የፌዴሬሽን ምክር ቤት የመንግስትን የስልታን ዘመን በህግ በማራዘሙ የትግራይ እንደራሴዎችን ከተቀመጠው ጊዜ በፊት ማሰናበት ህግን የተንተራሰ የውስጥ ጥያቄ ስለሚያስነሳ እንዳለ መቀበሉ ህወሃት ሌላ አማራጭ ስለሌለው እንደሆነ ተጠቁሟል። ሌላም ምክንያት አለው።

የትግራይ ክልል ራሱን ችሎ ምርጫ ለማካሄድ አቋም መያዙን ተከትሎ ምርጫው ከተካሄደ አሁን ፓርላማ ውስጥ ያሉ የትግራይ እንደራሴዎች ሙሉ በሙሉ እንዲመረጡ እቅድ መያዙ ተሰማ። ለፓርላማ አባላቱ ዋስትናም እንደተሰጣቸው ታውቋል።

የህወሃት ከፍተኛ አመራር የነበሩና በህወሃት በተፈጠረው ወቅታዊ የሃይል መከፋፈል የተነሳ መረጃ የማግኘት እድል እንዳገኙ በመግለጽ ለዛጎል መረጃ የሰጡ እንዳሉት አሁን በስራ ላይ ያሉት የፓርላማ አባለት የስራ ጊዜያቸውን ሳይጨርሱ ማባረር እንደማይችል የህወሃት አመራሮች አምነዋል።

ከፓርላማ አባላቱ መካከል ህወሃት ማሰናበት ቢፈልግ ” የስራ ጊዜዬን አልጨረስኩም” የሚል ጥያቄ እንደሚነሳ ያብራሩት የዛጎል የመረጃ ምንጭ፣ ይህንን ውዝግብ ለማስቀረት ሲባል ነው እንደገና እንዲመረጡ የሚደረገው። ይህም ለፓርላማ አባላቱ በቃል ደረጃ ተነግሯቸዋል።

Related stories   Egypt-Sudan alliance shifting in row with Ethiopia over Nile dam

የትግራይ እንደራሴዎች ማንኛውም የፓርላማ አባል የሚያገኘው ጥቅምና አስፈላጊ የክብርና የህግ ከለላዎች እንዲሁ በቀላሉ እንዲወሰዱባቸው እንደማይፈልጉ በቅርብ መስማታቸውን የመረጃ ምንጩ ገልጸዋል። ” ስለዚህም” አሉ ” ስለዚህም ህወሃት የምርጫ ጉዞው ገና ባልጸዳበት ሁኔታ ሌላ ችግር ውስጥ መግባት ስለማያዋጣው፣ የፌደራሉ መንግስትም የሚያውቃቸው ስራቸውን ያልጨረሱትን ተመራጮች በመሆኑ ጉዳዩን በስምምነት ዘግቷል” ሲሉ ያክላሉ።

እውነታው ይህ ቢሆንም ሌላም የተለየ ሃሳብ መስማታቸውን የገለጹት የመረጃው ባለቤት፣ ምርጫው በመራዘሙ ምክንያት አሁን ያለው ካቢኔ የስራ ጊዜው በመራዘሙ ህወሃት ተሳክቶለት ምርጫ ካካሄደና አዲስ የፓርላማ አባላትን ቢሰይም የፌደራል መንግስት አይቀበልም። ፓርላማም አይገቡም። በዚሁ መነሻ አሁን የስራ ጊዜያቸውን ያልጨረሱት የትግራይ እንደራሴዎች እንደ አዲስ በድጋሚ ተመርጠው ከመጡ በቀድሞው ስማቸው ፓርላማ እንዲገቡ ህወሃት ያሰላው ሂሳብ ነው።

ህገ መንግስትና የምርጫ ቦርድን ስልጣን በመርገጥ ሊካሄድ የታሰበውና ኮሚሽን አቋቁሞ ወደ ስራ የተገባበት ምርጫ በአስቸኳይ እንዲቆም የፌደሬሽን ምክር ቤት ማሳሰቡ ይታወሳል።

Related stories   “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገው

ሰሞኑንን ከተቀናቃኝ ፓርቲዎች ጋር የተወያዩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የትግራይ ክልል እስከ ሚቀጥለው ምርጫ ድረስ ክልሉን እንዲያስተዳድር ህጋዊ ፈቃድ እንዳለው ጠቅሰው ምርጫ ማድረጉና በጀት መከስከሱ አይጠቅምም ሲሉ ጉዳዩን ተከትሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ መልሰው ነበር። አያይዘውም ምርጫውን ከዕድርና ከእቁብ ጋር አመሳስለው የተባለው ጊዜ ሲደርስና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሲጠይቅ መንግስት ህጋዊ አካሄድ እንደሚከተል ይፋ አድረገዋል።

ህወሃት አዲስ እንደራሲዎች ለመሰየምም ሆነ ቋንቋ ቀይሮ ነባሮችሁን በአዲስ አስመርጦና ከመካከላቸው መቀሌ የሚቀመጡትን ቀንሶ ለመላክ ያሰላው ሂሳብ እንደማይሳካ በተደጋጋሚ የሚገልጹ ወገኖች ህወሃት የምርጫ አጀንዳ ሲያራምድ የነበረው ኦሮሚያና ሲዳማ እንዲሁም አዲስ የክልልነት ጥያቄ የሚያነሱትን አስተባብሮ የገንዘብ ድጋፍ በመስጠት የፌደራልስትች ሃይል በሚል መንግስት ለመመስረት አስቦ ነው። ይህ ሃሳብ ዛሬ ላይ ስለመከነ ህወሃት ምርጫውን እንዴት አድርጎ እንደሚተወውም ግራ እንደገባው አንዳንድ ምንጮች ይናገራሉ። አፍቃሪ ህወሃት የሆኑ ደግሞ ” አገረ ትግርይ ይፋ ይሆናል” ሲሉ ይደመጣሉ።

Related stories   አስከሬን እንዲለቀም ታዘዘ - ትህነግ የአጽም ፖለትካ ድራማ ይፋ ሆነ

ዛጎል ዜና ለአንባቢያን ሲባል ማስታወቂያ የማትቀበል፤ አድማስዋን አስፍታ መረጃ ለማድረስ እየሰራች ያለች ገለልተኛ ሚዲያ ናት። ድግፍዎን ይስጡን፣ ይጻፉ፣ በአገርዎ ጉዳይ ባይተዋር አይሁኑ 


 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *