ፖሊስ አቶ በቀለ ገርባን በነብስ ግድያና በመንግስት ተቋማትና በግለሰብ ንብረቶች ላይ በሚሊዮን ብሮች ለሚገመት ውድመት ተጠያቂ መሆናቸውን የሚይረጋግጥ የሰነድ ማስረጃና ምስክሮች ማሰባሰቡን አስታውቀ። ቦታና ተቋማትን ጠቅሶ የተረጠረበትንና ያሰባሰበውን መረጃ ሲስረዳ እንዳለው ሰባት ሽጉጦችን ማግኘቱን አስታውቋል።

ሰኞ እለት በፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ልደታ ችሎት የአራዳ ምድብ ተረኛ ወንጀል ችሎት በስዋለው ችሎት ፖሊስ ባቀረበው ሪፖርት ግጭት ለመቀሰቀስ ተጠቅመውባቸዋል ያለውን ሰባት ሽጉጦች ማግኘቱን አመክቷል።

ከድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያና እሱን ተከትሎ ከተፈጠረው ሁከት ጋር በተያያዘ በእስር ላይ የሚገኙት አቶ በቀለ ገርባ ክሱ እሳቸውን የሚመለከት እንዳልሆነ አስረድተዋል።

የኦሮሞ ፌደራሊሰት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር  አቶ በቀለ ገርባ በህግ ጥላ ስር ከዋሉ በሁዋላ ለሶስተኛ ጊዜ  ፍርድ ቤት ሲቀርቡ፣ የድምፃዊ ሃጫሉን አስከሬን ከቡራዩ እንዲመለስ በማድረግ ፣ የኦሮሚያ የብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ይዘው ሲገቡ በጥበቃ ላይ የነበረ አንድ የኦሮሚያ ፖሊስ አባልን ተኩሰው በመገደሉና ሦስት ሌሎች ፖሊሶች  እንዲቆስሉ ማድረጋቸውን አንዲሁም አቶ በቀለ በዕለቱ ሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም. ወደ ሻሸመኔ፣ አምቦና የተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ስልክ በመደወል አመፅና ሁከቱ እንዲባባስ ባስተላለፉት ትዕዛዝ ከፍተኛ የንብረት ውድመት መድረሱንና ከ50 በላይ የሰው ሕይወት መጥፋቱን ፖሊስ አስታውቋል። የስልክ የድምጽ ማስረጃም እንዳለው አመክቷል።

Related stories   በቡድን ተደራጅተው የውንብድና ወንጀል የፈጸሙት ተከሳሾች ከ18 እስከ 20 ዓመት በሚደርስ እስራት ተቀጡ፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን ባለፉት የምርመራ ጊዜ የተሰሩ ስራዎችን ለፍርድ ቤቱ ያስረዳ ሲሆን የጦር መሣሪያዎችን የፎረንሲክ ምርመራ ውጤትና የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች ምርመራ ውጤትን ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትና ከመረጃና መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ መቀበል እንደሚቀረው፣ እንዲሁም ለተለያዩ ተቋማት በሁከት የወደመ የንብረትን መጠን ለማወቅ የተጻፈ ደብዳቤ ምላሽ ማግኘት እና የቀሪ ምስክሮችን ቃል መቀበል እንደሚቀረው ተጨማሪ የ14 ቀን የምርመራ ግዜ ይሰጠኝ ሲል ጠይቋል፡፡

Related stories   “በተለምዶ ‘ሸኔ’ የሚባለው ራሱን ‘የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት’ ብሎ የሚጠራው ቡድን ነው”

አቶ በቀለ ገርባ በበኩላቸው “ወንጀለኛ የተባልኩት በፖለቲካዊ አመለካከቴ ነው፣ ወንጀል የሚሰራ ሰው ልጆቹን ይዞ አይሄድም ፣ እኔ ሃጫሉን በግል ስለማውቀው እና ስለማከብረው ለቅሶ ለመድረስ ነው የሄድኩት፣ ወንጀል ፈፅመሀል የተባልኩት አውቀው በምርጫ እንዳልሳተፍ ለማድረግ ነው ” ሲሉ ለችሎት ተናግረዋል፡፡ አክለውም የግል መኪናቸው እስካሁን በፖሊስ እንደተያዘና እንዳልተለቀቀላቸው ተናግረዋል፡፡

የተጠርጣሪው ጠበቆች በበኩላቸው ፖሊስ ከመጀመሪያ ጀምሮ የምርመራ ጊዜ ለማራዘም ሲቀርብ የነበረው ምክንያት ተመሳሳይ ነገር ነው፣ ምክንያቱ 14 የምርመራ ቀናት ለመጠየቅ በቂ አይደለም ያሉ ሲሆን፣ የደንበኛችን ወንጀል የግል ተሳትፎ ተለይቶ አልቀረበም ሲሉ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን የጠየቀውን የምርመራ ግዜ ተቃውመዋል፡፡

Related stories   “በተለምዶ ‘ሸኔ’ የሚባለው ራሱን ‘የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት’ ብሎ የሚጠራው ቡድን ነው”

የሁለቱንም ክርክር የሰማው ፍርድ ቤት 8 የምርመራ ቀን የፈቀደ ሲሆን የምርመራ መዝገቡ ከቀጠሮ በፊት በፅኅፈት ቤት በኩል እንዲቀርብ አንዲሁም የግል መኪናቸው ለምን ያልተለቀቀበት ምክንያት በፅሁፍ እንዲቀርብ ትእዛዝ ሰጥቶ ለነሀሴ 28 2012 ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል፡፡

ዜናው ከዋዜማና ከቪኦኤ የተቀናበረ ነው

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *