እንደተለመደው የአዋሽ ወንዝ ሞልቶ በአፋር ክልል 32 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸው ተሰማ። የዘንድሮ ክረምት ጠንካራ በመሆኑ የተፈናቃዮች ቁጥር ከጥፍ በላይ ሊጨምር እንደሚችል ተመልክቷል። የግልገል ጊቤ ቁር 3 የሃይል ማመንጫ ከሚጠበቀው በላይ ውሃ በመያዙ ወደፊት ሊያስከትል ከሚችለው አደጋ ለመጠንቀቅ ውሃ መልቀቅ እንደሚጀመር ይፋ አድርጓል።
የአዋሽ ወንዝ ሞልቶ በአፋር ክልል ተለያዩ ወረዳዎች 32 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋሰትና ማስተባባሪያ ጽህፈት  የቅድመ ማስጠንቀቂያና ፈጣን ምላሽ ዳይሬክተር አቶ አይዳሂስ ያሲን ናቸው የተናገሩት።
ዳይሬክተሩ እንዳሉት በክልሉ በአዋሽ ወንዝ ዳርቻ የሚገኙ 7 ወረዳዎች ከፍተኛ የጎርፍ ስጋት ተጋላጭ ናቸው።  ይህን ችግር ለመቅረፍ የአዋሽ ተፋሰስ ባለስልጣን ከሚመለከታቸው የፌዴራልና የክልሉ መንግስት አካላት ጋር በመቀናጀት የጎርፍ መከላከል ስራዎች ሲያከናውን ቢቆይም የዘንድሮው ክረምት ጠንከር ያለ በመሆኑ በ6 ወረዳዎች የጎርፍ አደጋ አጋጥሟል ።
ጎርፉን ተከትሎ በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት ባይኖርም 32 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውንና ግምቱ በመጣራት ላይ የሚገኝ ሰብልና እንስሳት ላይ ጉዳት ማድረሱን ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።
ከተፈናቃዮች መካከል 17 ሺህ 450 ሰዎች በአይሳኢታ ወረዳ የ5 ቀበሌ ነዋሪዎች ናቸው። ኢዜአ እንደዘገበው እስከ አሁን ድረስ በአይሳኢታ ወረዳ በጎርጉም ሁለት ቀበሌዎች ለሚገኙ ከ1 ሺህ100 በላይ ሰዎች የፌዴራል መንግስት በሄሊኮፕተር ምግብ የማቅረብ ስራዎች በማከናወን ላይ ነው።
ለጊዜው ክልሉ የምግብና ምግብ-ነክ የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ በማድረግ የህይወት አድን እርዳታ ለማቅረብ እየሞከረ ቢሆንም ከችግሩ ስፋትና አሳሳቢነት አንፃር የፌዴራል መንግስት እገዛ መጠየቁን አቶ አይዳሂስ ተናግረዋል ።
በመሆኑም ከሰላም ሚኒስቴርና ከሚመለከታቸው የፌዴራል አካላት ጋር በመተባባር ከዛሬ ጀምሮ በሄሊኮፕተር አስቸኳይ የምግብ አቅርቦት ስራዎችን ለማከናወን ዝግጅት መደረጉን አስረድተዋል ።
በውሃ የተከበቡት ሰዎች በሔሊኮፕተርና በሞተር ጀልባ በማውጣት ወደ ሌላ አካባቢዎች ለማስፈር የሚያስችል ዝግጅት መደረጉንም አስታውቀዋል።
በአፋር ክልል በታችኛውና መካከለኛው አዋሽ 63 ሺህ ሰዎች የጎርፍ አደጋ ተጋላጭ ናቸው። ከ44 ሺህ የሚልቁ ሰዎች ደግሞ ሰዎች ደግሞ በመፈናቀል ስጋት ላይ የሚገኙ ናቸው ተብሏል።
በተመሳሳይ ዜና ፋና እንዳስታወቀው  የጊቤ 3 የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ግድብ እየሞላ በመምጣቱ ውሃ በየደረጃው ለመልቀቅ የሚያስችል የሙከራ ስራ እንደተከናወነ ተገልጿል። ይህም ከግድቡ የሚለቀቀው ዉሃ ወደፊት በታችኛው ተፋስስ ላይ ጎርፍ እንዳያስከትል ለመቆጣጠር እና ውሃውን በተመጠነ መልኩ በመልቀቅ በክረምቱ መጨረሻ ላይ ግድቡ ሙሉ እንዲሆን ለማድረግ መሆኑን የጣቢያው ስራ አስኪያጅ አቶ ሃብታሙ ሰሙ ገልፀዋል፡፡

ውሃ ከግድቡ በየደረጃው እንዲለቀቅ መደረጉ በተፋሰሱ ውስጥ የጎርፍ መቆጣጠር ስራ ለማከናወን እንደሚያግዝም ጠቁመዋል፡፡ ግድብ የመጣውን ጎርፍ ሁሉ እንደመጣ ላለመልቀቅና የተመጠነ የውሃ ፍሰት እንዲኖር ለማድረግም በየጊዜው እየተቆጣጠሩ መልቀቅ ክረምቱ ሲጠነክር ሊከሰት የሚችለውን ጎርፍ ለመቆጣጠር እንደሚያግዝ አስረድተዋል፡፡

Related stories   አቡነ ማቲያስ መነጋገሪያ ሆነዋል - ኢትዮጵያ ላይ ዘመቻው እንዲከር ጥሪ አቅርበዋል

አቶ ሃብታሙ ግድቡ መያዝ ከሚችለው 15 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ውሃ ውስጥ 12 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ውሃ የያዘ ሲሆን በሴኮንድ በአማካኝ 800 ሜትር ኪዩብ ውሃ ለመልቀቅ እቅድ ተይዟል፡፡

ግድቡ ባለፈው ዓመት ህዳር ወር ከባህር ጠለል በላይ 882 ሜትር ላይ በመድረስ ከፍተኛ ውሃ መያዝ የቻለ ቢሆንም አሁን ላይ ግን ከዚህ መጠን ጋር ተመሳሳይ ውሃ መያዙን ተናግረዋል፡፡

Related stories   ምርጫውን ለማደናቀፍ ያሴሩ አካላት ህልማቸው አይሳካም – አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከሦስት ወር አስቀድሞ ከባህር ጠለል በላይ 892 ሜትር ላይ በመድረስ ሊሞላ እንደሚችል ያመለክታል፡፡

ውሃው ከአሁኑ ካልተለቀቀ ነሐሴ 4 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ሙሉ በሙሉ ሊሞላ እንደሚችልም ስራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡

ግድቡ አሁን ሳይለቀቅ ቆይቶ ከሞላ በኋላ የሚለቀቅ ከሆነ ከላይኛው የጊቤ ተፋሰስ የሚመጣውን ጎርፍ ሁሉ ለመልቀቅ ስለሚያስገድድ በታችኛው ተፋሰስ ላይ የጎርፍ መጥለቅለቅ ሊያስከትል ይችላል ብለዋል፡፡

Related stories   የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አገር ለማተራመስ በህቡዕ የተደራጁ በርካታ ግለሰቦችን ከነመዋቅራቸውና መስሪያዎቻቸው በቁጥጥር ስር አዋለ፤

ይሁንና የግድቡ ውሃ በየቀኑ እየጨመረ ስለሚሄድ ውሃ የመልቀቅ ሂደቱን ቀስ በቀስ መጥኖ በማከናወን ከግድቡ በታችኛው ተፋሰስ በሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ አደጋ እንዳያስከትል እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡

ግድቡ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ውሃ ሲለቅ የመጀመሪያው ሲሆን የውሃ መልቀቅ ሂደቱ እስከመቼ ሊቆይ እንደሚችል የታወቀ ነገር እንደሌለ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል አስታውቋል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *