ኤርትራ በረሃ የነበረውን ጦ በትግራይ በኩል ለከው እሳቸው በአዲስ አበባ ወደ አገራቸው የገቡት ዳውድ ኢብሳ ደጋፊም ተቃዋሚም አላቸው። ከሁለቱም ያልሆኑት ደግሞ በሚዲያ የነገሱ በተግባር የውዳሴውን ያህል የማይመዝኑ መሆናቸውን ይገልጻሉ።

ሰሞኑንን በቁም እስር ላይ መሆናቸው ከተነገረ ወዲህ የሚወዷቸው ” ዳውድ እንዴት ሆኑ” በሚል ጆሮ ተክለው ዜናቸውን ሲከታተሉ የማይደግፏቸው ደግሞ “ኦነግ ለምን በአዲስ አመራር አይተካም?” ሲሉ የሰነበተ ጥያቄያቸውን እያነሱ ነው። እግርመንገዳቸውንም የዳውድ የሁለት አስር ዓመታት የመሪነት ጉዞ ኦነግን ሰነጣተቀው እንጂ ምንም ያተረፈው ነገር የለምና ወቅቱን እንደ መልካም አጋታሚ መውሰድ አስፈላጊ መሆኑንን እየተናገሩም ነው።

አቶ ዳውድን የሚወዱትም ሆኑ ” በቃዎት” የሚሉዋቸው ወገኖች የየራሳቸው መከራከሪያ ቢያቀርቡም ፈራጃና ይህንኑ ሃሳብ ገሃድ አውጥቶ የሚያሟግት ሚዲያ አለመገኘቱ ጉዳዩን የጭፍን ፍቅርና ጥላቻ እንዳስመሰለው በርካታ ገለልተኞች ይገልጻሉ። እናም እንዲህ ያሉ መሃል ላይ ቆመው ለህዝብ ቅድሚያ የሚሰጡ ሚዲያዎች አስፈላጊ የሆኑበት ደረጃ ላይ መደረሱንም ያጠቁማሉ።

በኦሮሞ ጉዳይ ላይ አተኩረው የሚሰሩ ሚዲያዎች አፈጣጠራቸው ከትግል ጋር ተያይዞ መሆኑ  ነጻ ሆነው ህዝብን እንዲያገለግሉ አያስችላቸውም የሚሉ ወገኖች ነጻ፣ ገለልተኛና ህዝብን ማዕከል ያደረጉ መገናኛዎች አሁን ካሉት የትግል ሚዲያዎች በተጨማሪ ያስፈልጋሉ ባይ ናቸው።

ዛሬ በኦነግ ቢሮና በአቶ ዳውድ ኢብሳ መሪነት ጉዳይ እየተድበሰበሰ የሚታለፈው ጉዳይ የገለልተኛ ሚዲያ ችግር ነጸብራቅ መሆኑንን ባለሙያዎች ያሰምሩበታል። ህዝብን ማእከል አድርገው የሚሰሩ ሚዲያዎች ቢኖሩ ኖሮ የኦነግ አመራሮች አርጅተውና ጡረታ በመውጫ ጊዜያቸው ” እሳት የሆነውንና የተማረውን ትውልድ እድሜ ልክ እንምራህ አይሉትም ነበር”

በዚህ መነሻ የዳውድ ኢብሳን ዜናዎች የሚገመግሙት ለዘብተኛ የክልሉ ተወላጆች ” ዳውድ ኢብሳ ራሳቸው ስብሰባ ጠርተው በቃኝ በማለት ድርጅቱን ለወጣቶች በክብር አስረክበው የክብር ማዕረግ አግኝተው ሊኖሩ ይገባል” ሲሉ የሚደመጠው። ሽግግር ያካሂዱ ሲሉ ሃሳብ ሲሰጡም አብዛኛው የድርጅቱ አመራሮች ይህንኑ እርምጃ ሊከተሉና ሊደግፉ እንደሚገባ በማመን ጭምር ነው። ይህ አስተያተ የተሰማው አቶ ዳውድ ወደ ቢሯቸው በመግባት ስራ ማከናወን ጀመሩ የሚል ዜና እስኪሰማ ነው። ዜናው ከተሰማ በሁዋላም ክርክሩና እየተድበሰበሰ የሚቀርበው የህገወጥ ስብሰባ ጉዳይና የሳ

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

አቶ ዳውድ ቢሯቸው ከገቡ በሁዋላ ለቢቢሲ የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር መሩት የተባለው ስብሰባ መደረጉን እንደማያውቁ ተናግረዋል። ከግንኙነት ውጪ ስለነበሩ ምን እንደተደረገ መረጃ እንደሌላቸው አመልክተዋል። ለአሜሪካን ድምጽ ሬዲዮም ” በቁም ታስረዋል” ከተባሉበት ቤት ሆነው በተመሳሳይ ያለ እሳቸው እውቅና ስብሰባው መደረጉን አመልክተዋል።

በስፋት ከሃላፊነታቸው ተነስተዋል መባሉ፣ በድርጅቱ ጥላ ውስጥ ያሉ አመራሮች እርስ በርስ የሚጣላ መረጃ መስጠታቸው ግራ የሚይጋባ ቢሆንም፣ አቶ ዳውድ ኢብሳን እንዲተኩ ተመርጠዋል የተባሉት አቶ አራርሶ ቢቂላ “ዜናው ፍጽም ሐሰት ነው” አስተባብለዋል። አቶ አራርሶ ስብሰባው በሳቸው እውቅናና ምክክር መሰረት የተካሄደ መሆኑን ለቪኦኤና ቢቢሲ አስረግጠው ቢናገሩም አቶ ዳውድ ደጋግመው “የማቀው ነገር የለም” ሲሉ መልሰዋል። ማን ይታመን?

“አሁን ገና ነው የማጣራው፤ የፓርቲውን አመራሮችም ሆነ አባላት የዕለት ተዕለት ሥራዎችን በጥሞና የሚከታተል በጉባዔ የተመረጠ የሕግ ቁጥጥር ኮሚቴ አለ። የእነሱን ውሳኔ ጠብቆ በእነሱ ትዕዛዝ መንቀሳቀስ የድርጅቱ ግዴታ በመሆኑ እርሱን እጠብቃለሁ” ሲሉ አቶ ዳውድ ተካሄደ ስለተባለው ሹም ሽርና ስብሰባ ተጠይቀው መልስ ሰጥተዋል። ይህ የሰሞኑንን ብዥታ አስመልክቶ የሰጡት የመጨረሻው ቃል ነው። ይህንንም ያሉት ለቢቢሲ ነው።

ደህንነታቸውን አስመክቶ ፍርሃቻ እንዳለባቸው ሳይሸሽጉ የተናገሩት አቶ ዳውድ ከአማራ ክልል አመራሮችና ከሃጫሉ ድንገተኛ ግድያ በሁውላ የሚሆነው ስለማይታወቅ ይህንኑ ከግንዛቤ ከተው እንደሚንቀሳቀሱ የሚገልጹት አቶ ዳውድ “ስልኬ እንዲቋረጥ መደረጉን የደኅንነት ጉዳይ አድርጌ አልወሰድኩትም። ለሌላ ኦፕሬሽን እንደወሰዱት ነው የተረዳሁት። እነዚህ ሁለቱ ይገናኛሉ ብዬ ማመን ትንሽ ያስቸግረኛል፤ ነገር ግን ሊገናኙም ላይገናኙም ይችላሉ። ማወቅ አይቻልኩም” ሲሉ በተደጋጋሚ በሚቀርቡበት ቢቢሲ ሁለት እርስ በርሱ የሚምታታ ሃሳብ ሰንዝረዋል። አያይዘውም “ብዙ ጊዜ እየተደጋገሙ የሚመጡ ማስፈራሪያዎች፣ ማስረጃ መስሎ የሚመጣ ወሬ አለ። የዚህ ዓይነት መረጃ ተደጋግሞ ስለሚመጣ ትኩረት አልሰጠሁትም፤ ይህንን ፈርቼም ሥራዬን አላቆምኩም” በማለት ስጋታቸውን አክለዋል። ይሁን እንጂ ማስፈራራቱ ከየትናው ወገን እንደሆነና በምን መነሻ እንደሆነ ቢቢሲ አልጠየቃቸውም።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

ይህ ሁሉ ከሆነ በሁዋ ዛሬ የጀርመን ድምጽ አዲስ ዜና ይዞ ወጥቷል። በዘገባው አቶ ዳውድ በድጋሚ በጸጥታ ሃይሎች ከቢሯቸው ወደ መኖሪያ ቤታቸው እንዲመለሱ ተደርጓል። ዜናው የጠቀሳቸው የግንባሩ ቃል አቀባይ በማብራሪያቸው መጨረሻ ” አቶ ዳውድ ኢብሳ  ወደ መደበኛ ስራቸው ሲመለሱ ሁሉም ነገር በንግግር ይፈታል” ሲሉ በኦነግ ውስጥ ችግር ስለመኖሩ መረጃ ሰትተዋል። ዛጋቢው በንግግር ይፈታል የተባለው ችግር ምን እንደሆነ ግን ጠልቆ አልጠየቀም።

የጀርመን ድምጽ ሙሉ ዘገባ እንደሚከተለው ይነበባል።

ከቀናት ቆይታ በኋላ ወደ ጽህፈት ቤታቸው ተመልሰው የነበሩት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በድጋሚ በጸጥታ ኃይሎች ወደ ቤታቸው መወሰዳቸውን ግንባሩ አስታወቀ።

አቶ ዳውድ በጸጥታ ኃይሎች ተገደው ወደ ቤት እንዲመለሱ የተደረጉት «ለደህንነታቸው ሲባል ነው» የሚል ምላሽ ማግኘታቸውን የግንባሩ ቃል አቃባይ ቀጄላ መርዳሳ ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል።

የግንባሩ ሊቀመንበር በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ጥብቅ ቁጥጥር ስር መሆናቸው በዕለት ተዕለት ስራቸው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩንም አቶ ቀጄላ ተናግረዋል።«ባለፈው ጊዜም እንደተነገረው  ከእርሳቸውም አንደበትም የሰማነው ለደህንነታቸው ተብሎ ነው ።

ነገር ግን ይሄ ጉዳይ በስራቸው ላይ ቢሮአቸው ለመሄድ ተጽዕኖ አለው»ቀደም ሲል የግንባሩ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ባልተገኙበት በተወሰኑ የስራ አስፈጻሚ እና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት አማካኝነት ተከናውኖ የነበረው ስብሰባ ዓላማውን ባልተረዱ ሰዎች የስም ማጥፋት ዘመቻ ተካሂዶበት በግንባሩ ላይ ብርቱ ጉዳት ማስከተሉን አቶ ቀጄላ ተናግረዋል።«አሁን ከስብሰባው ጋር በተያያዘ በተፈጠረው ውዥንብር ብዙ ጥፋት ተከስቷል።

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

መጠነ ሰፊ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ሲከፈት ነበር። በስብሰባው ላይ የተሳተፉትን ሁሉ በጠላትነት የመፈረጅ ስራ ዎች ሀገር ባሉ በግንባሩ አባላት እና ደጋፊዎች ሲከናወን ቆይቷል። «አንዳንድ ሰዎች የሚጽፉትን እያየን ነው በጣም አጥፊ ተግባር ነው  አቶ ዳውድ ኢብሳ  ወደ መደበኛ ስራቸው ሲመለሱ ሁሉም ነገር በንግግር ይፈታል” ብለዋል አቶ ቀጄላ ፡፡

አያይዘውም  አቶ ዳውድ ኢብሳ ዛሬ ወደ መኖርያ ቤታቸው ከተወሰዱ በኋላ ከግንባሩ ምክትል ሊቀመንበር አራርሶ ቢቂላ ጋር መወያየታቸውን ቃል አቃባዩ ተናግረዋል።ዶይቼ ቨሌ ዛሬ ከሰዓቱን ጉለሌ ከሚገኘው የግንባሩ ጽህፈት ቤት አከባቢ እንደተመለከተው በቢሮው መግቢያ በር ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ተቀምጠው ከመጠበቃቸው ውጭ ምንም እንቅስቃሴ አላስተዋለም፡፡ የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ስዩም ጌቱ በአቶ ዳውድ ስልክ ላይ ደውሎ ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ተጨማሪ መረጃ ለመጠየቅ ያደረገው ሙከራ  የእጅ ስልካቸው ባለመስራቱ ሳይሳካ ቀርቷል።


ዛጎል ዜና ለአንባቢያን ሲባል ማስታወቂያ የማትቀበል፤ አድማስዋን አስፍታ መረጃ ለማድረስ እየሰራች ያለች ገለልተኛ ሚዲያ ናት። ድግፍዎን ይስጡን፣ ይጻፉ፣ በአገርዎ ጉዳይ ባይተዋር አይሁኑ 


 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *