አሃዞች የተፈራው በደጅ መሆኑንን እያመላከቱ ነው። ዛሬ ተጨማሪ 720 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸውና  የ14 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተጠቆመ።ባለፉት 24 ሰዓት 9 ሺህ 527 የላብራቶሪ ምርመራ ተደሮላቸው ነው 720 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የተረጋገጠው። ሚኒስትሩ አሁንም እንደወትሮው ጥንቃቄ ሲል እየወተወተ ነው።
የዛሬውን ጨምሮ ቫረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 13 ሺህ 968 ደርሷል።የ14 ሰዎች ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 223 እንደደረሰ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በዕለታዊ ሪፖርቱ አስታውቋል።
በተመሳሳይ 250 ሰዎች  አገግመዋል። በዚሁ ፣መሰረት ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 6 ሺህ 216 መድረሱም ተገልጿል። ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን 382 ሺህ 339 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 13 ሺህ 968 ደርሷል።
በዛሬው መረጃ መሰረት 65 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።አጠቃላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 7 ሺህ 527 ነው።
በኢትዮጵያ 6 ሺህ 216 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገገሙ፤ የ223 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 2 ሰዎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው እንደተመለሱ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እለታዊ መረጃ ያስረዳል። ይህ በንዲህ እያለ በዓለም በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎሽ ቁጥር ይህ ሲታተም  16,117,308 መድረሱን ዓለም ዓቀፍ ዳታዎች ያሳያሉ። 9,289,876 የገገሙ ሲሆን፣ ህይወታቸው ያለፉቱ ደግሞ 645,482 ደርሰዋል።
አሜሪካ አሁን ክፉኛ የተጠቃች ሲሆን 4286 714 ዜጎቿ በቫይረሱ ተይዘዋል።  149,602 ሞተዋል።  2,072,532  አገግመዋል። በዛሬው ቀን ብቻ 204 ስዎች ህይወታቸው አልፏል።

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *