” ዛቻ አለ። ማስፈራራት አለ። እኔ ግን ላለፉት አስራ ስድስት ዓመታት ለራሴ ሞቼ ለሰው ልጆች መብት ስሟገት ነው ያሳለፍኩት። እናም ዛሬ ብሞት አዲስ ነገር የለውም። ከህሊናዬ ጋር መክሬ ከዛሬ አስራ ስድስት ዓመት በፊት በፊት የገባሁት ቃለ አለ። ያ ቃል ዛሬም በልቤ ነው። የብሄር አክቲቪስት መሆን አልችልም። ቃል ኪዳኔም አይደለም” ሲሉ አቶ ኦባንግ ሜቶ ለዛጎል አስታወቁ።

የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር ይህን ያስታወቁት እየተሰነዘረባቸው ያለውን ዛቻ አስመልክቶ ነው። አሁን ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት የጄኖሳይድ ፍኖተ ካርታ እንድትቀመጥ የሚያስችል ስራ መጀመራቸውን ማስታወቃቸውን ተከትሎ ስጋት የገባቸው ማስፈራራታቸውን ማተናከራቸውን አልሸሸጉም። ግን ይህን ፈርተው ከጀመሩት እንቅስቃሴ ወደሁዋላ እንደማይሉ አስረግጠው ተናግረዋል።

“ቃል ብቻ አይደለም” ሲሉ ኦባንግ ይፋ እንዳስታወቁት አሁን የጀመሩት ስራ በቅርቡ ምላሹ ይታያል። ” ቃል ብቻ አይደለም። ማንም እንደሚያውቀው ላለፉት አስራ ስድስት ዓመታት ከዩኤስ አሜሪካ ኮንገርስ አባላትና የሚመለክታቸው ተቋማት፣ ጀጄኖሳይድ ፎረም፣ ከአውሮፓ ህብረት፣ ከሰሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማት፣ ከዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት፣ በተመሳሳይ ከሚሰራው ከአፍሪካው ፍርድ ቤት … ስሰራ ኖሪያለሁ። አሁንም ከነዚሁ አካላት ጋር በስፋት እየሰራሁ ነው” ሲሉ እሳቸው ህይወታቸው ቢያልፍ እንኳን ስራው እንደማይቆም ገልጸዋል።

. “ኢትዮጵያ በተመድ የጄኖሳይድ ፍኖተ ካርታ እንድትሰፍር አየተሰራ ነው ፤ ጄኖሳይድ አልተካሄደም ማለት ከሰውነት ደረጃ መውረድ ነው”

የዛሬ አስራ ስድስት ዓመት 424 አኝዋኮች በማንነታቸው ተመርጠው ሲጨፈጨፉ 317 ያህሉን እንደሚያውቋቸው አቶ ኦባንግ በሃዘን ያስታውሳሉ። ሃዘኑም እጅግ እንደሚሰብር ይናገራሉ። አስተማሪዎቻቸው ፣ አጎቶቻቸው፣ የወንድማቸው ሚስት፣ ባልደረቦቻቸው፣ አብሮ አደጎቻቸውና የአካባቢያቸው ሰዎች መጨፍጨፋቸውን  ሲያስታውሱ እንደ ሰው የሁሉም ስም ዝርዝር እጃቸው በመግባቱ ዝርዝሩን እያዩ የተጨፈጨፉትን ንጹሃን ሲቆጥሩ የተሰማቸው ሃዘን አንድ ቃለ እንዲገቡ እንዳደረጋቸው ይናገራሉ።

Related stories   Egypt-Sudan alliance shifting in row with Ethiopia over Nile dam

” አንድም የሰው ልጅ በተመሳሳይ እኔ እንዳገኘሁት በማንነታቸው የተጨፈጨፉ ሰዎችን ማንነት የሚያሳይ ዝርዝር እንዳይደርሰው ለማድረግ ለዘር ሳይሆን ለሰው ልጆች ሁሉ የሰብአዊ መብት መከበር ለመታገል ወሰንኩ። ዛሬም እዛው ቃሌ ላይ ነኝ” ሲሉ የሚያስረዱት የአኢጋን ዋና ዳይሬክተር፣ ” በዚህ መሃላዬ ላይ ቆሜ የምሰራው ስራ ማንንም ለማስቀየም ሳይሆን ለእውነት ስል እንደሆነ እንዲታወቅ ” ሲሉ መልዕት አስተላለፈዋል።

በሃሰትና በመሸፋፈን ላይ ተመስርቶ መኖር ህሊና አለን ለሚሉ የሰው ልጆች የቁም ሞት እንደሆነ፣ በዚህ አይነት አስተሳሰብ መጓዝ የሚፈቅድ ህሊና ተሸክሞ መኖር በቁም ከመሞት ስለማይሻል፣ የሆነውን ሁሉ ግልጽ በማድረግ ወደ ዘላቂ መፍትሄ ማምራቱ አማራጭ የሌለው ብቸናው መንገድ መሆኑንን ኦባንግ አመልክተዋል። ከዘር እሳቤ መውጣትም እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

See the bigger picture: As tribalism is nothing other than animalism

በቅርቡ በሶማሌ ክልል አብዲ ኢሌና አለቆቹ የሰሩትን ዘግናኝ ግፍና መረጃ የተደበቀበትን ወንጀል፣ የጋሞ ተወላጆች ጋሞ ስለሆኑ ብቻ መገደላቸውን፣በመዠንገር፣ በበደኖ ወዘተ የተፈጸመውን ወደኋላ ተመልሰው በማስታወስ በተለያዩ ቦታዎች የተፈጸሙትን ዘር ላይ መሰረት ያደረጉ እልቂቶችን ነቅሶ ፍትህ እንዲወርድ፣ በፍትህ አካሄዱ ላይ ዓለም ዓቀፍ ተቋማት እንዲሳተፉ መጠየቅ ማንንም የሰው ልጅ የሆነ ሁሉ ቅር ሊያሰኝ እንደማይገባ አቶ ኦባንግ ለዛጎል ተናግረዋል።

Related stories   “ትህነግ ከጁንታነትም ወርዶ በየጫካው ተሹለክላኪ የእህል ሌባ ሆኗል፣ ከያለበት እየታደነ ነው “ሜ/ጀ መሐመድ ተሰማ

እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ” ለምን ፍትህ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ እንዲጠየቅ ይሰራል” በሚል ማስፈራሪያና ዛቻ መሰራጨት እጅግ አስገራሚና ከባህላችን ያፈነገጠ ከመሆኑም በላይ የፍትህ ጸር ሆኖ የመሰለፍ ያህል በመሆኑ ሃሳቡን ኮንነውታል።

” አልፈራም። የሚያስቆመኝም ሃይል የለም። ለሰው ልጆች ተሰብአዊ መበት መከበር እንደመታገል ኅሊናን የሚያስደስም ነገር የለም” ያሉት ኦባንግ ” ይህን በማድረጌ ለሚመጣው ሁሉ ማናቸውንም ዓይነት መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነኝ። እየኖርኩም ሞቼ ስከፍለው ኖሬያለሁ” ሲሉ አቋማቸውን ይፋ አድረገዋል።

በቅርቡ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንና ከሰላም ሚኒስትሯ ጋር በነበራቸው ውይይት ጥበቃ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ተነግራቸው እንደነበር ያስታወቁት ኦባንግ ” እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ እንዳሻኝ ብቻዬን ነው ስንቀሳቀስ የነበርኩት፣ ወደ ክልልላቸን ትመጣ እንደሆ ዋ የሚለው ዛቻና ዓለም በፍትህ ስርዓቱ እንዲገባ መጠየቁ ይፋ ከሆነ በሁዋላ ዛቻው ማየሉ መንግስት ካመነበት ጥበቃ እንዲደረግላቸው የቀረበውን ሃሳብ አጤነዋለሁ” ከዛ በላይ ግን በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ያላቸ እምነትና ድጋፍ ነጻነት እንዲሰማቸው ማድርጉን አብራርተዋል።

ፍርድ ቤቱ በእነ አቶ ጃዋር ሲራጅ መሀመድ ላይ የቀዳሚ ምርመራ ሂደት እንዲቀጥል ብይን ሰጠ

በተያያዘ ዜና ሰሞኑንን በዘራቸው፣ በማንነታቸውና እምነታቸው ሳቢያ ተለይተው ጥቃት የተፈጸመባቸውን ዜጎች አስመልክቶ የአውሮፓ ህብረት ሙሉ መረጃ እንዳለው፣ ሌሎችም ታላላቅ አገራት በጉዳዩ ዙሪያ እየሰሩበት መሆኑን ታውቋል። የሶማሌ ምክትል ፐሬዚዳንት አቶ ሙስጣፊም በክልላቸው የተፈጸመውን ጭፍጨፋ ለዓለም ለማቅረብ የጀመሩት ስራ መጠናቀቁን የዛጎል ምንጮች ተናግረዋል።

Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

ይህ ሁሉ ተዳምሮ የዚህ ቀውስና የሴራ አካላ ዋና ተውናዮች ወደ ዓለም ዓቀፍ ፍርድ ቤት የሚቀርቡበት የህግ አግባብ እየተመቻቸ እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል። ማንም ሆን ማን የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በቀር ከዓለም ዓቀፉ ህግ እንደማያመልጥ የገባቸው ከስጋት የተነሳ ነገሩን እልማድበስበስ ቢሞክሩም እንደማይሳካ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ይገልጻሉ። መንግስትም ለዓለም አቀፍ የምርመራ ቡድኖች በሩን ሊከፍት ፈቃደኛነት ማሳየቱን እነዚሁ ክፍሎች ገልጸዋል።

 
 

Subscribe to our newsletter!

[newsletter_form type=”minimal” lists=”undefined” button_color=”undefined”]

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *