በየዓመቱ 2 ሚሊዮን ሰዎች የሚሳተፉበት የሐጅ ሥነ ሥርዓት ዘንድሮ በ10ሺ ሰዎች ብቻ እንደሚፈፀም ሳዑዲአረቢያ አስታወቀች፡፡ ሳኡዲ አረቢያ መንፈሳዊ ተጓዦች ወደ አገሯ እንዳይገቡ አግዳለች፡፡ የሐጅ ቪዛም ዘንድሮ አላተመችም፡፡
ዛሬ በሚጀመረው ሥነ ሥርዓት የሚሳተፉት የሌላ አገር ዜጎች በሳኡዲ የመኖርያ ፈቃድ ያላቸው ብቻ ናቸው ተብሏል፡፡ በግምት ከ10ሺ የማይበልጡ ሰዎች ብቻ ሐጅ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
መኖርያ ፈቃድ ኖሯቸው በሳኡዲ የሚገኙ የሌላ አገር ዜጎችም ቢሆኑ ወደ ቅድስት አገር መካ ሲገቡ ሙቀታቸው መለካት ይኖርባቸዋል፡፡ የኮቪድ-19 ቫይረስ ምርመራም ማድረግ ይገደዳሉ፡፡
ሐጅ ፈጻሚዎቹ ከሥነ ሥርዓቱ በፊትም ሆነ ሥርዓቱን ከፈጸሙ በኋላ ራሳቸውን ለተወሰነ ጊዜ ማግለልም ይጠበቅባቸዋል፡፡
በሳኡዲ የሐጅ ጉዳዮች ሚኒስትር መሐመድ ሳለህ ቢንተን ለአል አረቢያ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃለ ምልልስ ሐጅ አድራጊዎች ወደ መካ ከመግባታቸው በፊት በቤታቸው ራሳቸውን ለአራት ቀናት ገለል አድርገው መቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚያም መካ ከተማ ከገቡ በኋላ በሆቴላቸው ለሌላ አራት ቀናት ተገልሎ መቆየት ግድ ይላቸዋል፡፡
ሳኡዲ አረቢያ በቫይረሱ የተያዙባት ሰዎች ቁጥር 270,000 ሲሆን 3,000 ሰዎች ሞተውባታል፡፡
በኢስላም እምነት ከአምስቱ የሃይማኖቱ መሠረቶች አንዱ አቅም ያለው ሰው በሕይወት ዘመኑ ቢያንስ አንድ ጊዜ የሐጅ ሥነ ሥርዓት እንዲያደርግ ይጠበቅበታል፡፡
ዓመታዊው የሐጂ ሥነ ሥርዓት ዛሬ ረቡዕ ነው የሚጀምረው፡፡ ወትሮው ከመላው ዓለም ሁለት ሚሊዮን ሰዎች በዚህ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት የሚሳተፉ የነበረ ሲሆን ዘንድሮ ግን በኮሮና ምክንያት ቁጥሩ ተገድቧል፡፡
ምንጭ፤ ቢቢሲ – FBC

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *