“ዕርቀ-ሰላም በሚሆንበት ጊዜ እንዲሳካ ከብት ማረድ ካስፈለገ ገዝተን እናርዳለን፤ አይ ከብት አይደለም ሰው ይታረድልን የምትሉ ከሆነ ይኸው የኔን ደም አፍስሱና ኦሮሞን አስታርቁልኝ”  ኦቦ ኃይሌ ገብሬ በአንድ ወቅት የኦሮሞ ድርጅቶች እንዲስማሙ ሲማጸኑ አልቅሰው የተናገሩት ቃል ነው።

ቀደም ባሉት ዓመታት ሶስት ቦታ ተከፍሎ በተናጠል ሲንቀሳቀስ የቆየው ኦነግ በህዝብ ትግል ወደ አዲስ አበባ ሲገባ ልዩነቶችን ያስወግዳል ተብሎ ተጠብቆ ነበር። በተለያዩ ጊዚያት ተሞክረው የከሸፉት የዳግም አንድነት ሽምግልናና ድርድሮች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተወግደው ኦነግ አንድ ትልቅ ድርጅት ሆኖ እንደሚወጣ እምነት ቢኖርም በትግባር ግን ሊሳካ አልቻለም።

አባገዳዎች፣ ህዝብና ደጋፊዎች በየመድረኩ ጫና ቢያደርጉም ሶስት ሆኖ አገር ቤት የገባው ኦነግ ወደ አንድ የሚያመጣውን ድርድር ማድረግ አልቻለም። በመጠኑ ተጀምረው የነበሩ ውይይቶችም ለውጥ ሳያመጡ ቀርተዋል።ለአንድ ህዝብ ቆመናል የሚሉ ወገኖች መስማማት ያልቻሉበት ዋና ምክንያት በመላው ኦሮሞ ዘንድ ቅሬታን የሚፈጥር ብቻ ሳይሆን የማይግባቡበትን ምክንያታቸውን አለማወቁ በራሱ እንቆቅልሽ ነው። ይህንን እንቆቅልሽ የሆነ አስተያየት በየመድረኩ መስማትም የተለመደ ነው።

የአቶ ዳውድ፣ የብ/ጄነራል ከማልና የአባ ቢያ ኦነግ ሶስት መልክ ይዞ አገር ቤት ከገባ በሁዋላ ከዜና ያላለፈው የኦሮሞ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረትም ቢሆን የተወሰኑትን ያገለለ ነበር። በጃዋር መሐመድ ጎትጓችነት ይፋ ሆነ የተባለው ህብረት ቆይቶ ሲሰማ በሚስጢር ኦዲፒን አክስሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ላይ ኩዴታ ለማካሄድ የተወጠነ መሆኑ ሃሳቡ ተግባራዊ ከመሆኑ ሰዓታት በፊት መክሰሙን ሚስጢር የሚያውቁ በውቅቱ የገለጹት ጉዳይ ነው።

Related stories   Egypt-Sudan alliance shifting in row with Ethiopia over Nile dam

በጤማ መንፍሰ ያልተገነባው አንድነት በዳዴ ሲቀር ኦፌኮ፣ ኦነግ ሸኔና ከማል ገልቹ ህብረት መፍጠራቸው ድጋሚ ተሰማ። የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ሃላፊ የነበሩት ከማል ገልቾ ይህንኑ ህብረት አፍታም ሳይቆዩ ሸሹትና መግለጫ ሰጡ። ጃዋርን ሳይቀር እመነቱን እንደጣለ ፊትለፊት በመውጣት ተናገሩ።

እየፈረሰ ሲገነባ የቆየው የኦሮሞ ድርጅቶች ጋብቻ በጃዋር ሚዲያዎችና የፖለቲካ ቅስቀሳ ላይ ተንጠልጥሎ እድገት ያሳየ ቢመስልም፣ ከማል ገልቹ እንዳሉት በድርጅት ደረጃ ነጥሮ እንዲወጣ ያልተደረገ፣ ዘመኑንን የሚመጥን አሳብ ያላነገበና ለቅስቀሳ ህዝብን በሚያሞቁ መፈክሮች የተቀኘ በመሆኑ አብዛኞች የመካከለኛው መደብ ነዋሪዎችና ” ዲቃላ” በሚባሉት ዘንድ አልተወደደም። እንደውም ቅሬታ በገሃድ ይቀርብ ጀመር። በሌላም በኩል የአካባቢያዊነት ስሜትም ጎለመሰ። ነፍጥ ያነሱት የሸኔ ሃይሎች ፍላጎት ምን እንደሆነ ግልጽ አለመሆኑ ቅሬታና ጉምጉምታውን አናረው።

ይህ ሁሉ ተዳምሮ ሳለ ኦነግና የኦሮሞን ትግል የሚያስተባብሩ የሚባሉት የኦፌኮ አመራሮች፣ አክቲቪስት የሚባሉትና ጃዋር ከትህነግ ጋር ጋብቻ መጀመራቸውን ይፋ አደረጉ። ተጋሩ፣ ዲጂታል ወያኔ፣ የህወሃት ካድሬዎችና አፍቃሪዎች ሚዲያቸው ሁሉ ፍቅር እሽሩሩ መሆኑ በርካቶችን አሳዘነ። በይፋ መቃወምም ተጀመረ። እነ በቀለ ገርባ ደም ከፍሎ ከትህነግ መንጋጋ ላወጣቸው ህዝብ ” እንኳን ልገረፍ ግልምጫም አልደረሰብኝም” ሲሉ መርዶውን አረዱት። በነካ አፋቸው ከአማራ ጋር በሚል የማይረሳ ዲስኩር አቀረቡ።

ከትህነግ ጋር የተፈጸመውን የማይታመን  ጋብቻ በተደጋጋሚ ካወገዙት መካከል አርቲስ ሃጫሉ አንዱ ነበር። ህይወቱም የተቀጠፈው በዚሁ አቋሙ ነው የሚሉ እንደሚሉት ሃጫሉ ይህንን ጉዳይ የኦሮሞን ደም ዳግም የመጠጣት ያህል ክህደት እንደሆነ በግልም ሆነ ባደባባይ ይናገር ነበር።

Related stories   ደመቀ መኮንን በፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሚመራ የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ጋር ተወያዩ

ከሃጫሉ ህልፈት በፊት ጀምሮ በኦነግ ሸኔ ውስጥ የጉባኤ ጉዳይና ጠብመንጃ ይዞ ጫካ ባለው ሃይል ሳቢያ ግልጽነት ባለመኖሩ አካባቢን መሰረት ያደረገ ልዩነት ይሰማ ነበር። አቶ ዳውድ ብቃት የላቸውም ከሚሉት ጀምሮ ኦነግ አዲስ ምርጫ ማካሄድ እንዳለበት የሚያምኑ በተለይም የመሃል አገር የሆኑት የምክር ቤት አባላት ውስጥ ውስጡን ቅሬታቸውን ሲያሰሙ እንደነበር በተባራሪ የሚሰማ ጉዳይ ነው።

የሃጫሉ ህልፈት ተዋኞች እነማን እንደሆኑ የሚያመላክቱ ጉዳዮች ይፋ ከሆኑ በሁዋላ ይህ አለመግባባት መስፋቱን ለድርጅቱ ቅርብ የሆኑና ውጭ ሆነው ድጋፍ የሚያደርጉ እየገለጹ ባለበት ወቅት ነው የአቶ ዳውድ ምክትል አቶ አራርሶ ቢቂላ ” ጉባኤ መጥራት መብቴ ነው። ህጉ ይፈቅድልኛል” ማለታቸው የተሰማው።

ዛሬ ለንባብ የበቃው የጀርመን ድምጽ ራዲዮ የግንባሩን አመራር ብቻ በማነጋገር ስብሰባው ህገወጥ መሆኑንን አስነብቧል። በዘገባው ወደ ጽህፈት ቤት ውስጥ መግባት እንዳልቻሉ የገለጹት የግንባሩ አባል ጉባኤው በተሳታፊ ቁጥርም ህጉን እንደማያሟላ ብዛት ጠቅሰው የተናገሩትን እንዳለ አስፍሯል። መግባት ካልቻሉ ምን ያህል ተሳታፊዎች እንዳሉ እነዴት ማወቅ እንደቻሉ አልጠየቃቸውም።

Read also  የኦነግ ሸኔ ምክትል ሊቀመንበር አስቸኳይ ስብሰባ ጠሩ – የዳውድ ኢብሳ የመሪነት እጣፈንታ ሊያከትም?

ምንም ይሁን ምን ምክትል ሊቀመንበሩ የመሩት ስብሰባ እየተካሄደ መሆኑ ተረጋግጧል። የጀርመን ድምጽ ያነጋገራቸው የግንባሩ የፋይናንስ ዘርፍ ሃላፊ አቶ በቴ ዑርጌሳ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ አጠቃላይ ጉባዔውን ሊያካሂድ  ከአራት እስከ አምስት ወራት ቀርተውት ነበር ብለዋል።  አሁን በጥቂት ሰዎች አማካይነት የሚካሔደው ስብሰባ አላማው እና ግቡ እንደማይታወቅም ገልጸዋል። የግንባሩን ቀጣይ አቅጣጫ ለመናገር ግን ከስብሰባው በኋላ የሚወሰኑ ውሳኔዎች ይጠበቃሉ ሲሉም  ህገወጥ ካሉት ስብሰባ ውሳኔ እንደሚጠብቁ አመልክተዋል።

Related stories   አስከሬን እንዲለቀም ታዘዘ - ትህነግ የአጽም ፖለትካ ድራማ ይፋ ሆነ

መንግስት ለድህንነታቸው ሲል አቶ ዳውድን እየጠበቃቸው መሆኑንን እንደገለጸላቸው የጽህፈት ቢት ሃላፊው ለቢቢሲ ቀደም ሲል አስታውቀዋል። የአንድ ወገን ሃሳብ ብቻ የያዘው የጀርመን ራዲዮ ዘገባ እንዳለው የመንግስት ወታደሮች የድርጅቱን ቢሮ የጥበቃ ሰራተኞችን በማስገደድ አስከፍተው አሁን ስብሰባ ላይ ላሉት ወገኖች አመቻችተዋል። ይህ በሌላ ወገን ማረጋገጫ ያልተሰጠበት የጀርመን የአማርኛው ድምጽ ድምጽ ራዲዪ ሪፖርት  የመንግስት ወታደሮች ሰሞኑን ሁሉ የግንባሩን ጽህፈት ቤት ሲያንዣብቡት መቆየታቸውን በክስ ያቀርባል። ዜናውንም ለማመጣጠን ስለመሞከሩ እንኳን አልገለጸም።

Read also  አቶ ዳውድ ኢብሳ በመኖሪያ ቤታቸው ጥበቃ ውስጥ ናቸው ፤ ፖሊስ ለደህንነታቸው ሲባል ነው ይላል!!

አቶ በቴ እንዳሉት ይኸው ቡድን የግንባሩን ሊቀመንበር ጨምሮ ዋነኞቹ የግንባሩ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በሌሉበት የሚያደርገው ውይይት እና የሚወስናቸው ውሳኔዎች በእስር ላይ የሚገኙትን የግንባሩን አመራሮች የከእስር የሚያስለቅቅ እስካልሆነ እና አመራር ለመቀየር የሚደረግ ጥረት ከሆነ ተቀባይነት የለውም።

ይህ በንዲህ እንዳለ አቶ አራርሶ የመሩት ስብሰባ በነገው እለት መግለጫ ያወጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ለዛጎል ቅርብ የሆኑ አስታውቀዋል።

Image credit BBC

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *