በጎንደር ከተማም ከመንግስት የጸጥታ መዋቅር ውጭ በብርጌድና በሻለቃ በማደራጀት ሰው በማገትና ሃብትና ንብረት ዘረፋ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ቡድኖችን ስርአት ለማስያዝ መሠራቱን አብራርተዋል። በህገ ወጥ አደረጃጀት ተደራጅተው ከነበሩት ውስጥ 215 በምኅረት፣ 405 ሰላማዊ በሆነ መንገድ እጅ እንዲሰጡ፣ ፈቃደኛ ያልነበሩ 686 ሰዎች ደግሞ በኃይል እጅ እንዲሰጡ በማድረግ ሕግና ስርአት የማስከበር ሥራ ተሠርቷል
አማራ ክልልን መምራት ሲጀመሩ የተረከቡት ወንበር የሚፋጅ ነበር። ሲጀመር በነቀፌታና በከፍተኛ ትችት አቀባበል የተደረገላቸው አቶ ተመስገን ግን ዛሬን የሚገልጹት ” የዛሬ ዓመት ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ ነበርን” ሲሉ ነው።
ክልሉን ለማተራመስ የተገዙና ሳይገባቸው የሚነዱ፣ እንዲሁም ጽንፈኛ አካሄድን መርጦ የነበረው አብን በጅምላ ያካሄዱት ቅስቀሳ ህዝቡን ግራ አጋብቶት እንደነበር የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ የሚያስረዱ በተደጋጋሚ ሲናገሩት የነበረው ሃቅ ነው።
ድንቅ አመራሮቹን ያጣው የአማራ ክልል ከሃዘን ማጥ ባለወጣበት፣ ይህንኑ ሃዘኑንን ለፖለቲካ ገበያ በሚጠቀሙ ተኩላዎችና ራሳቸውን በክልሉ በሚከበረው የፋኖ ስም የሰየሙ ነውጠኞች፣ በማህበራዊ ገጽ ድጋፍ ሰጪነት በሚሰራጨው የክፋት ዘመቻ ክልሉ ከቀውስ ወደ ቀውስ እየተሸጋገረ ባለበት ወቅት ወደ ሃላፊነት የመጡት አቶ ተመስገን ዛሬ ነገ ሳይሉ ወደ ስራ መግባታቸውን ባልደረቦቻቸው ይመሰክራሉ።
መረር ያለ ንግግር በማሰማት የሚታወቁት ተመስገን ዛሬ እንዳስታወቁት ያ የቀውስ ጊዜ ላይመለስ ሄዷል። ፋኖም ቤቱ ተመልሶ ገብቶ በመደጋገፍ ይሰራል። የፋኖ መሪም ባለማወቅ የተደረገው ሁሉ እንደማይደገም አረጋግጠዋል። እየዘገዩ እውነታው የገባቸው አብኖችም የበሰለ አካሄድ በመከተል ለክልሉ መረጋጋት ድግፍ ማድረጋቸው በሶሰተኛ ወገኖች ምስጋና ሲቀርብበት ተሰምቷል።
ባለፈው በጀት ዓመት ሕግን በማስከበር በኩል አበረታች ተግባራት መከናወናቸውን ጠቅሰው ለክልሉ ሸንጎ ሪፖርት ያቀረቡት ተመስገን ያረጋገጡት እውነት ይህንኑ ነው። የክልሉ መገናኛ ከስፍራው የሚከተለውን ዘግቧል።
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ የክልሉን 2012 በጀት ዓመት ሪፖርት ለምክር ቤት አባላት ባቀረቡበት ጊዜ እንደገለጹት በበጀት ዓመቱ ለክልሉ ሰላምና ጸጥታ ትኩረት ተሰጥቶ ተሠርቷል።
በክልሉ ሰላም እንዳይኖር በማኅበራዊ ሚዲያ ሲለቀቁ የነበሩ የሀሰት ትርክቶች አሉታዊ ሚና እንደነበራቸውም ጠቁመዋል። በጎንደር ከተማም ከመንግስት የጸጥታ መዋቅር ውጭ በብርጌድና በሻለቃ በማደራጀት ሰው በማገትና ሃብትና ንብረት ዘረፋ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ቡድኖችን ስርአት ለማስያዝ መሠራቱን አብራርተዋል። በህገ ወጥ አደረጃጀት ተደራጅተው ከነበሩት ውስጥ 215 በምኅረት፣ 405 ሰላማዊ በሆነ መንገድ እጅ እንዲሰጡ፣ ፈቃደኛ ያልነበሩ 686 ሰዎች ደግሞ በኃይል እጅ እንዲሰጡ በማድረግ ሕግና ስርአት የማስከበር ሥራ ተሠርቷል ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ።
በአዋሳኝ ክልሎች የአመራር ለአመራርና የሕዝብ ለሕዝብ ውይይት ማካሄድ ስለመቻሉም ጠቁመዋል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎችን ወደ ቀያቸው መመለስ እንደተቻለም አቶ ተመሥገን አሳውቀዋል። ከተፈናቀሉት የኅብረተሰብ ክፍሎች ጀርባ የተጀራጀና ጸረ ለውጥ ኃይል ስለመኖሩም አንስተዋል።
ትህነግ በጸብ አጫሪነት ባህሪው እንደገፋበትና እንቅስቃሴውን ሁሉም ሊገነዘበው እንደሚያሻም ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ተናግረዋል።
በክልሉ የሕግ የበላይነት ተረጋግጦ ሰላም እንዲሰፍን ላስቻሉ በየደረጃው ላሉ የክልሉ አመራሮችም ምስጋና አቅርበዋል።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *