“Our true nationality is mankind.”H.G.

“ዛሬ ከነወንጀሉ የምታሞካሹት ወያኔ ስንረሸን እነዚህ ጋንግስተሮች፣ አሸባሪዎች እና አረመኔዎች ይለን ነበር” አፈንዲ

አቶ አፈንዲ ሙተቂ ከወያኔ ሚዲያዎች እየተቀበሉ በኦሮሞ ሚዲያዎች ማሰራጨት አቁሙ ሲል ጠየቀ። ይህን ቡድን ከነወንጀሉ ማሞከሸት ይቅር የማይሉት ስህተት ነው በማለትም በገሃድ አውግዟል።
” ደግሜ እናገራለሁ ወያኔ በምንም ተዓምር የኦሮሞ የትግል አጋር መሆን የማይችል የወንጀለኞች ጥርቅም ነው” ሲል አፈንዲ የጠየቀው አስቀድሞ ይህንን አቋሙን በመግለጹ ሳቢያ በግል ለደረሱት መልዕክቶች የማያወላዳ አቋም እንዳለው ለማሳሰብ መሆኑንን ገልጿል።
ጸሃፊና ጥናት አቅራቢው አፈንዲ “ስርዓት ያዙልን” ካለ በሁዋላ ” እንዴ!!” ሲል ጠይቆ ” ከመቶ ዓመት በፊት የሞተው ምኒልክን በጥፋቱ እያወገዝን ትናንት ሰው ሲፈጅ የነበረውን ወያኔን ስታደንቁብን አታፍሩም እንዴ? እንዲህ ዓይነት ውርደት አይቼ አላውቅም” ሲል ዛሬ ህወሃትን የትግል አጋር አድረገው በሚሰሩ የኦሮሞ ሚዲያና ልሂቃን ላይ የሰላ ትችት ሰንዝሯል።
“ዛሬ ከነ ወንጀሉ እንደ ጀግና የምታሞካሹት ጌታቸው ረዳ ከሶስት አመት በፊት የኦሮሞ ልጆች በጥይት በሚታጨዱበት ወቅት ‘እነዚህ ጋንግስተሮች፣ አሸባሪዎች እና አረመኔዎች ናቸው። ይህንን የጋንግስተር ቡድን ልክ እናስገባለን’ እያለ ሲደነፋ ነበር። ጌታቸው ረዳን ማሞገስ የእነዚያ ሰማእታት ደም ከንቱ ነው ብሎ እንደመሳደብ ነው” ሲል አፈንዲ የመረረ ቅሬታውን አሰምቷል። ተግባሩንም ” ውርደት” ብሎታል።
የመሰለውን ሃሳብ በማቅረብ የሚታወቀው አፈንዲ ሙተቂ ” እኔ የምለው” ሲል በመገረም ቅሬታውንና ሃፍረት  ያለውን ያብራራል።
Related stories   አሜሪካ ለጊዜው ሲባል የከረመ ሃሳብ ያካተተ መግለጫ አወጣች፤ ምርጫውን በተዘዋዋሪ ደግፋለች

“የኦሮሞ ህዝብ ትግል ያለ ወያኔ ድጋፍ ግቡን አይመታም” ያላችሁ ማን ነው? የወያኔ አጋርነትን ወእደኛ መሳብ ለምንድነው የምትፈልጉት? ወያኔን ሳታደንቁትና እርሱ የሚዘባርቀውን ውሸት በሚዲያ ሳታሰሙን ለኦሮሞ ህዝብ መታገል አይቻልም እንዴ? ለምን የታላቁን የኦሮሞ ህዝብ ሃይል ዝቅ አድርጋችሁ ትመለከታችሁ? ይህ ትልቅ ክህደት እና ዝቅጠት ነው”

በሪዮ ኦሊምፒክ አደባባይ ውድድሩን በድል ያጠናቀቀው ፈይሳ ሌሊሳ ከለውጡ በሁዋላ ባየው ተመሳሳይ የህወሃትና የኦሮሞ ድርጅቶችና ፖለቲካ አመራሮች የትግል ትብብር ቅሬታውን መግለጹ አይዘነጋም። በዚህም አቋሙ በተደጋጋሚ ቅሬታና ትችት ሲሰነዘርበት እንደነበር የሚታወስ ነው።
Image may contain: 1 person, text
በቅርቡ በቅጥር ነብሰ ገዳዮች በድንገት የተቀጠፈው ሃጫሉ ከመገደሉ ሳምንት በፊትና ቀደም ሲል ጀምሮ የወያኔንና የኦሮሞ ፖለቲከኞችን የትግል አጋርነት፣ የኦሮሞ ፖለቲከኞችን የአስመራ ጉዞ ” ሃፍረት ነው” ሲል ማውገዙ የቀርብ ቀን ትዝታ ነው። መረጃዎች እንደሚሉት ሃጫሉ በዚህ አቋሙ የተነሳ ሃሳቡ ተቆርጦ እንዳይተላለፍ ተደርጓል። ይህም የግድያውን ቅንብር ያመላክታል በሚል በስፋት እየተነገረም ነው።
አፈንዲ በፌስ ቡክ ገጹ ይህንን አስፍሯል።
አሁንም ልድገመው። ከወያኔ ቤት የተለቀቁ ዜናዎችን በኦሮሞ ሚዲያ ማስነገር አቁሙ። ወያኔ በምንም ተአምር የኦሮሞ ትግል አጋር መሆን የማይችል የወንጀለኞች ጥርቅም ነው። ዛሬ ከነ ወንጀሉ እንደ ጀግና የምታሞካሹት ጌታቸው ረዳ ከሶስት አመት በፊት የኦሮሞ ልጆች በጥይት በሚታጨዱበት ወቅት “እነዚህ ጋንግስተሮች፣ አሸባሪዎች እና አረመኔዎች ናቸው። ይህንን የጋንግስተር ቡድን ልክ እናስገባለን” እያለ ሲደነፋ ነበር። ጌታቸው ረዳን ማሞገስ የእነዚያ ሰማእታት ደም ከንቱ ነው ብሎ እንደመሳደብ ነው። ስርዓት ያዙልን።
እንዴ!! ከመቶ ዓመት በፊት የሞተው ምኒልክን በጥፋቱ እያወገዝን ትናንት ሰው ሲፈጅ የነበረውን ወያኔን ስታደንቁብን አታፍሩም እንዴ? እንዲህ ዓይነት ውርደት አይቼ አላውቅም።
እኔ የምለው
“የኦሮሞ ህዝብ ትግል ያለ ወያኔ ድጋፍ ግቡን አይመታም” ያላችሁ ማን ነው? የወያኔ አጋርነትን ወደኛ መሳብ ለምንድነው የምትፈልጉት? ወያኔን ሳታደንቁትና እርሱ የሚዘባርቀውን ውሸት በሚዲያ ሳታሰሙን ለኦሮሞ ህዝብ መታገል አይቻልም እንዴ? ለምን የታላቁን የኦሮሞ ህዝብ ሃይል ዝቅ አድርጋችሁ ትመለከታችሁ? ይህ ትልቅ ክህደት እና ዝቅጠት ነው።
እረፉልን አቦ! እረፉልን። እረፉልን።
በዘበዛ ሁላ!!
0Shares
0