ዘገባው በጥርጣሬ የተሞላና እርግጠኛውን ጉዳይ መናገር አልቻለም። በደፈናው “በአቶ ዳውድ ኢብሳ ቤት አካባቢ እየተከናወነ ያለው ነገር ምንድን ነው?” ሲል ነው ጥያቄ የሚያቀርብ እርዕስ የመረጠው። ቢቢሲ በጥያቄ መልክ ይህንን ቢልም በጉለሌ የድርጅቱ ጽህፈት ቤት ስለሚከናወነው የኦነግ ሸኔ ስራ አስፈሳሚዎች ስብሰባ ለዜናው የጠቀሳቸውን የቢሮ ሃላፊ አልጠየቃቸውም።

ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ አራርሶ  አስቸኳይ ስብሰባ መጥራታቸውን ተከትሎ የአቶ ዳውድ ቤት  በፌዴሬል ፖሊስ መከበቡን የፓርቲው ቢሮ ኃላፊ አቶ ገዳ ኦልጅራ ናቸው ለቢቢሲ የተናገሩት። አቶ ገዳ እንደሚሉት ከሆነ በአቶ ዳውድ ኢብሳ ቤት አካባቢ የሚገኘው የጸጥታ ኃይል የሊቀመንበሩን ደኅንነት ለመጠበቅ መሰማራቱን ከፖሊስ መስማታቸውንም ነው ያስረዱት። በሌላ ንግግር ቤታቸው መከበቡን ነው ለቢቢሲ ያረጋገጡት። ይሁን እንደዘገባው  መከበባቸውን ቃል በቃል ሃላፊው አልተናገሩም። ግን ከመኖሪያ ቤታቸው ከወጡ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ይውላሉ የሚል ስጋት እንዳላቸው ተናግረዋል። ፖሊስ አቶ ዳውድን መያዝ ከፈለገ ቢታቸው ውስጥ መቀመጣቸው ሊያግደው የቻለበትን ምክንያት ሃላፊው አልተጠየቁም።

ይልቁኑም አቶ ዳውድ  ከሦስት ቀናት በፊት በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለው ከአንድ ቀን በኋላ መፈታታቸውን አቶ ገዳ አስረድተዋል። “ዋና ሊቀመንበራችን በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ነው ያሉት። እንደልባቸው ተንቀሳቅሰው የዕለተ ዕለት ሥራቸውን ማከናወን አልቻሉም” ሲሉ አቶ ዳውድ ከቤታቸው መውጣት እንዳልቻሉ ቢቢሲ አመልክቷል። አቶ ዳውድ ብቻ ሳይሆኑ በቤታቸው ውስጥ ያሉ የቤተሰባቸው አባላትም ከመኖሪያ ግቢው መውጣትናም ሆነ ከውጪ መግባት ተከልክለዋል። የአቶ ዳውድ ኢብሳ ስልክ ከሦስት ቀናት በፊት ጀምሮ እየሠራ እንዳልሆነ በዘገባው ተጠቁሟል።

የአቶ ዳውድ ኢብሳ ቤት ለምን እንደተከበበ የሚያውቁት ነገር አለ ወይ ተብለው የተጠየቁት አቶ ገዳ፤ ፖሊስ ይህን ያደረገው ለአቶ ዳውድ ደኅንነት ሲባል እንደሆነ ተነግሮኛል ይላሉ።

ይህ በንዲህ እንዳለ የኦነግ ሸኔ የውጪ ድጋፍ ሰጪዎች ሁለት አቋም እንደያዙ እየተሰማ ነው።

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *