ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የ26 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 583 ደግሞ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል

ሚኒስትሯ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ እንዳሰፈሩት በ24 ሰዓታት 6 ሺህ 907 የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተደርጎላቸው 583 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

በዚህም በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 19 ሺህ 289 ደርሷል። እንዲሁም በቫይረሱ ምክንያት ባለፉት 24 ሰዓታት የ26 ሰዎች ሲያልፍ በዚህ በሀገሪቱ በቫይሩ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 336 መድረሱን ነው ሚኒስትሯ ያስታወቁት።

በአሁን ወቀት በሀገሪቱ 145 ፅኑ ህሙማን የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝም ተነግሯል። በሌላ በኩል በ24 ሰዓታት ወስጥ 330 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል።

ታራሚዎች፣ ፖሊሶች እና ስደተኞች ጭምር በኮሮና ተይዘዋል

በድሬደዋ የኮሮና በሽታ ስርጭት አሁን ባለበት ደረጃ ከፍተኛ ስጋት እየሆነ መምጣቱን የመስተዳድሩ ጤና ቢሮ አስታወቀ። የበሽታውን ስርጭት ለመከላከል አስገዳጅ መመሪያዎችን ማስተግበር እና የእንቅስቃሴ ገደብ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አንድ የጤና ባለሞያ ተናግረዋል።

የድሬደዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ይዘሮ ለምለም በዛብህ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት በህብረተሰቡ ዘንድ እየታየ ባለው መዘናጋት የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እየጨመረ መምጣቱንና ድሬደዋ ከአዲስ አበባ ቀጥሎ ከፍተኛ ስጋት ያለባት ከተማ ሆናለች።

Related stories   ሲሲሊ፥ ለወሲብ በባርነት የሚሸጡ ሴት ናይጄሪያውያን

በአስተዳደሩ አቅም በፈቀደ መልኩ እየተካሄደ ባለው የኮቪድ ምርመራ ቫይረሱ እየተገኘባቸው ካሉ የህብረተሰቡ ክፍሎች አብዛኞቹ ወጣቶች መሆናቸውን ኃላፊዋ አስረድተዋል።

የጤና ባለሞው ዶክተር አቤል መልካሙ ለዶይቼ ቬለ በስልክ  በሰጡት አስተያየት “የመመርመር እቅም ዝቅተኛ መሆን እንጂ ቁጥሩ ከዚህም ሊልቅ እንደሚችል” ጠቅሰው መደረግ አለበት ያሉትን አስተያየት ሰተዋል።

ፖሊስ ጣቢያዎች እና ማረሚያ ቤት የኮሮና ስርጭት ስጋት ናቸው መባሉን በሚመለከት ጥያቄ የቀረበላቸው የጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በፖሊስ ጣቢያዎች የጥንቃቄ አሰራር ስራ ላይ እንዲውል መደረጉን ገልፀው በማረሚያ ቤት ተመሳሳይ ችግር እንዳይፈጠር እየተሰራ ያለውን ስራ ጠቁመዋል።

በአስተዳደሩ እስካሁን የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው አምስት መቶ ሰባ አምስት ሰዎች አስራ አምስቱ ህይወታቸው ማለፉን፤ አራት መቶ ሃያ አምስት የሚሆኑት አገግመው መውጣታቸውንና  በአሁን ሰዓት አንድ መቶ ሰላሳ ሶስት የሚሆኑ ሰዎች በተለያዩ ህክምና ማዕከላት ውስጥ መኖራቸውን ወ/ሮ ለምለም በሰጡት መግለጫ አብራርተዋል፡፡

DW

ጀርመን ሁለተኛ ዙር የኮሮና ተኅዋሲ ስርጭትን እየተጋፈጠች ነዉ ሲል አንድ የጀርመን የሐኪሞች ሕብረት አስጠነቀቀ። ነዋሪዉ ለኮሮና ተኅዋሲ ስርጭት መገታት የማኅበራዊ ርቀትን እና ጥንቃቄዉን ቸል ባለበት በአሁኑ ወቅት ሃገሪቱ ዉስጥ ሁለተኛ ዙር የኮሮና ወረርሽኝ ሞገድ እየታየ ነዉ፤ ምናልባትም አደጋዉ ከዚህ ቀደም ከነበረዉ የጠነከረ እና የከፋ ሊሆን ይችላል ሲል ማኅበሩ አሳስቦአል።

Related stories   ሲሲሊ፥ ለወሲብ በባርነት የሚሸጡ ሴት ናይጄሪያውያን

ባለፈዉ ሳምንት በጀርመን በኮሮና ተኅዋሲ የሚያዘዉ ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ከታየ በኋላ ምሁራን የኮሮና ስጭትን ለመግታት ነዋሪዉ አካላዊ ርቀትን እና የእጅን ንጽሕና እንዲጠብቅ እንዲሁም የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛን እንዲያደርግ በድጋሚ ጥሪ ማድረግ መጀመራቸዉ ይታወቃል።

በዓለም የኮሮና ተኅዋሲ መረጃ መዘርዝር መሰረት በጀርመን ባለፉት 24 ሰዓታት ዉስጥ ብቻ 509 ሰዎች በኮሮና መያዛቸዉ ተረጋግጦአል። በአሁኑ ወቅት በጀርመን በአጠቃላይ ከ 211 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮና ተይዘዋል። ኮሮና ባስከተለባቸዉ ሕመም እስካሁን 9226 ሰዎች ደሞ ሞተዋል።

DW

ኮሮናቫይረስ፡ ሳይታወቅ ለዓመታት በሌሊት ወፎች ውስጥ ነበር

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ፍቱን መፍትሄ ላይኖር ይችላል- የአለም ጤና ድርጅት

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ፍቱን መፍትሄ ላይኖር እንደሚችል የአለም ጤና ድርጅት አሳሰበ።የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በበይነ መረብ በሰጡት መግለጫ ለቫይረሱ በአሁን ወቅት ፍቱን መፍትሄ የለም ወደፊትም ላይኖር ይችላል በማለት ተናግረዋል።
 
ይህ ሀሳብ የመጣው ድርጅቱ የኮሮና ቫይረስ ለረጅም ጊዜ ሊቆይ ይችላል ሲል ካስጠናቀቀ በኋላ ነው። ሆኖም በዓለም እየተካሄደ የሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ክትባት ሙከራ ቫይረሱን ለመከላከል ሊረዳ ይችላል ሲል ቢቢሲ በዘገባው አስፍሯል። የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ በሙከራ ላይ የሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ክትባት በሽታ የመከላከል አቅምን ያሻሽላል ሲል ማሳወቁ የሚታወስ ነው።

እናቶች  በኮሮና ቫይረስ ቢያዙም ልጆቻቸውን ጡት ማጥባት  አለባቸው-የዓለም የጤና ድርጅት

አዲስ የተወለዱ ሕፃናትን ወይም ልጆችን ጡት ማጥባት የሚሰጠው ጥቅም  የኮቪድ 19 በሽታ ከሚያመጣው ስጋት እጅግ የላቀ  በመሆኑ እናቶች  በኮሮና ቫይረስ ቢያዙም ልጆቻቸውን ጡት ማጥባት አለባቸው ሲል  ዓለም  አቀፉ የጤና ድርጅት ገልጿል።

Related stories   ሲሲሊ፥ ለወሲብ በባርነት የሚሸጡ ሴት ናይጄሪያውያን

የዓለም  አቀፉ የጤና ድርጅት ኃላፊ ዶክተር ቴድሮስ  አድሃኖም ÷ምንም እንኳን እናቶች በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ቢያዙም ልጆቻቸውን  ጡት ማጥባታቸው ለህጻናቱ  የሚሰጠው ጥቅም በሽታው ከሚያስከትለው ጉዳት ከፍ ያለ  መሆኑን ተናግረዋል።

ሃላፊው ይህንን የተናገሩት በዓለም  አቀፍ ደረጃ የጡት ማጥባት ግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንት በተከበረበት ወቅት ሲሆን ÷ በኮቪድ- 19 በሽታ የተጠረጠሩ ወይም መያዛቸው የተረጋገጠ  እናቶች እንደሌሎች እናቶች ሁሉ   ህጻናት ልጆቻቸውን ጡት ማጥባት እንዲቀጥሉ መበረታታት አለባቸውም  ብለዋል።

አዲስ ለተወለዱ ሕፃናት እና ልጆች ጡት ማጥባት የሚሰጠው ጥቅም  በኮቪድ-19 ኢንፌክሽኖች ከሚመጣው ስጋት እጅግ የላቀ ነውም ነው ያሉት።

ምንጭ፡-ሮይተርስ

#FBC
 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *