“Our true nationality is mankind.”H.G.

በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አጋማሽ ከ4 ነጥብ 1 ቢሊዮን በላይ ችግኝ ተተከለ

በዘንድሮው  የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አጋማሽ ላይ እያለን   ሊተከል ከታቀደው  5 ቢሊዮን ችግኝ   4 ነጥብ 1 ቢሊዮን መተከሉ ዕቅዱ፣ዝግጅቱና ተሳትፎው ውጤታማ እንደነበር ያሳያል ሲሉ  ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ገለጹ

ጠቅላይ ሚኒስት ዶክተር አብይ አህመድ ዛሬ የአረንጓዴ አሻራ  የቴክኒክ ኮሚቴ  በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ተገኝቶ ያቀረበውን   የስራ አፈጻጸም ሪፖሪት አዳምጠዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር በዚሁ ወቅት በሰጡት አስተያየት  በሶስት ወራት ሊተከል ከታቀደው 5 ቢሊዮን ችግኝ  4 ነጥብ አንድ ቢሊየኑን በአንድ ወር ተኩል መትክል መቻሉ የዝግጅቱንና የተሳትፎውን ውጤታማነት ያሳያል ብለዋል፡፡

በመርሃግበሩ አጋማሽ የእቅዱን  83 በመቶ ማሳከት ከተቻለ በቀሪው ጊዜ የበለጠ ተግቶ በመስራት ከእቅዱ በላይ መስራት እንደሚቻልም ጠቅሰዋል፡፡  የአረንጓዴ አሻራው ልክ እንደ ህዳሴው ግድብ  ያቀድነውን  ማሳካት አንደምንችል ያሳየንበት አንዱ ፕሮጀክት ነውም ብለዋል፡፡

Related stories   የዘረኝነት ጥግ “እናት ነኝ የሌሎች ህፃናት ወላጆችን ግን ገደልኩ”

ሐምሌ 22 እንነሣለን በዛፍ ታሪክ እንሠራለን አረንጓዴ ...

የአረንጓዴ አሻራን ጉዳይ እንደሁለተኛ ሳይሆን አንደዋነኛ ጉዳያችን መመልክት አለብን ያሉት  ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤  አሁንም  ከዚህ የበለጠ ትኩረት መስጠት እንደሚስፈልግ ጠቅሰዋል፡፡  እያንዳንዱ ተቋምም ቀዳሚ ተግባሩ አድርጎ መንቀሳቀስ ይኖርበታል ብለዋል፡፡ አረንጓዴ አሻራው ከምንተክለው ችግኝ ባሻገር የስራ እድል መፍጠርና ኢኮኖሚዊ ተጠቃሚነትንም እያረጋገጠ መሄድ እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡

አረንጓዴ አሻራ የቁጥሩ ጉዳይ ሳይሆን በየቀኑ እየተከልን የሚገኘውን ዘላቂ ጥቅም የምናረጋግጥበት ሂደት መሆን አለበት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ክልሎች ባስመዘገቡት ውጤት ሳይዘናጉ የተሻለ ለመስራት መትጋት እንዳለባቸውና አስፍተው ማቀድ እንደሚገባቸውም  አሳስበዋል፡፡ በዝቅተኛ አፈጻጸም ላይ ያሉ ክልሎችንም ማነቃቃትና መደገፍ  እንደሚስፈልግ ጠቅሰዋል።

Related stories   የዘረኝነት ጥግ “እናት ነኝ የሌሎች ህፃናት ወላጆችን ግን ገደልኩ”

በሚቀጥለው ዓመትም ሀገር በቀል ችግኞችንና   የተለያዩ የፍራፍሬ አይነቶችን ከወዲሁ በማዘጋጀት  በተለይም እንደ አፋርና ሶሜሌን በመሳሰሉ ቆላማ አካባቢዎች በመትክል  ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን እያረጋገጡ መሄድ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡

በቀጣይ በ2013 ዓ.ም በርካታ ችግኞችን ለመትከል ከወዲሁ መዘጋጀት እንደሚስፈልግና  ይህ ባህላችንም ከእኛ አልፎ ወደ ጁቡቲ ፣ኬኒያ፣ ኤርትራ እና ሌሎችም የጎረቤት ሀገራት መዳረስ እንደሚገባው ገልጸዋል፡፡

አካባቢው አረንጓዴ ካልሆነ የምንፈልገውን ዝናብ ማግኘት አንችልም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እኛ የምንተክለው ችግኝ ለእነርሱ ፤እነርሱም የሚተክሉት ለእኛ ጠቃሚነው ብለዋል።

Related stories   የዘረኝነት ጥግ “እናት ነኝ የሌሎች ህፃናት ወላጆችን ግን ገደልኩ”

በኢያሱ መሰለ – አዲስ ዘመን

ፎቶ በጸሀይ ንጉሤ

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0