“Our true nationality is mankind.”H.G.

መንግስትና ኦብነግ በክልሉ ቁልፍ የተባለ የሰላም ስምምነት አደረጉ፤ ኢንቨስተሮች ለልማት እንዲገቡ ተጋበዙ

በአሁኑ ወቅት በሶማሌ ክልል አንድም የጥይት ድምጽ ስለማይሰማና እንደፈለገ ተዛውሮ መራት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ስለተፈጠረ አልሚዎች በክልሉ ያለውን ሰፊ መሬት ተጠቅመው ወደ ልማት እንዲገቡ ጥሪ ቀረበ። የክክሉ መንግስትና የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር በጋራ አሁን ያለውን ሰላም ለማስተበቅ የሚያስችላቸውን ቁልፍ ስምምነት ማድረጋቸው ተነገረ።

በኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አወጪ ግንባርና በክልሉ መንግሥት መካከል የሰላም ስምምነት መፈረሙ ለክልሉ ሰላምና ፀጥታ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ።

የሶማሌ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አሊ በደል በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር በስልክ ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት፤ በቀደሙት ዓመታት ያለመረጋጋትና ከፍተኛ የፀጥታ ስጋት እንደነበረ አመልክተው፤ አሁን ግን የተሻለ ሰላምና መረጋጋት ሰፍኗል፤ በኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) እና በክልሉ መንግሥት መካከል የተደረሰው ስምምነት ይህንኑ አጠናክሮ ለመቀጠል ያስችላል።

Related stories   ሰላም፣እርጋታና የዜጎች ደህንነት ለኢትዮጵያውያን ፍትሃዊ እድገት ወሳኝ ናቸው – በአሜሪካ የህዝብ ዲፕሎማሲ አማካሪ ምክር ቤት

የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር ጫካ በነበረበት ወቅት በክልሉ የነበረው ያለመረጋጋት አሁን ሙሉ ለሙሉ መቀረፉን ያስታወሱት አቶ አሊ፤ በአሁኑ ወቅት አንድነትን በማጠናከር፣ ፀጥታን በማስከበርና ሰላምን በማስፈን ዙሪያ የተደረሱ ስምምነቶች ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑን አስታውቀዋል።

ስምምነቱ የሶማሌ ክልል በኢትዮጵያ የድንበር አካባቢ ላይ እንደመገኘቱ ፤ የሀገር ውስጥ ሰላምን በማስከበር ከውጭ የሚመጣውን ጫና መቀነስ እንደሚያስችል አስረድተው፤ ሰላምን ከማስከበር ባሻገር የፀጥታ ስጋት በማይኖርበት በእንደዚህ ዓይነቱ ወቅት ወጣቶች በስራ ፈጠራ ያለምንም መስተጓጎል እንዲሳተፉ የሚያስችሉ ስራዎችን ለመስራት መታቀዱንም ተናግረዋል።

ቀደም ሲል የህዝቡ እንቅስቃሴ የተገደበ፤ በኅብረተሰቡም ዘንድ የነበረው የፀጥታ ስጋት ከፍተኛ የነበረ ሲሆን፤ አሁን ላይ ያ ችግር ተቀርፎ ክልሉ የተሻለ ሰላም ባለቤት ሆኗል፤ የተገኘውን ሰላም ለማስቀጠልም በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ተደርሷል ብለዋል።

Related stories   ምዕራባዊያን አገራት በኢትዮጵያ ላይ እያራመዱት ያለው አቋም የዴሞክራሲ መርህን የጣሰ ነው

አቶ አሊ ቀደም ሲል አሳሳቢ የነበረው የሰላም መደፍረስ ስለተቀረፈና ክልሉ ለግብርና የተመቸ መሬት፤ በርካታ ወንዞች የሚፈሱበት፤ ምርታማ አካባቢ በመሆኑ የክልሉ ወጣቶችን በግብርና ዘርፍ በስፋት ለማሰማራት ታቅዷል ብለዋል ።

አቶ አሊ ክልሉ የድንበር አከባቢ እንደመሆኑ ሰላም በተጠበቀ ቁጥር ህገወጥ የነበረውን የንግድ እንቅስቃሴ ህጋዊ በማድረግ ሀገሪቱንም ሆነ ክልሉን ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱን አብራርተዋል።

ተቃዋሚና ገዥው ፓርቲ ለሰላም ቁጭ ብሎ ሲወያይ ይህ የመጀመሪያው ነው ያሉት አቶ አሊ ፣ አሁን አንድም ቦታ የጥይት ድምፅ መሰማት ቆሟል ብለዋል። በክልሉም ከፍተኛ የመልማት አቅም ያለው መሬት በመኖሩ ወደ ክልሉ መጥቶ የልማቱ አካል ለመሆን የሚፈልግ ወደ ክልሉ መጥቶ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። ለዚህም ቀልጣፋ መስተንግዶ እንደሚጠብቃቸውም አስታውቀዋል ።

Related stories   ‹‹የህዳሴው ግድብ ለሱዳን ከፍተኛ ጥቅም አለው፤ የቀጠናውን የኢኮኖሚ ትስስር ያጠነክራል››

የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር በመንግሥት በኩል ለንግግርና ለሰላም እየተወሰዱ ያሉ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች አዎንታዊ መሆናቸውን በመገንዘብ ከሐምሌ 6 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ የተኩስ አቁም ስምምነት ማድረጉ ይታወሳል።

አዲስ ዘመን ሐምሌ 22/2012

ምስል – የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል ፋይል

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0