1. በአሜሪካ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ4 ሚሊዮን ተሻገረ
  2. በብራዚል ከ67 ሺህ በላይ ሰዎች  በአንድ ቀን ብቻ  ቫይረሱ እንዳለባቸው ተረጋገጠ
  3. ትራምፕ በኮሮናቫይረስ ስጋት የሪፐብሊካን ፓርቲ ጉባኤን ሰረዙ
  4. የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዓለማችን ላይ መከሰቱ ከተሰማበት ጀምሮ ከ 15.9 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውና 642,827 ሰዎች ሞተዋል።
  5. 9,743,298 ሰዎች አገገመዋል።
  6. ደቡብ አፍሪካ 422 በላይ ሺህ የኮቪድ ተጠቂዎች አሉዋት

ኮሮና ወደ አስከፊ ደረጃ እያመራ መሆኑንን የሰሞኑ አሃዞች ያመላክታሉ። የመመርመር አቅም ውስን መሆኑ እንጂ አሃዙ አሁን ከሚባለው በላይ አስደንጋጭ እንደሚሆን በዘርፉ የተሰማሩ እየገለጹ ነው። ባለፉት 24 ሰዓታት ለ7 ሺህ 264 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 760 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በቲውተር ገጻቸው አስታውቀዋል።

ዶክተር ሊያ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ባለፉት የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉንም አመልክቷል። አጠቃላይ የሟቾች  ቁጥር 200 ደርሷል፡፡ በሃያ አራት ሰዓት 140 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል። በዚሁም ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 5 ሺህ 785 ደርሷል።

በተጨማሪም 68 ሰዎች በፅኑ ህክምና ላይ እንደሚገኙም ተገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ለ364 ሺህ 322 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 12 ሺህ 693 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ቫይረሱ ያለባቸውና ክትትል እየተደረገላቸው የሚገኙ ሰዎች አጠቃላይ ቁጥር 6706 እንደሆነ የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *