቢሆንም ከምስጋና ይልቅ በየቀኑ ትችት ሲያስተናግዱ የሚውሉ መሪ ሆነዋል። (የገቡበትን አጣብቂኝ ዘግይቸ እስከምረዳ ድረስ ላይ ላዩን እየተመለከቱ ከሚተቿቸው ሰዎች መካከል አንዱ እኔ ነበርኩ። ለዚህም ይቅርታ እጠይቃለሁ። )
ለመሆኑ ዶክተር አብይ በስንት ጠላቶችና ፅንፈኛ ሀይሎች ተከበው አበሳቸውን እንደሚያዩ አስበንው እናውቃለን?
በአንድ በኩል ከስልጣን የተወገደው ህወሀት የተባለው የሽማግሌዎች ስብስብ ቡድን ወደስልጣን እንደማይመለስ ቢያውቀውም “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” በሚል ብሂል ኢትዮጵያን ይበታትንልኛል የሚለውን የጥፋት እቅድ በየጊዜው ሲሸርብና ሲያስፈፅም ይውላል። በሌላ በኩል ኦነግ ሸኔና አባ ቶርቤ የተባሉ አሸባሪ ቡድኖች የመንግስት ሀላፊዎችንና ታዋቂ ሰዎችን እየተከታተሉ ይገድላሉ።
አሁን የአምባቸውን ምስል ፌስቡክ ላይ ባየሁ ቁጥር ፀፀቱ ይገርፈኛል። እሱን ተችቼ የፃፍኩትን ፅሁፍ ከፌስቡክ ገፄ አጥፍቸዋለሁ። የጥፋተኝነት ስሜቱ ግን ከህሊናየ ሊጠፋ አልቻለም። ይህ ፀፀቴ በጠቅላይ ሚንስትር አብይ እንዲደገም አልፈልግም። ዶክተር አብይ ወደስልጣን ከመጡ በሗላ ተዘርዝረው የማያልቁ በርካታ ለውጦችን ያመጡ ቢሆንም ከምስጋና ይልቅ በየቀኑ ትችት ሲያስተናግዱ የሚውሉ መሪ ሆነዋል። (የገቡበትን አጣብቂኝ ዘግይቸ እስከምረዳ ድረስ ላይ ላዩን እየተመለከቱ ከሚተቿቸው ሰዎች መካከል አንዱ እኔ ነበርኩ። ለዚህም ይቅርታ እጠይቃለሁ። )
ግብፅ በአባይ ግድብ ግንባታ ላይ የአብይን አስተዳደር መፈናፈኛ አሳጥታ ይዛዋለች። የአንድነት ሀይሉና የአማራ ብሄርተኞች በበኩላቸው “የፊዴራልና የአዲስ አበባ መስተዳድር የሀላፊነት ቦታዎች በተረኝነት በኦሮሞዎች ብቻ ተያዘ” ብለው ጩኸታቸውን ያሰማሉ። “ጊዜው የኦሮሞ ነው” ብሎ የሚያስበው በጃዋር መሀመድ ይመራ የነበረው ፅንፈኛ ቡድን ደግሞ “ሁሉንም ነገር እኛ ካልተቆጣጠርነው ለውጥ የለም” የሚል ድምዳሜ ላይ ስለደረሰ “የአብይ አስተዳደር የነፍጠኛን አሀዳዊ ስርአት ለመመለስ እየሰራ ነው” ብሎ ስሙን ያጠፋል፤ አመፅ ይቀሰቅሳል። እንደ ለማ ሱሴ አይነት “ለውጡ ተቀልብሷል” በሚል ያኮረፉ ሰዎች ደግሞ በመንግስት የሀላፊነት ቦታ ላይ ተቀምጠው ሴራ ይጎነጎናሉ። “የብሄር ፖለቲካ መታገድ አለበት፤ ህገ መንግስቱም አሁኑኑ ተቀዶ መጣል አለበት” የሚለው ወገን ደግሞ “ነውጥ እንጂ ለውጥ አልመጣም” እያለ በየቀኑ የአብይን ስም ሲያብጠለጥል ይውላል።
እንግዲህ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ በነኝህ ችግሮች ሁሉ ተከበው፣ እንደ ገና ዳቦ ከላይና ከታች እየተለበለቡ ነው እያንዳንዱን ቀን የሚያሳልፉት። ግን ለምንድነው በጎውን ነገር የማንመለከተው? ህወሀት ከስልጣን ከተወገደ በሗላ በዶክተር አብይ አመራር አማካኝነት የመጡ ለውጦችን ለመረዳት የተቸገርንበት ምክንያትስ ምንድነው?
ወያኔ በምርጫ ቦርድና በፍርድ ቤት ጉዳይ እንደማይደራደር አለም ያወቀውና ፀሀይ የሞቀው እውነታ ነበር ። ዶክተር አብይ ግን በነዚህ ተቋማት ላይ መአዛ አሸናፊንና ብርቱካን ሚዲቅሳን ሲሾሙ “ለእኔ ያገለግሉኛል” ብለው አስበው እንዳልሆነ ሁላችን የምንረዳው ጉዳይ ነው። በተለይ ብርቱካን በገለልተኝነቷና በጠንካራ አቋሟ ተፈትና ያለፈች ሴት ናት።
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሆኖ የተሾመው ዶክተር ዳንኤል በቀለም መንግስት የሚፈፅመውን ወንጀል ሊደብቅላቸው እንደማይችል ጠቅላይ ሚንስትሩ ጠንቅቀው ያውቃሉ። እነኝህን ሰዎች የሾሟቸው “እኔን ይደግፉኛል” ብለው ሳይሆን ለውጥ በማምጣት ሂደት ውስጥ አስተዋፅኦ ያበረክታሉ ብለው በማመናቸው እንደሆነ ግልፅ ነው።
ክልሎች ያለማንም ጣልቃ ገብነት ራሳቸውን በራሳቸው ማስተዳደር ችለዋል።የመናገርና የመፃፍ ነፃነት ምህዳሩ እጅግ ከመስፋቱ የተነሳ አንዳንድ ሰዎች ከመተቸት አልፈው ጠቅላይ ሚንስትሩን እስከመዝለፍ ደርሰዋል።
የግል ሚዲያውም አብይን ካልተቸ በስተቀር የሰላም እንቅልፍ መተኛት የሚችል አይመስለውም። ኦኤምኤን፣ ትግራይ ሚድያ ሀውስ፣ድምፂ ወያነ፣ኩሽ ሚድያ፣ ርዕዮት ሚዲያ፣ አዲስ ስታንዳርድ፣ አዲስ ፎርቹን፣ አባይ ሚድያ፣ ኢትዮ 360 ሚዲያና ጃዋር አስተዋውቆለት ከመቶ ሺህ በላይ ተከታዮችን ያገኘው እንደ ፊንፊኔ ኢንትርሴፕት አይነት አነስተኛና ጥቃቅን የፊስቡክ ገፅ ሳይቀር በየቀኑ ጠቅላይ ሚንስትር አብይን ሲያብጠለጥሉ ይውላሉ።
የሚያሳዝነው ኢትዮጵያ እንድትበታተን የሚፈልጉት ብቻ ሳይሆኑ “ኢትዮጵያን እንወዳለን” የሚሉት ወገኖች ጭምር በማወቅም ይሁን ባለማዎቅ የዚህ ዘመቻ ተካፋዮች መሆናቸው ነው። በመለስ ዜናዊ የግፍ አገዛዝ ዘመን እንኳን እንደዚህ አይነት የተቀናጀ የሚዲያ ዘመቻ ተካሂዶ አያውቅም።
ጠቅላይ ሚንስትሩን በማጣጣል ረገድ እንደ እኔ አይነቱ ተራው ዜጋም አልቦዘነም። አፄ ምኒልክ ሩህሩህና ትዕግስተኛ መሪ እንደነበሩ ታሪክ ይነግረናል። ለዚህም አሁንም ድረስ “እምየ ምኒልክ” ብለን እንጠራቸዋለን። ይገባቸዋል! ነገር ግን ጠቅላይ ሚንስትር አብይ “መግደል መሸነፍ ነው፤ፍቅር ያሸንፋል” ብለው በፍቅርና በሰላም ተከባብሮ መኖር እንደሚገባ ሲነግሩህ ” ይሄ የሀይማኖት ሰባኪ ነው፤ አገር መምራት አይችልም” ብለህ ታጣጥለዋለህ። ዘግይቶም ቢሆን የአገር ደህንነትን ለማስጠበቅ በወንጀለኞች ላይ እርምጃ መውሰድ ሲጀምር ደግሞ “አምባገነን ሆነ” የሚለውን የወያኔን ዘለፋ ታስተጋባለህ።
ይሄ ሰው ግን አያሳዝንህም? ቴዲ አፍሮ “አያሳዝንም ወይ” እያለ ለአፄ ቴውድሮስ ያቀነቀነውን ዜማ ስንሰማ “በወቅቱ የነበሩ ኢትዮጵያውያን እንዴት የቴውድሮስን አላማ መረዳት አቃታቸው?” ብለን በፀፀት ተውጠን አብረን እናንጎራጉራለን። በተቃራኒው ደግሞ አሁን ከጎናቸው ቆመን ድጋፍ ልንለግሳቸው የሚገባውን መሪ በየቀኑ ስናወግዛቸው እንውላለን።
ግን ግን …ዶክተር አብይ የሰሩት ሀጥያት ምንድነው? እግዚአብሄርን በመፍራታቸውና ኢትዮጵያን በመውደዳቸው? የመጡበትን ጎሳ ለይተው “እንኳን ከዚህ ወርቅ ህዝብ ተፈጠርኩ” ባለማለታቸው? በወረደ ቋንቋ ለሚተቿቸውና ለሚሰድቧቸው ሰዎች መልስ ባለመስጠታቸው? ተጥሎ የተገኘን ልጅ አንስተው በማሳደጋቸው? ትሁት በመሆናቸው? የፖለቲካ እስረኞችን በመፍታታቸው? የታሰሩ ስደተኞችን አስፈትተው ራሳቸው በሚጓዙበት አውሮፕላን ይዘው በመመለሳቸው? ችግኝ በመትከላቸው? አዲስ አበባን በማስዋባቸው? ሙስና ውስጥ ባለመዘፈቃቸው? አስር አመት የተጓተተውን የአባይን ግድብ ግንባታ አፋጥነው ውሀ ሙሌት በመጀመራቸው? ኢትዮጵያን እናበልፅግ በማለታቸው? እኔ ሊገባኝ አልቻለም።
ይህንን ስል ዶክተር አብይ ፍፁም ናቸው እያልኩ አይደለም። እንደማንኛውም ሰው በንግግርም ይሁን በአሰራር ይሳሳታሉ። የኢትዮጵያ የቀድሞ መሪዎች ፍፁም እንዳልነበሩት ሁሉ የአሁኖቹም ፍፁም ሊሆኑ አይችሉም። ሰው ናቸውና ያጠፋሉ ፤ይሳሳታሉ። ድጋፋችን የምንሰጣቸው ፍፁም ናቸው ብለን ሳይሆን ትልቋን ስዕል ማለትም ኢትዮጵያን ታሳቢ በማድረግ ነው።
ህዝቡ ለዶክተር አብይ የሰጠውን ድጋፍ ቀንሶ የነበረው የጠቅላይ ሚንስትሩ አስተዳደር ጃዋር ላይ ያሳይ በነበረው መለሳለስና ማባበል ምክንያት መሆኑን ብዙዎቻችን የምናውቀው እውነታ ነው። ግን በወቅቱ ከነበረው ተጨባጭ ችግር አንፃር እኛስ በጠቅላይ ሚንስትሩ ቦታ ብንሆን ኖሮ ምን የተለየ ነገር እናደርግ ነበር?
የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊው አቶ ታየ ደንደአ ሰሞኑን በአንድ ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት ጃዋር መሀመድ “ተከበብኩ” ብሎ ያስተላለፈውን ጥሪ ተከትሎ ለተገደሉ 97 ሰላማዊ ዜጎች ተጠያቂ ተደርጎ ቢታሰር ኖሮ የጃዋርን እስር በመቃወም ሊከሰት የሚችለውን ብጥብጥ መቆጣጠር የሚችል የተቀናጀ የፀጥታ ሀይልና መዋቅር አልነበረም። ሥለዚህ የማይቻል ነገር ነካክቶ የማይወጡት አዘቅት ውስጥ ከመግባት ይልቅ ጠንካራ የፀጥታ ሀይል እስከሚደራጅ ድረስ ፈተናውን በትዕግስት ማለፍ ይጠይቅ ነበር።
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድም ባለፈው ሳምንት ከኦቢኤን ቴሌቭዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የግል ጠባቂዎቻቸውን እንኳን ለመቀየር የተቸገሩበት ጊዜ እንደነበር ገልፀዋል። እንግዲህ ዶክተር አብይ ይህንን ሁሉ ፈተና አልፈው ነው መንግስታቸውን አጠናክረው ህግ ማስከበር የጀመሩት። ታዲያ እኝህ ሰው ድጋፍ አያስፈልጋቸውም?
እኔ በበኩሌ ከላይ እንደገለፅኩት በዶክተር አምባቸው ላይ የፈፀምኩትን ስህተት በጠቅላይ ሚንስትር አብይ ላይ መድገም አልፈልግም። ሰው ተሰባሪ ነው! እግዚአብሄር ክፉውን ነገር ያርቅ እንጂ ዶክተር አብይ አንድ ነገር ቢሆኑ ወይም ከስልጣናቸው ተነስተው አገሪቱ ወድ ትርምስ ብታመራ “አያሳዝንም ወይ” እያልኩ ሳንጎራጉርና በፀፀት ራሴን ስገርፍ መኖር አልፈልግም። ለዚህ ነው “አብይን የምደግፈው ለራሴ ስል ነው” የምለው! “ድጋፍ በሚሻበት ሰአት ለምን ከጎኑ አልቆምኩም?” የሚል የጥፋተኝነት ስሜት ሳይሰማኝ አልጋየ ላይ መውደቅና የሰላም እንቅልፍ መተኛት ስለምፈልግ ነው አብይን የምደግፈው!

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *