“ማን ነው ማንን የሚወጋው? ለምንድነው የፌደራል መንግሥት ትግራይን የሚወጋው? ይህ የእብደት ንግግር ነው። የፌደራሉ መንግሥት የራሱን ሕዝብ የመውጋት ሃሳብና ፍላጎት ፍጹም የለውም” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ መናገራቸውን ተከትሎ በትግራይ ክልል ወታደራዊ ሰልፍ ተደረገ።

ሰልፉ የተደረገበት ዓላማ በግልጽ ባይነገርም የትግራይ ክልል የጸጥታ ቢሮ “ለሰላም ሲባል ለሚከፈል ዋጋ ሁሌም ዝግጁ ነን” በማለት በኦፊሳል ፌስቡክ ገጹ አስፍሯል።

በትግራይ መቀለ ሰፊ ቁጥር ያላቸው የክልሉ የልዩ ኃይል አባላትና ሚሊሻዎች ከባድና ቀላል የጦር መሳሪያዎችን አንግበው በሰልፍ ጎዳና ሞልተው ወደ ስታዲዮም ሲተሙ ታይተዋል። በሌሎችም የክልሉ ከተሞች ተመሳሳይ ስለፍ መካሄዱን የሚያሳዩ ምስሎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ተሰራጭተዋል።

በሁመራ ተካሄደ በተባለው ሰልፍ ” ያበጠው ይፈንዳ ” የሚል መፈክር መያዙን ከትግርኛ ወደ አማርኛ ከተተረጎመ ጽሁፍ ለመረዳት ተችሏል። ሰልፉ የአማራ ክልል ህወሃት በድንበር ከተሞች ትንኮሳ እያካሄደብኝ ነውና ራሴን ለመከላከል እገደዳለሁ በሚል በይፋ ለተናገረው ምላሽ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል።

የትግራይ ክልል አስተዳዳሪ ህወሃት ራሱን ከብልጽግና ካገለለ በሁዋላ በግልጽ በማይታወቅ ምክንያት እያደር ከፌድራሉ መንግስት ጋር ተካሯል። ህወሃት ብልጽግናን ለማስወገድ የሚያስችለው አቅም ለመገንባት የፌደራሊስት ሃይሎች በሚል አርባ አምስት የሚጠጎ ድርጅቶችን አሰባስቦ እንደነበር አይዘነጋም። ከ360 ሚሊዮን ብር በላይ መድቦ በመቀሌ ጉባኤ ካካሄደ በሁዋላ ታላቅ ድግስ አድርጎ ጭፈራ በላይቭ ዝግጅት አሳይቶም ነበር።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

ከመስራቾቹ አንዱ የሆኑት አቶ ትግስቱ አወሉ ሰሞኑንን በፓርቲዎች ስብሰባ እንደተናገሩት መንግስትን ሆን ብሎ “አሃዳዊ” በሚል በመፈረጅ ለሌሎች ብሄረሰቦች ጋር ለማጣላት እቅድ ተይዞ እንደነበር ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።

በዛሬው ስለፍ ከታዩት መፈክሮች መካከል አንዱ 

ብዙም ሳይቆይ የተሰባሰቡት ድርጅቶች ሰብሳቢያቸውን ጨምሮ ህብረቱን በመለየታቸው፣ ተለይተውም አዲስ አበባ ስብሰባ በማድረግ ህወሃትን ማውገዛቸው ህወሃትን ሌላ አማራጭ እንዲከተል እንዳስገደደው ቀደም ሲል ጀመሮ ሲነገር ነበር።

ክልሉ ህገወጥና ህገመንግስቱን  በጣሰ መልኩ ምርጫ አካሂዳለሁ የሚለውም አሳብ የሚገፋበት ከሆነ የፌዴሬሽን ምክር ቤት “በሕገ መንግሥቱና ሌሎች ሕጎች የተሰጠውን ስልጣን ለመተግበር እንደሚገደድ” ባስጠነቀቀ አጭር ቀናት ውስጥ ህወሃት ወታደራዊ አማራጭ ለመከተል እንዳሰበ የሚያመላክት ሰልፍ ተድርጎ ነው የዛሬው የወታደራዊ ትዕንት የተወሰደው።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

” የማይሞቱት ጦርነት ይቀሰቅሳሉ” ሲል የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጦርነት እናቶችን ይገላል። ህጻናትን ይገላል። አዛውንቶችን ይገላል። ንብረት ያወድማል ሲሉ ህዝብ ሞት እንዳያገኛቸው ቤተሰቦቻቸውንና ራሳቸውን ሸሽገው ሊያጫርሷቸው የጦርነት እሳት ውስጥ ከሚከቷቸው ሁሉ ራሱን እንዲጠብቅ መምከራቸው አይዘነጋም። ይህንንም ያሉት ደጋግመው ነው።

የትግራይ ክልልን የሚያስተዳድረው ህወሃት ክልሉን ያለ አንዳች ጣልቃ ገብነት በነጻነት እየመራ ባለበት በአሁኑ ሰዓት ከፌደራል መንግስትና የሚጣላበትና ጦርነት ውስጥ ገብቶ የትግራይን ሕዝብ ችግር ውስጥ የሚከትበት ምክንያት ግልጽ እንዳልሆነለት መብርሃቶም ገደይ ለዛጎል አስተያየቱን ሰጥቷል።

የስዊዲን ነዋሪው እንዳለው የትግራይ እናቶች ዛሬም ሰባ ሺህ ልጆቻቸውን ለማን ነው የሚገብሩት? ሲል ጠይቋል። እንደ እሱ አስተያየት ውይይት ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል።

በሌላ ዜና የቀድሞ የህወሃት ጀነራሎች ጉዳዩን ለማርገብና ወደ ሰላማዊ መንገድ ለመውሰድ እየሰሩ መሆኑን ዛጎል ሰምታለች። የመኮንኖችህንና የነባር ከፍተና አመራሮችን ስም መጥቀስ አግባብ ስላልሆነ አንጂ እነዚህ ክፍሎች ችግሮችሁ በስለማ እንዲያልቁ እየሰሩ ነው።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

ይህ በንዲህ እንዳለ በሰሜን የመከላከያ ሰራዊት የመዋቅር መልሶ ማዋቀር መጠናቀቁ ታውቋል። ዛጎል ባገኘችው መረጃ መሰረት በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር ያለው ሰራዊት ከላይ እስከታች አመራሩ ተቀይሯል። የዕዝ ሰንሰለቱና የግንኙነት መስመሩ በአዲስ ተተክቷል።

ኢትዮጵያና ኤርትራ የወታደራዊና የደህነት የጋራ ስምምነት መፈራረማቸው የሚታወስ ነው። ይህንን ስምምነት ህወሃት አጥብቆ የሚቃወም ሲሆን መንግስት ግን ከአጎራባች አገሮች ጋር የሚከተለው ፖሊሲ እንጂ ህወሃትን ለይቶ የሚያስፈራው ምንም ምክንያት እንደሌለ ይገልሳል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *