“Our true nationality is mankind.”H.G.

ፖሊስ በጃዋር ጠባቂዎች ላይ ተጨማሪ የወንጀል ግኝት አለኝ አለ

NtJDO

ፖሊስ ሲያከናውን የቆየውን ምርመራ ሪፖርት ሲያደረግ ተጨማሪወንጀልአስታወቀ። ተጠርጣሪዎቹ  ማግኘቱን አስታወቀ። ተጠርጣሪዎችህ የጃዋር አንጋቾች በሚሰጣቸው ትዕዛዝ ከሰኔ 23 እስከ 24 ቀን 2012 ዓ.ም ውጪ ቀደም ባሉት ጊዜያት የተለያዩ ወንጀሎችን ለመፈጸማቸው የወንጀል ግኘት እንዳለው ነው ያብራራው። ከስር የፋና የችሎት ዘገባ እንዳለ አትመነዋል።
በአቶ ሃምዛ ቦረና ወይም ሃምዛ አዳነ መዝገብ የተካተቱ 9 ተጠርጣሪዎች ዛሬ ከሰአት ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
ተጠርጣሪዎቹ 1ኛ ሃምዛ ቦረና ወይም ሃምዛ አዳነ፣ያለም ወርቅ አሰፋ፣ ታምራት ሁሴን ፣ ሰበቃ ቃርቴ፣ ጌቱ ተረፈን ጨምሮ ዘጠኝ ተጠርጣሪዎች ሲሆን ስምንቱ የአቶ ጁሃር ዋና ጠባቂ ዎች ወይም አጃቢዎች ናቸው።
በፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ ችሎት ለሶስተኛ ጊዜ በቀረቡ በእነዚህ ተጠርጣሪዎች ላይ ÷ መርማሪ ፖሊስ ከዚህ በፊት በተሰጠው 11 ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ የሰራውን የምርመራ ስራ አብራርቷል።
በዚህም ምርመራ በተጠርጣሪዎች ላይ የተያዘ መሳሪያ ምርመራ ማደረጉን፣ ተጨማሪ 10 የተከሳሽ 20 ደግሞ የምስክሮችን ቃል መቀበሉን መርማሪ ፖሊስ ገልጿል ።
በዚህም በአንደኛ ተጠርጣሪ ሃምዛ አዳነ ወይም ሃምዛ ቦረና ላይ በተለያዩ መገናኛ ሚዲያዎች ብሄርን ከብሄር እና ከሃይማኖት ግጭት እንዲፈጠር ያደረጉትን ቅስቀሳ የሚያመላክት በቪዲዮ ምስል የተደገፈ ማስረጃ እንዳለው ለችሎቱ ገልጿል።
በተጨማሪም 1ኛ ተጠርጣሪ በኦሮሚያ በተለያዩ ቦታዎች የብሄርና የሃይማኖት ግጭት መቀስቀሳቸውን የሚያስረዳ ምስክር ማግኘቱን አስረድቷል።
ከ3ኛ እስከ 8ኛ ያሉ ተጠርጣሪዎች በአዲስ አባባ ብቻ 14 ሰዎች እንዲሞቱ ምክንያት መሆናቸውን በምስክር ተረጋግጧል ያለው መርማሪ ፖሊስ ÷በአጠቃላይ ከ350 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙን ማስረጃ መሰብሰቡንም ነው ገልጿል።
ከዚያም ባለፈ በተጠርጣሪዎች በተፈጸመ ወንጀል በቡራዩ የ4 ሰዎች ህይወት ማለፉን እና ሌሎች አራት ሰዎች ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ማስረጃ መሰብሰቡን ገልጾ÷ በዚህም ከባድ ጉዳት የደረሰባቸውን የህከምና ማስረጃ ህይወታቸው ያለፉትን ደግሞ የአስከሬን ምርመራ ውጤት የመቀበል ስራ እንደሚቀረው መርማሪ ፖሊስ አብራርቷል።
ተጠርጣሪዎቹ በሚሰጣቸው ትዕዛዝ ከሰኔ 23 እና ከ24 ቀን 2012 ዓ.ም ውጪ በተለያዩ ጊዜያት በፈጸሙት ወንጀል ሌላ ግኝት አግኝተናል ያለ ሲሆን÷ ሌሎች በርካታ የሰውና የሰነድ ማስረጃ እስክናሰባሰብ ተጨማሪ 14 ቀን ይፈቀድልን ሲል አመልክቷል።
የተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸው÷ እየተከናወነ ያለው ምርመራ ተገቢነት የሌለው ነው የሚቀርበው ምክንያት ተጨማሪ ጊዜ የሚያሰጥ አይደለም፣በእጃቸው ተገኘ የተባለው መሳሪያ በየጊዜው የቁጥር ስህተት እየቀረበበት ነው ፖሊስ ግልጽ አይደለም የሚሉ በርካታ መቃወሚያ አንስተዋል።
አራት ተጠርጣሪዎች በአካለም ሆነ በስልክ ከቤተሰብ ጋር የመገናኘት ፍቃድን ማግኘት እንዳለቻሉ በድጋሚ አቤቱታ አቀርበዋል።
1ኛ ተጠርጣሪ አቶ ሃምዛ በበኩላቸው÷ እኔ አክቲቪስትና ጋዜጠኛ ሆኔ በውጭ ሃገር ስኖር የነበና ለውጥ መጣ መባሉን ሰምቼ ነው ወደሃገር የመጣሁ ሲሆን÷ በተለያዩ መገኛና ብዙሃን ህገ መንግስት መብቴን ተጠቅሜ የራሴን ያመንኩበትን ነው የገለጽኩት ሲሉ ለችሎቱ ተናግረዋል።
መርማሪ ፖሊስም ምርመራው የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብታቸውን ከግምት ወስጥ ያስገባ መሆኑን በመግለጽ÷ ማንንም አስሮ ለማቆየት ሳይሆን አጠቃላይ የተፈጸመ ወንጀል ላይ የሚያስፈልጉ ማስረጃዎችን ለመሰብሰብና ለመመርመር መሆኑን ምላሽ ሰቷል።
ከዚያም ባለፈ ፍርድ ቤቱም የወንጀሉን ውስብስብነትና ስፋት ከግምት አስገብቶ የጠየቅሁትን ተጨማሪ ጊዜ ይፈቀድልኝ ሲል ጠይቋል።
የሁለቱን ክርክር ያዳመጠው ፍርድ ቤትም ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ ከቤተሰብ ጋር እንዲገናኙ በማድረግ ተከታትሎ ትዛዝ መፈጸሙን እንዲያቀርብ በተጨማሪም 1ኛ ተጠርጣሪ ህጋዊ ውክልና የሚሰጡበትን ሂደት እንዲያመቻች ትዛዝ ሰቷል።
ምርመራውን አጠናቆ እንዲቀርብ ከተጠየቀው 14 ቀን ውስጥ 8 ቀን በመፍቀድ ለሃምሌ 29 ቀን 2012 ዓ.ም ውጤቱን ለመጠባበቅ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል።
በታሪክ አዱኛ

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   በሃሰተኛ ሰነድ ሾፌር ሆኖ የጫነውን ከ6 ሚሊዮን በር በላይ የምያወጣ ቡና የዘረፈው ዕምነት አጉዳይ ተፈረደበት
0Shares
0