“Our true nationality is mankind.”H.G.

አቶ ጃዋር በድብቅ የባለስልጣናትና ታዋቂ ሰዎችን ስልክ ይጠልፉ እንደነበር ፖሊስ ተናገረ፤ አቶ ጃዋር ምርመራው እኔን አይመለከትም ብለዋል

NtJDO

የፌዴራል መርማሪ ፖሊስ በአቶ ጃዋር ሲራጅ መሃመድ ቤት በድጋሚ ባደረገው ፍተሻ በግለሰብ እጅ የማይገኙ ሳተላይቶችና ከውጭ በድብቅ የገቡ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን ማግኘቱን ገለጸ።

መርማሪ ፖሊስ በሃምሌ 9 ቀን 2012 ዓ.ም. በፍርድቤቱ በተሰጠው የ13 ቀን ተጨማሪ ጊዜ የሠራውን አዳዲስ የምርመራ ሥራዎችን ይፋ አድርጓል።

መርማሪ ፖሊስ ባለፉት 13 ቀናት ሰራው ያለው አዲስ ሥራ፤

 • በአቶ ጃዋር ቤት በድጋሚ በተደረገው ፍተሻ የቴሌኮም መሳሪያዎች፣ በግለሰብ እጅ የማይገኙ የኤሌክትሮኒክስና የሳተላይት ዲሾችን ጨምሮ ሌሎችንም አግኝቷል። 
 • መሣሪያዎቹ ከውጭ በድብቅ መግባታቸውና ከውጭ ሀገር ባለሞያ አስመጥተው በድብቅ ማስገጠማቸውን ጠቅሷል። በመሣሪያው የታዋቂ ሰዎችን ስልክ በመጥለፍ ሚስጥራዊ ንግግራቸውን ያዳምጡ እንደነበር ማስረጃ ሰብስቢያለሁ ብሏል።
 • አቶ ጃዋር ጋር የተገኙት 7 ሽጉጦች ከፋብሪካ ሥሪታቸው ውጭ ሌላ ምልክት ተለጥፎባቸው መገኘቱን፣ ህገ ወጥ መሳሪያ መሆኑንም ማረጋገጡ ገልጿል።
 • በዕለቱ አቶ ጃዋር በOMN ተጠቅመው ብሄርን ከብሄር፣ ሃይማኖትን ከሃይማኖት ግጭት እንዲነሳ ባስተላለፉት ጥሪና ትዕዛዝ
  • በሀረር፣ በድሬዳዋ፣ በአ/አ በሌሎችም ቦታዎች በተነሳ ሁከትና ብጥብጥ በኦሮሚያ ክልል ብቻ 109 ንፁሃን ዜጎች ህይወታቸው ማለፉን፣
  • 137 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት መድረሱን፣
  • 44 ሆቴሎች መቃጠላቸውን፣
  • 2 ሃውልቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን፣
  • 328 የግል መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውን፣
  • 199 የንግድ ተቋማትና 2 የሰብዓዊ መብት ተቋማት ጉዳት መድረሳቸውን
  • 26 የግል ተቋማት መቃጠላቸውን 1 የእምነት ተቋም መቃጠሉን
  • 53 ተሽከርካሪዎች እንዲቃጠሉ ማድረጋቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ሰብስቢያለሁ ብሏል።
 • በአቶ ጃዋር ላይ 10 የተጠርጣሪ 25 የምስክር ቃል መቀበሉን ገልጿል።
 • ህገ ወጥ ቡድን በማደራጀት ንፁሃን ዜጎችን ሲያሳፍኑ እንደነበር ታዋቂ ሰዎች ላይ እርምጃ እንዲወስድ ትዕዛዝ ሲሰጡ እንደነበር ማስረጃ ሰብስቤአለሁ ብሏል።
 • ሃምሌ 23 የድምፃዊ ሃጫሉን አስክሬን ቀምተው ለ10 ቀን መስቀል አደባባይ ለማቆየት፣ የሚኒሊክ ሃውልት እንዲፈርስ ለማድረግና 4 ኪሎ ቤተመንግሥት ገብተው ጥቃት ለመፈፀም መሞከራቸውን የሚገልፅ 25 የምስክር ቃል ተቀበዬአለሁ ብሏል።
 • በአዲስ አበባ በዕለቱ በቦሌ ክ/ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ገቢዎች ቢሮን ጨምሮ 166 ሚልዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙን የሚያመላክት ማስረጃ ማግኘቱን ጠቅሷል።
 • በቡራዩ አስክሬን ሲቀሙ በተፈጠረው ተኩስ 4 ሰዎች መሞታቸውና 4 ሰዎች ከፍተኛ የአካል ጉዳት መድረሱን ጠቅሷል። እንዲሁም በቡራዩ 7 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን መረጃ አግኝቻለሁ ብሏል።
 • የዓይን ማስረጃና ታማኝ ምስክሮችን በየአድራሻቸው አፈላልጌ ለማግኘትና ቃል ለመቀበል ሌሎች ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ወደ ኦሮሚያ ክልል ያቀኑ 17 የምርመራ ቡድኖች የምርመራ ውጤት ለማምጣት ፣ የግልን የመንግሥት ተቋማት መረጃ ለመሰብሰብ 14 ቀን ይሰጠኝ ብሏል።
Related stories   አሜሪካ ለጊዜው ሲባል የከረመ ሃሳብ ያካተተ መግለጫ አወጣች፤ ምርጫውን በተዘዋዋሪ ደግፋለች

የአቶ ጃዋር መሃመድ ጠበቆች፤

 • የመርማሪ ፖሊስ ስራ ግልፅ አይደለም፣ የተለየ የምርመራ አላየንም፣ ከዚህ በፊት 34 ምስክሮችን ቃል መቀበሉን ገልጿል፤ ዛሬ 25 ብሏል ይህ የተዛባ ነው፤ ምርመራውን በተፋጠነ ሁኔታ እየሰራ አይደለም፤ ደንበኛችንን በእስር ለማቆየት ያቀረበው ተጨማሪ ጊዜ ጥያቄ እንጂ ያቀረበው ምክንያት ተጨማሪ ጊዜ አይሰጥም ብለዋል። ፍርድ ቤቱ መርማሪ ፖሊስ ያለውን የሚያምንበት ከሆነ እንኳን አጭር ጊዜ ሊሰጠው ይገባል፤ ደንበኛችን በዋስ ይውጡ ብለዋል።

መርማሪ ፖሊስ፤

 • ምርመራ እያደረግን ያለነው ፍርድ ቤት በሰጠን ጊዜ ነው፤ ዛሬም አዳዲስ ግኝቶችን ነው ያቀረብነው ከባለፈው ከቀረበው ምስክር ውጭ ነው ያቀረብነው ብሏል።
 • እኛ የውሸት ምርመራ አይደለም እያደረግን ያለነው በተፈፀመ ወንጀል ላይ ነው ሰፊ ምርመራ እያደረግን የምንገኘው ብሏል።
 • አቶ ጃዋር በዋስ ቢወጡ ማስረጃዎችና ምስክር ሊያሸሹ ይችላሉ ሲል የዋስትና ጥያቄውን ተቃውሟል

የአቶ ጃዋር መሃመድ ጠበቆች፤

 • ምርመራው የፖለቲካ ጉዳይ ነው፤ ፍርድ ቤት ላይ ተፅእኖ ለማሳደር የሚደረግ ተግባር ነው ብለዋል።

መርማሪ ፖሊስ፤

 • አቶ ጃዋር በOMN ኦንላይ ባስተላለፉት ቅስቀሳ በወንደመው ንብረት ፣በጠፋው የሰው ህይወት መነሻ ነው ምርመራ እያደረግን ያለነው ይህን ፍርድ ቤቱ ይገንዘብልን ብሏል።

አቶ ጃዋር መሃመድ በራሳቸው ያቀረቡት አቤቱታ፤

 • የችሎት ውሎውን የምንፈልገው ሚዲያ እንዲዘግቡልን ይደረግ፤ የመንግሥት ሚዲያዎች ብቻ ነው እየዘገቡ ያሉት፤ እነሱም የፖሊስ ምርመራ ብቻ ነው የሚያቀርቡት ሚዛናዊ አይደለም፤ ስለዚህ እኛ የምንፈልጋቸው ይዘግቡልን ሁሉም ይፈቀድ አልያም ሁሉም ይከልከሉልን ሲሉ ጠይቀዋል።
Related stories   የመ/ሰራዊትን መለያ ለብሶ ከሱዳን ወደ ወልቃይት ሊገባ የነበረ የትህነግ የሽብር ሃይል ተደመሰሰ፤

የፍርድ ቤት ምላሽ፤ 

 • ችሎቱ ግልፅ ችሎት ነው፤ ማንም ሚዲያ ገብቶ መዘገብ ይችላል፤ እስካሁን ባለው ችሎት በሚዲያ የሚቀርበውን የችሎት ውሎ የመርማሪን ሥራና የእናተን መቃወሚያ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ያቀረቡትን በግል ደረጃ ለማዳመጥ ሞክረናል ስህተት አላየንም፤ የተዛባ ዘገባ ካለ ሚዲያውን ጠቅሳችሁ አቤቱታ ማቅረብ ትችላላችሁ። ከአሁን በኋላ አቶ ጃዋር ስለ ሚዲያ እንዳያነሱና አስተያየት እንዳይሰጡ ብሏል። የሚመለከታቸው ጉዳዮችን ላይ ብቻ እንዲያነሱ ገልጿል።

አቶ ጃዋር መሃመድ፤

 • ለፖሊስ ያለኝን ክብር እገልፃለሁ፤ በፌደራል ፖሊስ ጠበቃ ሲደረግልኝና ከፍተኛ ትብብር ሲደረግልኝ ነበር።
 • እዚህ ያሉ መርማሪዎች ፕሮፌሽናል ናቸው ይህንን አውቃለሁ ምርመራው ግን የፖለቲካ ጉዳይ መሆን ለመግለፅ እወዳለሁ። 
 • ፖሊስ ተገኝቷል ያላቸው 7 መሳሪያዎች ከፌደራል ፖሊስ የተሰጡኝ መሳሪያዎች ናቸው፤ አራቱም ለጥበቃ የተመደቡልኝ እንጂ ከጫካ ያስመጣኋቸው ወንበዴዎች አይደሉም፤ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የደህንነት አካላት ጋር ህጋዊ የሚባሉ እስከ ቤተ መንግሥት ባሉ ፌደራል ፖሊስ ታማኝ መሆናቸው ተረጋግጦ የተመደቡልኝ ጠባቂዎች ናቸው እንጂ ነብስ በላ አይደሉም።
 • ከ1,000 በላይ መሳሪያ በታጣቂዎች በደቡብና በምዕራብ ኦሮሚያ ሲገቡ ከአባ ገዳዎች ጋር ተነጋግሬ ለመንግሥት መሳሪያውን አስረክቢያለሁ ከዚህ በፊት።
 • ከኤሌክትሮኒክስ ጋር የተነሳው በጉሙሩክ በኩል አስፈላጊው ቀረጥ ከፍዬ ያስገባሁት ነው። 
 • እዚህ ሀገር ሰላማዊ ትግል ለማድረግ ነው ስንቀሳቀስ የነበረው፤ በሱማሌና ኦሮሚያ ክልል ተፈጥሮ የነበረውን ግጭት ለመፍታት መኖሪያ ቤቴ ድረስ አስመጥቼ አስታርቂያለሁኝ።
 • አፋርና አማራ ክልል ድረስ በመሄድ ህዝቦችን ትስስር እንዲፈጠር ሰርቻለሁ፤ በኦሮሚያና አማራ ክልል ግጭት እንዳይፈጠር ጥሪያለሁኝ። 
 • የሃይማኖት ግጭት ፈጠረ ለተባለው እናቴ ኦርቶዶክስ ናት፣ ባለቤቴ ፕሮቴስታንት ናት፣ ከእኔ ጋር የተያዙት በተለይ አጃቢዎቼ ግማሹ ኦርቶዶክስ ግማሹ ደግሞ ፕሮቴስታንቶች ናቸው፤ ይህ የፖለቲካ ጉዳይ ነው፤ የፖለቲካ ችግርን በፖለቲካ መድረክ መፍታት እንጂ በዚህ ልክ ሊሆን አይገባም፤ እኔንም ሌሎችንም ከምርጫ ለማስቀረት ታስቦ ነው የታሰርኩት፤ እኔን የፖለቲካ ማስፈፀሚያ ከማድረግ የጠበቆችን ጊዜም ማባከን አይገባም እኔና እስክንድር ነጋ የተለያየ አመለካከት ነው ያለን ነገር ግን በአንድ ዓይነት ክስ ላይ ነው እየተከሰስን ያለነው ይህ ተገቢነት የለውም።
Related stories   ትህነግን በብሄራዊ ውይይት እንዲሳተፍ የሚደረግ ግፊት መኖሩን መንግስት ይፋ አደረገ፤ " ፍጹም ተቀባይነት የለውም" ብሏል

የፍርድ ቤቱ ምላሽ፤

 • ፍርድ ቤቱ የፖለቲካ ማስፈፀሚያ አይደለም፤ ጉዳዩን ገለልተኛ ሆኖ ነው እያየ ያለው፤ እንዲህ ዓይነት የፖለቲካ ጉዳይ መነሳት እዚህ የለበትም፤ እዚህ መነሳት የሚችለው የህግ ጉዳይ ነው፤ የፖለቲካ ጉዳይ በሌላ ቦታ ማየት ትችላላችሁ፤ እርስዎን (አቶ ጃዋርን) ፍርድ ቤቱ ገለልተኛ ሆኖ እየተመለከተ ነው ብሏል፤ በጉዳዩ ላይም ትዕዛዝ ሰጥቷል።

መርማሪ ፖሊስ፤

 • 7 መሳሪያ ለOMN ጥበቃ የተፈቀደልኝ ነው ያሉት ትክክል ነው ተፈቅዷል፤ ነገር ግን ከዓላማው ውጭ፣ ህገ ወጥ ወንጀል ሲፈፀምበት፣ ተተኩሶም የሰው ህይወት ሲያልፍበት ነው የተያዘው።
 • እኛም የፖለቲካ አባል አይደለንም፤ መርማሪዎች ነን የተፈፀመውን ወንጀል እናጣራለን እንጂ የፖለቲካ ተለጣፊዎችና ደጋፊዎች አይደለንም። እንዲህ ያሉ የፖለቲካ ጉዳዮችን ፍርድ ቤት ያስቁምልን ብለዋል።
 • አጃቢዎቻቸው በተለያዩ ተቋማት ተቀጥረው ሲሰሩ ነበር ከተቋማቱ በህገ ወጥ መንገድ የኮበለሉ መሆናቸውን የፅሁፍ ደርሶናል። አጃቢዎቹ ከመንግሥት እንዳልተመደቡና ህጋዊ እንዳልሆኑ ገልጿል።

ለተጨማሪ ምርመራ 12 ቀን በመፍቀድ ለነሃሴ 5 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።ምንጭ ፦ ታሪክ አዱኛ (ኤፍ.ቢ.ሲ)

ሙሉ ሪፖርቱን ያድምጡ

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0