የፌደራል መንግስት፣ የብልጽግና ፓርቲና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኃላፊዎች ከትግራይ ተወላጅ ባለሃብቶች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂደዋል።

በውይይቱ ላይም የፌደራል መንግስት ጦርነት ሊከፍትብን ነው፣ መንግስት የትግራይ ክልልንና ተወላጆችን እያገለለ ነው፣ ወዘተ የሚሉ የፕሮፖጋንዳ ትርክቶች ለፖለቲካ ፍጆታ ከመዋላቸው ባለፈ መሬት ላይ የሌሉ መሆናቸውን በመተማመን ላይ መደረሱን የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ያወጣው መረጃ ያመልታል። ከዚህ በተጨማሪም ማንኛውም በህጋዊ መንገድ ልማት ላይ፣ የሀገር እድገት ላይ መዋእለ ንዋያቸውን የሚያፈሱ የትግራይ ባለሀብቶች መንግስት ከጎናቸው እንደሚቆምም ቃል እንደተገባላቸውም ተገልጿል።

ይህን ጉዳይ እየተከታተለ የሚያስፈፅም ተወካዮች መሰየማቸውም ነው የተገለፀው። “አገር ሊፈርስ ነው ጓዝህን ጠቅልለህ ወደ ክልልህ ግባ” የሚለውን ውዥንብር ፕሮፖጋንዳ ሳይታለሉ ራሳቸውን አረጋግተው ሊሰሩ እንደሚገባም ተወያይቷል።

“ይህ በንዲህ እንዳለ፣ ኢትዮጵያ የሁሉም አገር ናት፤ ሁላችንም ሰርተን የምንለወጥባት ሀገር እንጂ የምንሸማቐቅባት ሀገር አለመሆንዋንም ከግንዛቤ ሊገባ ይገባል” ተብሏል በውይይት መድረኩ ላይ። ከትግራይ ተወላጅ ባለሃብቶች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አስመልክተው ከፌደራል መንግስት ተወካዮች ፣ ከብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሃላፊዎች ጋር ውይይት አካሄዱ፡፡ ሙሉ ዘገባው ከብልጽግና ፓርቲ የፌስቡክ ገጽ እንዳለ የተወሰደ ከታች ያለውን ይመልከቱ።

Related stories   የትህነግ "ውሮ ወሸባዬ" - የመንግስት ሩጫ - የሃላኑ የኢትዮጵያን ቋንጃ የመበጠስ የእባብ አካሄድና ባንዳዎች!
ሓምሌ 19 ቀን፣ 2012ዓ.ም ከትግራይ ተወላጅ ባለሃብቶች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተካሄደው ውይይት፤ የፌደራል መንግስት ጦርነት ሊከፍትብን ነው፣ መንግስት የትግራይ ክልልን እያገለለ ነው፣ የትግራይ ተወላጆችን እያገለለ ነው : የመንግስት ሚድያዎች ሳይቀር ባለሃብቶች ሰርተው ያፈሩትን ሃብት በዘራቸው አገኙት እያሉ ዘመቻ እያካሄዱ ነው ፤ ወዘተ የሚሉ ጥያቄዎች በማንሳት ማስተካከያ እንዲደረግባቸው ጥያቄ አንስተዋል::
የመንግስትና የፓርቲ ተወካዮችም ከሚድያ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች የሚታዩ ክፍተቶች እንዲታረሙ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል:: በመንግስት ስር ሆነው ብሔርን መሰረት አድርገው አገልግሎት የሚሰጡ ሰራተኞች ካሉም በጋራ በመሆን ማስተካከያ ስራዎች ይሰራል ያሉ ሲሆን መንግስት ጦርነት ሊፈጥርብን ነው የትግራይ ተወላጆች እያገለለ ነው የሚሉ የፕሮፖጋንዳ ትርክቶች ግን ለፖለቲካ ፍጆታ ከመዋላቸው ባለፈ መሬት ላይ የሌሉ መሆናቸውን መተማመን ላይ ተደርሷል፡፡
በፌደራል መንግስት በኩል በማንኛውም አግባብ የጦርነት ሃሳብም ፍላጎትም እንደሌለው የተገለፀላቸው ሲሆን ከምርጫ ጉዳይ ጋርም ተያይዞ ቢሆን በምንም መንገድ ወደ ጦርነት የሚያስገባ ነገር አለመኖሩን ተገልፆላቸዋል::
ከዚህ በተጨማሪም ማንኛውም በህጋዊ መንገድ ልማት ላይ፣ የሀገር እድገት ላይ መዋእለንዋያቸውን የሚያፈሱ የትግራይ ባለሀብቶች መንግስት ከጎናቸው እንደሚቆምም ቃል የተገባላቸው ሲሆን፤ ይህን ጉዳይ እየተከታተለ የሚያስፈፅም ተወካዮችም ሰይመዋል፡፡ አገር ሊፈርስ ነው ጓዝህን ጠቅልለህ ወደ ክልልህ ግባ የሚለውን ውዥንብር ፕሮፖጋንዳ ሳይታለሉ ራሳቸውን አረጋግተው ሊሰሩ እንደሚገባም ተወያይቷል፡፡ ይህ በንዲህ እንዳለ፣ ኢትዮጵያ የሁላችንም አገር ናት፤ ሁላችንም ሰርተን የምንለወጥባት ሀገር እንጂ የምንሸማቐቅባት ሀገር አለመሆንዋንም ከግንዛቤ ሊገባ ይገባል ተብሏል፡፡
ተጋሩ ሰብ ሃፍቲ ምስ ሰበ ስልጣን ፌደራል መንግስቲ፣ ፈፀምቲ ስራሕን ምምሕዳር ከተማ ኣዲስ ኣበባን ኣብ ህልዊ ኩነታት ኣመልኪቶም ተዛትዮም፡፡
ሓምለ 19፣ 2012 ዓ.ም ምስ ተጋ ሰብ ሃፍቲ ዝተሳለጠ ዘተ፣ መንግስቲ ፌደራል ከጥቀዐካ እዩ፣ ትግራይን ህዝባን ይግለሉ ኣለዉ ወዘተ ዝብሉ ፕሮፖጋንዳታት ኣብ መሬት ዘየለዉ ካብ ሓቂ ዝረሓቑ ከምዝኾኑ ኣብ ምርድዳእ ተበፂሑ እዩ፡፡ ካብዚ ብተወሳኺ ድማ ዝኾነ ብሕጋዊ መንገዲ ኣብ ልምዓት፣ ኣብ ዕብየት ሀገርና መዋእለ ንዋዮም ዘፍስሱ ሰብ ሃፍቲ ተጋሩ መንግስቲ ኣብ ጎኖም ደው ከምዝብል ቃል ዝተኣተወሎም እንትኾን፤ ነዚ ዝከታተል ተወካሊ እውን ሰይሞም እዮም፡፡ ብተወሳኺ፣ “ዓዲ ክትፈርስ እያ ጉዞኻ ጠቕሊልካ ዓድኻ እቶ” ብዝብል ካብ ሓቂ ዝረሓቐ ፕሮፖጋንዳ ከይተታለሉ ካብ ስግኣት ነፃ ኾይኖም ክሰርሑ ክምዝግባእ እውን ተሓቢሩ እዩ፡፡ እዚ ክምዚ እንዳሃለወ፣ “ኢትዮጵያ ሀገር ኩላትና እያ፤ ሰሪሕና፣ ፅዒርና እንልወጠላ ሀገር እምበር ርእስና እንደፍአላ ሀገር ከምዘይኮነት ክንርዳእ ክምዝግባእ እውን ተሓቢሩ እዩ፡፡

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *