“Our true nationality is mankind.”H.G.

ኦነግ እና ሕወሓት – በሬ ካራጁ እንዲሉ አራክሶ፣ ጨፍጭፎ፣ አስሮ፣ አሸባሪ ብሎ ካባረረው ጋር ወዳጅነት


ሕወሓትም ከወለጋ ጫካ አሳዶ እነ ለገሰ ወጊን ገድሎ እንዳላባረረ ዛሬ ኦነግ ወለጋን ብቻ ሳይሆን ኦሮሚያን እንዲቆጣጠር ደጋፊ ሆኖ ወጥቷል። የወጋም የተወጋም ነገራቸውን በይደር ትተው መተባበራቸው ድል ቢመጣ ታሪክን መድገማቸው የማይቀር ቢሆንም ዋናው ጉዳይ ግን የፀረ-አማራና ፀረ-ምንሊክ ተረት ተረት ነው!

By  Anmut A.
ኦነግና ሕወሓት የ60ዎቹ ትግል ውጤት ብቻ ሳይሆኑ በተለያየ ቅርፅና አመክንዮ የብሔር ጥያቄን ይዘው የተነሱም ናቸው።
ሕወሓት በኦነጋውያን ዘንድ የአቢሲኒያ ገዢ መደብ አካል የሆነና ያንን መደብ በብሔር መብት ሽፋን ያስቀጠለ ነው። ኦነግ ለሕወሓታውያን የፀረ-አማራ ትግል ወሳኝ አጋር ቢሆንም ሌሎች የአማራን ንቅናቄ የሚገዳደሩ ኃይሎች እስከተፈጠሩ ድረስ አላስፈላጊ ፀረ-ዲሞክራሲያዊ ተቀናቃኝ ቡድን ነው።
ሕወሓትም የሻዕቢያን ትግል የፀረ-ቅኝ ግዛት ትግል ባለው መጠን የኦነግን ትግል ትግል በተመሳሳይ የፀረ-ቅኝ ግዛት ትግል አላለውም ነበር።
❶ ቀዳሚ የአጋርነት ሙከራ
ገና ድሮ በትጥቅ ትግል ወቅት ሕወሓት የመሐል አገር ‘መናጆ’ (አጓጓዥ) እያማረጠ ባለበት ወቅት ከኦነግ ጋር በትብብር ለመስራት ጥያቄ አቅርቦ ነበረ ። ነገር ግን ኦነግ “ከአቢሲኒያ ኃይሎች ጋር አልሠራም” በማለቱ ሳይሆን ቀርቷል።
ቆይቶም የፀረ-ደርግ ትግሉ ወደመሐል አገር መጠጋት ሲጀምር በምዕራብ ኦሮሚያ አካባቢ የትብብር ጦርነት ለማድረግ ሞክረው የነበረ ቢሆንም ሕወሓት ኦነግን በፀረ-ዲሞክራሲያዊነት (ጠባብነትና ተገንጣይነት) ፈርጆት ስለነበር እንደማይሆን አውቆ ቀድሞ ተዘጋጅቶበታል ። ይሔውም ቀዳሚነቱንና የበላይነቱን የሚቀበል የኦሮሞ የፖለቲካ ኃይል ከደርግ ተማራኪዎች አሰባስቦ 1982 ላይ ኦህዴድን መስርቶ ነበር።
ኦህዴድ የተመሠረተበት ምክንያት ከኦነግ ጋር አጋርነት መፍጠር እንደማይቻል በማመን ለአገራዊ ገፅታ ማሟያ ኦሮሚያን እንዲወክል ነው።
ሕወሀትና ኦነግ ሸኔ….!!! (ነአምን ዘለቀ) | EthioReference
እናም ወደመጨረሻ ላይ ከኦነግ ጋር የተፈጠረ ወታደራዊ ትብብር ከከሸፈው የሽግግር መንግስት ተሳትፎ ግብዓትነት ያለፈ አይደለም።
በርግጥ የኦነግ ተገንጣይነት አስተሳሰብ በዘመኑ የኦሮሞ ልሒቃን ዘንድ ከነበረው ተቀባይነትና የኦሮሞ ብሔርተኝነት ቅስቀሳ አኳያ ኦነግን ለማባበል ሻዕቢያም ተሳትፎ የህገመንግስቱን መነሻ የሽግግር ቻርተር በመንደፍ ጭምር እንዲሳተፍ ተደርጎም ነበር።
ይሔም በዋናነት በአፍሪካ ቀንድ የበላይነት ፉክክር ውስጥ ለነበሩት ሕወሓትና ሻዕቢያ በቅርብ የነበረ : በመጠኑም የተደራጀ ኃይል በመሆኑ አጀንዳው የአካባቢውና የአላማቸው ቀውስ ምክንያት እንዳይሆን ነው። እናም ኦነግ በአንድ እጅ የነፃ ሪፐብሊክ ፕሮግራም ይዞ በአንድ እጅ የሽግግር ቻርተርን ለማስፈፀም ፈረመ።
❷ የሽግግር ትብብር
የሽግግር መንግስት ምስረታ ሒደቱን ጠቀሜታ ከማንም በላይ የተረዳው ሕወሓት ነበር። አንድም በውስጥና በውጭ መንግስታት ዘንድ ህጋዊነትና ተቀባይነት ለማግኘት በአሳታፊነቱ የማይተች እንዲሆን ለማድረግ እንደማይሆኑና እንደሚባረሩ ያመነባቸውን እንደኦነግ ያሉ በወቅቱ የተደራጁ አኬላትን ሁሉ በመጋበዝ አገራዊ ቁጥጥሩን አደላደለ። በሽግግሩ ውስጥ በሹመት ጭምር አሰለፋቸው።
ቀድሞ የተመሠረተው ኦሕዴድና ኦነግም በተለያየ አሰላለፍ አንድን ሕዝብ ወክለው አመራሮቹ የሽግግር መንግስቱ ባለስልጣናት እስከመሆን ደርሰው ነበር። የኦሕዴድ ቀድሞ መፈጠር ጣጣ በኦነግ ሚዛን “የአቢሲንያ ኃይሎች ተለጣፊና ተላላኪ” በሚል ርስበርስ እንዲባሉ ምቹ ሁኔታ ተፈጠረ። የኦሕዴድ አባልና ደጋፊ የተባለ ኦሮሞ ላይ ግፍ ተፈፀመ።
ዞሮ ዞሮ ቀድሞም የታሰበበት ነበርና በሽግግር ሂደት ከኦነግ ጋር ሊፈጠር የነበረ ትብብር በተለያየ ምክንያት ተበላሽቶ ኦነግ ከሽግግር ሂደቱም : ከአገርም ሊወጣ ቻለ።
አሸባሪነትን የጨመረ ፀረ-ኦነግ ዘመቻ
ኦነግ በኦሮሚያ ኦሕዴድ ናችሁ እያለ ስንቱን እንዳልፈጀ : በቀጣዮቹ አመታት እንደገና ኦነግ ናችሁ ተብለው የተጠረጠሩ የኦሮሚያ ልሒቃንና ወጣቶች ፍዳቸውን አይተዋል። ኦነግም ቀድሞ ለ18 አመታት ሲያደርገው የነበረውን የትጥቅ አማራጭ ከደርግ ማግስት ለቀጣይ 25 አመታት እንዲባዝንበት ተገደደ። ተገንጣይነትን መነሻ ያደረገ የጠባብነት ዋነኛ ባለቤት ተገኘ። መብት ጠያቂ ሁሉ “ሲፋቅ ኦነግነት ነው” ተባለ።
ገና በረሃ እያለ የአጋርነት ጥያቄ ያቀረበውና በሽግግር ሂደቱም ጋባዥ የነበረው ሕወሓት ኦነግን ከወለጋና ሐረርጌ ጠረገው። አልፎም በተስፋ መቁረጥ የተሰለፈውን ኦነግ በፓርላማ ፊት በአሸባሪ ድርጅትነት ፈረጀው። አሸባሪ ከተባለው ኦነግ ጋር የተገናኘ: አርማና ሰንደቁን የያዘ በአሸባሪ ተባባሪነት እስር ቤት ተወረወረ።
የኦነግ አባላት ከኤርትራ ዛሬ በአዲግራት በኩል መቀሌ ...
ዛሬ ሕወሓት ከፌደራል የስልጣንና ኃይል ቁጥጥር ሲለቅ : ኦነግ አሸባሪነቱ ተነስቶ ከስደት አገር ቤት ገባ ። አሁን ለሕወሓት እንደሽግግሩ ወቅት ኦነግን የሚተካ አጋር አልተገኘም ÷ ኦነግ ደግሞ ያንኑ የሽግግር ዘመን አጀንዳ እንዳንጠለጠለ ሳያድግ ሳያረጅ ባለበት ተገኘ። እናም የወጋም የተወጋም ነገሩን ትተው ሕወሓታውያን ያባረሯቸውን ሰዎች በመቀሌ የአቀባበል ድግስ አድርገው ተቀበሉና ኦነግም ወደሚያውቀው የወለጋ ጫካ ተደበቀ።
ሕወሓትም ከወለጋ ጫካ አሳዶ እነ ለገሰ ወጊን ገድሎ እንዳላባረረ ዛሬ ኦነግ ወለጋን ብቻ ሳይሆን ኦሮሚያን እንዲቆጣጠር ደጋፊ ሆኖ ወጥቷል።
የወጋም የተወጋም ነገራቸውን በይደር ትተው መተባበራቸው ድል ቢመጣ ታሪክን መድገማቸው የማይቀር ቢሆንም ዋናው ጉዳይ ግን የፀረ-አማራና ፀረ-ምንሊክ ተረት ተረት ነው!
የኢትዮጵያ ባለጭንቁ አማራ ደግሞ የእለት እንጀራ ፍለጋ ሲንከራተት የሐምሳ አመት የጥላቻ ስብከት በትር እየወረደበት ነው። ለሚምልባት አገር ህልውና ሕይወቱን እየገበረም ከድህነት እየታገለ ነው።

Share and Enjoy !

0Shares
0
0Shares
0