ሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ ለ35 ዓመታት በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ አገልግለዋል። አብዛኛውን ዕድሜ ዘመናቸውን ባሳለፉበት የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ በተለያዩ የሀላፊነት ቦታዎች ሰርተዋል። እሳቸው ይመሩት የነበሩበት ክፍልም የልማት አርበኛ ተብሎ እንዲሸለም አድርገዋል። ሆኖም ከአራት ዓመት በፊት ባልታወቀ ምክንያት ከሰራዊቱ ከተሰናበቱ በኋላ የግል ስራ እየሰሩ የሚገኙ የሀገር ባለውለታ ናቸው።

አዲስዘመን፡የለውጡንየሁለትዓመታትጉዞእንዴትይገመግሙታል?

ሌተናልጀነራልባጫ ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም በኋላ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዜጋ የሚፈልጋቸውና ሲመኛቸው የነበሩ በርካታ ለውጦች መጥተዋል። የለውጦቹ ዋና ምሰሶ ከሆኑት መካካል አንዱ ለዜጎች የሚሰጥ ክብር ነው። በለውጡ ለማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ የሚሰጥ ክብር ትልቅ ቦታ ይዟል። ይህ ክብር በአገር ውስጥም በአገር ውጭም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ጭምር የሚያካትት ነው።

በተለይ ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም በፊት የነበረው መንግስት አገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በውጭም ያሉትን ዜጎች እያሳደደ የሚያስር ነበር። በአንጻሩ ከለውጡ በኋላ ያለው መንግስት ዜጎችን አሳዶ ከማሰር ይልቅ ከእስር የሚያወጣ፣ ወደ አገራቸው የሚገቡበት ሁኔታ የሚያመቻች፣ በውጭ አገር የታሰሩ ዜጎችን ጭምር ከውጪ መንግስታት ጋር በመነጋገር ዜጎች አገራቸው ገብተው በክብር እንዲኖሩ አድርጓል። ዜጎች በአገራቸው ክብር የማያገኙ ከሆነ ደግሞ የትም አገር ክብር ማግኘት አይችሉም። ማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ይሁን መንግስት ስልጣኑ የሚመነጨው ከህዝብ ነው። ስለዚህ ለዜጎች ክብር የማይሰጥ መንግስት እሱ አምባገነን ነው። ከመጋቢት 24 ቀን በኋላ የተገኘው ለውጥ አንዱ ለዜጎች ክብር የሚሰጥ መንግስት መኖሩ ነው።

ሁለተኛው የለውጡ ትልቅ ፍሬ የዜጎች ነጻነት ነው። ነጻነት ማለት በአገር ያለ ስጋት የመኖር፣ ባለህ የፖለቲካ አቋም ችግር የማይደርስብህ፣የማትገለልበና በወንጀል የማትጠየቅ መሆንህ ነው።

ሶስተኛ የዴሞክራሲ ምህዳርን በማስፋት ረገድም ብዙ ለውጦች ታይተዋል። ድሮ ሲያሳስሩ የነበሩ ነገሮች አሁን መብትና ነጻነት ሆነዋል። ለአብነትም በአገር ውስጥ እንደጠላት ሲታዩ የነበሩ በርካታ ሚዲያዎችና የፖለቲካ ፓርቲዎች በአገር ውስጥ ገብተው እየሰሩ ይገኛሉ።

አራተኛው ከጎረቤት አገሮችም ጋር በስጋት ሳይሆን በወዳጅነት አብሮ መኖር ተችሏል። ለምሳሌ ከኤርትራ ጋር አሁን ያላትን መልካም ግንኙነት ማየት ይቻላል። በጥቅሉ ለውጡ በዲሞክራሲና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊና ተጨባጭ ለውጦችን አምጥቷል። እነዚህና ሌሎች በርካታ የሚጠቀሱ ለውጦች በሀገሪቱ መጥተዋል። ነገር ግን እነዚህ ለውጦች ማደግ አለባቸው፣የተጀመሩ መልካም ነገሮች ወደ ኋላ እንዳይመለሱ ጠብቆ ማስኬድ ያስፈልጋል።

ሌላው ገና ያለገኘናቸው ሌሎች አስፈላጊ ለውጦች አሉ። ለምሳሌ እኛ ስንዴ መለመን አይገባንም፤ ስንዴ እንዳንለምን ደግሞ መንግስት በምግብ እህል ራሳችንን የምንችልበት ሁኔታ መፍጠር አለበት።

በአጠቃላይ ለውጡ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈልገው፣ በርካታ መሰናክሎች ተደርገውበት እነዚህን መሰናክሎች ወደ ኋላ ያልመለሱትና ሊመልሱት የማይችሉ፣ አሁንም ዕድገቱን እየጨመረ የሚሄድ ነው። ለውጡ የህዝብ ፍላጎት ነው። ማንም ቡድን ተነስቶ ይህን ለውጥ አመጣለው ብሎ ያመጣው አይደለም። ይህ ለውጥ የመጣው ለውጡ እንዲመጣ የሚንቀሳቀስን ሀይል ህዝቡ በሚገባ ስለደገፈው ነው። ህዝቡ ይህ ለውጥ እንዳይመጣ ባይፈልግ ኖሮ ማንም ቡድን ለውጡን ሊያመጣው አይችልም ነበር።

አዲስዘመን፡የህዝቡየለውጥመሻትከምንየመነጨነውብለውያምናሉ?

ሌተናልጀነራልባጫ፡ ጭቆናው በቃኝ፣ በአገሬ መኖር አልቻልኩም፣በንብረቴ ማዘዝ ተስኖኛል፣ወጥቼ መግባት አልቻልኩም፣የፈለገ ሰው በፈለገበት ሰዓት ያስረኛል፣ ይገለኛል፣ ያሳድደኛል፣ በተሰደድኩበትም ጭምር ተከትሎ ያሳድደኛል። ይህ በአገሬ ላይ ሊሆን አይገባም በቃኝ ስላለና የህዝብን እንቢተኝነት በጠበጃ አፈሙዝም ማስቆም ስላልተቻለ ነው ይህ ለውጥ የመጣው። ይህ የህብረተሰብ

 ዕድገት ሳይንስ ነው። ህዝቡ እዚህ ደረጃ ላይ ባይደርስ ኖሮ ይህ ለውጥ አይመጣም። ስለዚህ ህዝብ ለውጥ መምጣት አለበት ብሎ ውሳኔ ላይ በመድረሱ ለውጡ መጥቷል ፤ ለውጡን ያመጣው መላው ህዝቡ ነው።

አሁን ያለውን የለውጥ አመራር ቤተ መንግስት ያስገባው ማንም ግለሰብ ወይም ቡድን ሳይሆን መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ነው። ለውጡ ከመጣ በኋላ ፖለቲከኛ፣ተንታኝ፣ ያልሆነ የለም። ያልተከፈተ የሚዲያ አይነት የለም። ያልተነገረ ፖለቲካዊ አቋም ሆነ አስተሳሰብ የለም። ስለዚህ ለውጡ እነዚህ ሁሉ ነገሮች አስተናግዷል።

አዲስዘመን፡– የአርቲስትሀጫሉንግድያናከግድያውጋርበተያያዘየተፈጠረውንብጥብጥናሁከትእንዴትያዩታል?

ሌተናልጀነራል ባጫ፡-ምንጊዜም ቢሆን ለውጥ ካለ ጸረ ለውጥ አለ። ምክንያቱም ለውጥ በሚባልበት ጊዜ መለወጥ ያልፈለገ ግን ደግሞ በለውጥ ፈላጊው ማዕበል ተደፍቆና ለውጡ የበላይነትን አግኝቶ ከመድረክ የወጣ አንድ ጸረ ለውጥ ሀይል ይኖራል። የለውጡ ቡድንና የጸረ ለውጡ ቡድን ፍትጊያ ለሀጫሉ ግድያ ምክንያት ሆኗል። ሀጫሉ ለውጡን ካመጡት፤ ለውጡ እንዲመጣ ካቀነቀኑት፣ከታገሉት ሰዎች የመጀመሪያው ረድፋ ላይ የሚሰለፍ ነው።

ሀጫሉ በለውጡ የመጀመሪያ ረድፍ ላይ የሚሰለፈው በዘፈኑ ሳይሆን በድፍረቱ ነው። ዘፈን ማንም ዘፍኗል። ሀጫሉ ይነገራሉ ተብሎ የማይታሰቡ፤ ለሰዎች እንግዳ የሆኑ አቋሞችን መድረክ ላይ ያወጣ ነው። በዚያን ዘመን ያንን አቀንቅኖ ሀጫሉ ከመድረክ ወርዶ በሰላም ያድራል ብሎ ማሰብ ከባድ ነው። ሀጫሉ ይህን ልዩ ባህሪ ያላበሰው ውስጣዊ ፍላጎቱ፣ ድፍረቱና ጀግንነቱ ነው። ስለዚህ ለውጥ ለማምጣት በዚህ መልኩ ሲታገል ይህ ጸረ ለውጥ ሀይል ደግሞ ይህን ለውጥ ወደ ኋላ ለመመለስ በሚደርገው ትግል ሀጫሉ ተሰውቷል።

አዲስዘመን፡– ሀጫሉግድያዓላማውምንድነውይላሉ?

ሌተናልጀነራል ባጫ፡- ይህን ለውጥ ወደ ኋላ ለመመለስ የተደረጉ ጥረቶችን ለመገንዘብ ሶስቱን ሰኔዎችንና ሌሎች ክስተቶችን ወደ ኋላ እናስታውሳቸው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም ቦንብ ሳይወረወርባቸው ገና እንደተመረጡ መፈንቀለ መንግስት እንዲደረግ የአገር መከላከያ ጠቅላይ ኢታማጆር ሹሙን ሲጎተጉቱ ነበር። ኢታማጆር ሹሙ ያንን አላደረጉም።

ሌላው በ2010 ዓ.ም ሰኔ ወር ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለመግደል ቦንብ ተወረወረ። ቀጠለና 2011 ዓ.ም መግቢያ ላይ ቡራዩ ላይ ግርግር ተፈጠረና ከዚያ በኋላ ኮማንዶ የደመወዝ ጥያቄ እጠይቃለሁ ብሎ ቤተ መንግስት ገባ። ኮማንዶዎቹ ቤተ መንግስት የገቡት የደመወዝ ጥያቄ ለመጠየቅ ሳይሆን ለመፈንቀለ መንግስት ነው። ቡራዩ ላይ የተፈጠረው አሳዛኝ ክስተት በአራት ወራት ውስጥ ተመልሰን ቤተ መንግስት እንገባለን ተብሎ የተደረገ ነው። ይህን ሁሉ የሚያደርገው በጸረ ለውጡ ነው። ይህም አልተሳካም። ስለዚህ በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች የተፈጠሩት የጸጥታ ችግሮች በጸረ ለውጡ ቡድን የተቀነባበሩ ናቸው።

ስለዚህ ከሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም በፊት መፈንቀለ መንግስት ተሞከረ፣ ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም ቦንብ ተወረወረ፣ ቡራዩ በተከሰተው ችግር መፈንቀለ መንግስት ለማድረግ ኮማንዶ ቤተ መንግስት ገባ፣በጥቅምት ወር 2011 ዓ.ም አካባቢ የኦሮሞና የጌዲዮ፣ በኦሮሚያ በቤኒሻንጉልጉሙዝ፣ በኦሮሚያ በደቡብ ክልል፣ በአማራ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ግጭቶች ተከስተው በርካታ ሰዎች ተፈናቀሉ። የእስላም እና የክርስትና ሀይማኖት ተከታዮችን እንዲጋጩ ተደረገ፣ ቤተ ክርስቲያንና መስኪዶች ተቃጠሉ። እነዚህ ክስተቶች በሙሉ የደባ/የሴራ / ፖለቲካ ውጤቶች ናቸው።

እነዚህ ሁሉ ተደርገው ጠቅላይ ሚኒስትሩንና መንግስታቸውን መቀየር አልቻሉም። ስለዚህ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፖለቲካ ተቀባይነት እንዳያገኙ ብዙ ሴራዎች ተፈጽመዋል። ሴቶች ልጆች ተጠለፉ። እነዚህን ሴት ልጆች ታጥቆ ጫካ ያለ ሰው አልጠለፋቸውም። ምክንያቱም ቢጠልፋቸው ኖሮ ለራሱ የፖለቲካ ትርፍ ሲል ይናገር ነበር። ጫካ ያለ ታጣቂ የሚፈልገው ነገር ፖለቲካዊ ተቀባይነትን ነው። መንግስት ጸጥታ የማስከበር አቅም የተዳከመ መሆኑን ለህብረተሰቡ በማስረዳት ከህብረተሰቡ ተቀባይነት ለማገኘት ነው የሚፈልገው።

ሴት ልጆቹ የተጠለፉት መፈንቀለ መንግስት መደረግ አለበት ብሎ ሲጎተጉት በነበረውና በተለያየ መንገድ ለውጡን እየመራ ያለ መንግስት ደካማ ነው፤ ጸጥታ ማስከበር አይችልም የሚለውን ነገር ለማስረገጥ የሚያስብና በአገራችን የተከሰቱትን ግጭቶች ሲመራ በነበረው ቡድን ነው። ይህ የመፈንቀለ መንግስቱ ጠንሳሽ ቡድን ሴት ልጆችን ጠለፍኩ ብሎ መናገር አይችልም። ምክንያቱም በህጋዊነት በአገር ላይ ይኖራልና።

ይህ ጸረ ለውጥ ቡድን ህዳሴ ግድብ ተሸጠ አለ፣ ሌላም ሌላም የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ነዛ ያቀደው ግን ሊሳካለት አልቻለም። ይህን ሁሉ ከሞከረ በኋላ ከተላላኪዎቹ ጋር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ጦርነቱን አዲስ አበባ ጀምረን አዲስ አበባ እንጨርሳለን ብለው ወሰኑ። ጦርነቱን አዲስ አበባ ጀምረው አዲስ አበባ እንደሚጨርሱት ዕቅዳቸውንም ነገሩን። አዲስ አበባ ጀምረው አዲስ አበባ ለመጨረስ ትስስር ተፈጠረ።

ኦሮሞና አማራን ማጋጨት በአገሪቱ የመጣውን ለውጥ መቀልበስም፤ አሁን ያለውን የለውጥ መንግስትም ከስልጣን ማስወገድ ይቻላል የሚል መደምደሚያ ላይ ስለተደረሰ ለሀጫሉ በኦኤምኤን ቴሌቪዥን ቃለ ምልልስ ተዘጋጀለት። ለሀጫሉ የሚዘጋጅለት ጥያቄ የኦሮሞንና የአማራን ግንኙነት የሚበጥስና የሚያጋጭ እንዲሆን ታስቦ ነው። ሀጫሉ ለቃለ መጠይቅ ሲቀርብ ጋዜጠኛው በጣቢያው የምርመራ ጋዜጠኝነት ስራ ስለተጀመረ ከመጀመሪያዎቹ ተመራማሪዎች መካከል አንዱ ሀጫሉ ነው ብሎ ነው ያስተዋወቀው።

የምርመራው ጥያቄ ደግሞ ሀጫሉ ትግል ትተሀል፤ ድሮ ቄሮን አላችሁ ወይ ብለህ ትጠይቅ ነበር? አሁን ደግሞ ብረት ትገዛላችሁ ወይ እያልክ ነው እየጠየክ ያለው? ወደ ንግድ ገብተሃል። ወደ ንግድ የገባሃው ደግሞ ከብልጸግና ፓርቲ ጋር …ወዘተ የሚሉት ይገኙበታል። ዋናው ጥያቄ ግን ይህ አይደለም።

የሁከቱ ጠንሳሾች ኦሮሞና አማራን ልታባላ የምትችለው ሀጫሉ ስለ አጼ ምኒልክ የሚናገረው አቋሙ አማራን የሚያስቆጣ ስለሆነ ስለአጼ ምኒልክ አንሳለት ተብሎ ጋዜጠኛው ተነግሮታል። ጋዜጠኛውም ጥያቄውን አቀረበ፤ ሀጫሉም ስለ አጼ ምኒልክ የፈለገውን ነገር ተናገረ። ሀጫሉ በኦነግ ሸኔ ዛቻ እየመጣበት እንዳለና ለምን ያ ዛቻ እንደሚመጣበትም በግልጸ የተናገረው ነገር ግን ተቆርጦ ሳይተላለፍ ቀርቷል። ስለዚህ ሀጫሉ የተመረጠው ምክንያት በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ ታዋቂና የትግል ምልክት ተደርጎ የሚቆጠር ስለሆነ ነው። ሀጫሉን መግደል ማለት አንደኛ የኦሮሞን ህዝብ ከመንግስት ጋር ታጋጫለህ። ስለዚህ ኦሮሞና ይህ መንግስት ይለያያሉ ከሚል የተሳሳጠ እሳቤ ነበር።

ሀጫሉ ስለ አጼ ምኒልክ ተናገረ ፤ በምኒልክ ጉዳይ ደግሞ አማራ ይነሳል። ሀጫሉን አማራ ነው የገደለው የሚል አስተሳሰብ በኦሮሞ ይፈጠራል። ኦሮሞ በአማራ ላይ ይነሳል። ሆኖም አጼ ምኒልክ የአንድ ኢትዮጵያን የመሩ መሆኑ ቀርቶ የአማራ ንጉስ ተደርገዋል። ልክ አሁን ጠቅላይ ሚኒስትሩ መላው ኢትዮጵያን ህዝብ የሚያገለግሉ እንጂ ለኦሮሞ ብቻ የቆሙ አይደሉም። ስለዚህ ሀጫሉ የተገደለው የአማራና የኦሮሞ ግጭት ለማምጣት ነው። የሴራ ዕቅድ የለውጡን አመራሮች በቀላሉና በሰከንድ አራት ኪሎ ቤተ መንግስት ገብተን እናስወጣለን በሚል ስሌት ነው።

ሀጫሉ ተናግሮ የሚያሳምን፣ መርቆ የሚያጸድቅ፣ ረግሞ የሚያደርስ አንደበተ ርዕቱ፣ ደፋርና በሁሉም ኢትዮጵያዊያን ልብ የሚኖር ነው። መንፈቀለ መንግስት አድርጎ ወደ ስልጣን ለመምጣት ለሚያስበው ወንጀለኛ ቡድንም ሽብርን የሚለቅባቸው ተጸዕኖ ፈጣሪ ሰው ነበር። በዚህ ምክንያት የተለያዩ ቡድኖች በጣምራ ሆነው ሀጫሉን ገደሉት።

ሀጫሉን የገደሉበት ዓላማ ኦሮሞና አማራን ማጋጨት ከዚያ በኋላ የሀጫሉን ቀብር አዲስ አበባ ውስጥ ማድረግ፤ አዲስ አበባ ውስጥ ሳይቀበር 10 ቀናት በማቆየት ሁከቱንና ግጭቱን በመጨመር መንግስት መቆጣጠር ያቅተዋል። ከዚያ በኋላ ቤተ መንግስት ያለው የለውጥ አመራር ይወጣል፤ የሚፈልጉትን ሰው ወይም ቡድን ስልጣን ይይዛል ማለት ነው። ፍላጎቱ የነበረው ሀጫሉን አዲስ አበባ እንገለዋለን፣ አዲስ አበባ ውስጥ እንቀብረዋለን፣አብረን መንግስትንም እንቀብራለን ነበር። ይህ አልተሳካላቸውም። ለዚህ ወደ ስልጣን መምጫ ፍላጎታቸው ማሳኪያ ይሆን ዘንድ ሀጫሉን ገደሉት።

ለማንኛውም እንደዚህ አይነት ሴራና የወንጀለኞች ቡድን ከወንጀል አስተሳሰብ ውጭ ሌላ የማይፈጥሩ ለፖለቲካ ዓላማ ሳይሆን ለወንጀል ዓላማ ፍላጎት ሀጫሉን ገደሉት። ምክንያቱም ፖለቲካ አስተሳብ ነው እንጂ ወንጀል አይደለም። በአቋራጭና በሀይል ወደ ስልጣን መምጣት ወንጀል ነው። ይህን ያደረጉት ጤነኞች አይደሉም ወንጀለኞች ናቸው። የሚገርመው እነሱ ገለውት መልሰው ያዝኑለታል። ስለዚህ አሁንም ለውጥ አለ፤ ጸረ ለውጥም አለ። ጸረ ለውጡ የአመራር ምርጫ ከተደረገ ማግስት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ወንጀል እየሰራ ነው።

የሀጫሉን ሞት ተከትሎ ሰዎች ሞተዋል። ዜጎች 30ና 40 ዓመታት የለፉበት ንብረት ወድሟል። ሻሸመኔና መስል ከተሞች እንዳልነበሩ ሆነዋል። ግን እነሱ እንደፈለጉት ኦሮሞና አማራ ተነስቶ አልተዋጋም። ሁሉም ህዝብ ለምን እንደተደረገ ገብቶታል። ስለሆነም አማራና ኦሮሞን እርስ በእርስ የመፋጀት ምኞት አልተሳካላቸውም።

መረጃውን እናንተ ማረጋገጥ ትችላላችሁ እኔ እንደሰማሁት አብዛኛው ጉዳቱ የደረሰው በአማራ ላይ ብቻ አይደለም። ለምሳሌ በሁከቱ 164 ሰዎች ሞተዋል። ከዚህ ውስጥ 114 ሰዎች የተገደሉት ኦሮሞ ናቸው። ይህን ያደረጉ ሰዎች ለሀጫሉ ሀዘኔታ ካላቸው፣ የሚወዱትና ለኦሮሞ ጥቅም የሚቆሙ ከሆነ ኦሮሞ አይገሉም፣ በየአካባቢው የሚገኙትን የአባ ገዳ ምልክት የሆኑትን ሀውልቶችን ጭምር አፍርሰዋል።

ይህን ያደረገው ዓላማ ያለውና ለውጡን ያመጣ ቄሮ አይደለም። እነዚህ ቡድኖች አዲስ አበባ ጀምረን አዲስ አበባ እንጨርሳለን የሚለው መርሀ ግብርና ዕቅድ ሲቀርጹ በተለያየ ቦታ መዋቅር አላቸው። በየቦታው የሚያስተባብሩ ሰዎች አሏቸው። ለማስተባበር ደግሞ የግድ የዚያ አካባቢ ነዋሪ ሊሆንም፤ ላይሆንም ይችላል። የሚያስፈልገው ገንዘብ ብቻ ነው። ስራ ያጣ ከህብረተሰቡ ማህበራዊ ኑሮ የተገለለ ገንዘብ በመበተን የሁከቱ ፊታውራሪ ልታደርገው ትችላለህ፤ ሌላው በስሜት አብሮ ያደምቃል። ስለዚህ ይህ ቡድን በየአካባቢው ኦሮሞንም የሌላውንም ሀብት በዚህ መንገድ አወደመ። አገርንም አተራመሰ። ሀጫሉን ቢገሉትም፣ አማራንና ኦሮሞን የማፋጀት፣ መንግስትንም የማስወገድ ዕቅድ አልተሳካላቸውም።

አዲስዘመን፡– ሀጫሉንበዚህወቅትለምንለመግደልየወሰኑይመስሎታል ?

ሌተናልጀኔራልባጫ፡ ወቅቱ የህዳሴው ግድብ ሙሌት የተጀመረበት ነው። የግብጽ መንግስት እነዚህን ቡድኖች ፋይናንስ ያደርጋል። ከመስከረም 30 ቀን 2013 ዓ.ም በኋላ መንግስት የለም፤ ሁላችንም እኩል ነነን ሲሉ የነበሩ ሰዎች ስፖንሰር ላደረገው የግብጽ መንግስት መስከረም 30 ምን ዋጋ አለው። ምን ያደርግለታል ? የህዳሴው ግድብ ሙሌት የሚጀመረው አሁን ስለሆነ ሙሌቱ እንዳይጀመር ነው የምፈልገው። ሙሌቱ ማቆም ከተፈለገ ጉዳዮን አሁን ነው ማድረግ ያለባችሁ የሚል ትዕዛዝ ስለተሰጣቸው ነው ያንን ያደረጉት።

ስለዚህ የግብጽ የህዳሴ ግድብ ሙሌት እንዲጀመር አትፈልግም። መፈንቀለ መንግስት የማድረግ ፍላጎት ያለው ወንጀለኛ ቡድንም የለውጡ መንግስት ስልጣን ላይ እንዲቆይ አይፈልግም፤ ስለሆነም የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው በሚል የደንቆሮዎች ፖሊሲ የአገርን ሉዓላዊነትና ነጻነት ለግብጽ አሳልፈው ሰጡ። ለነገሩ ማንም ሰው ወንጀል ሊሰራ ይችላል። ወንጀል የሰራ ሰው ሁሉ የአገርን ጥቅም አሳልፎ ይሸጣል ማለት አይቻለም።

ነገር ግን ሁሌም በወንጀል ውስጥ የሚኖር የአገርን ጥቅም አሳልፎ ይሻጣል። ምክንያቱም እነዚህ የወንጀለኛ ቡድኖች ምንጊዜም ወደ ህግ ፊት የሚያቀርባቸውን ሀይል በማጥፋት ስልጣን ይዘው እንደፈለጉት ለመሆን በአገር ጥቅም ከመደራደር ወደ ኋላ የሚሉ አይደሉም። ሁሉም ወንጀለኞች የአገርን ጥቅም አሳልፈው አይሰጡም። የአገርን ጥቅም አሳልፈው የሚሸጡ ግን ሁሌም ወንጀለኞች ናቸው። በተለይ የወንጀለኛው ቡድን ደግሞ መቼም ቢሆን የአገርን ጥቅም አሳልፎ ከመስጠት የሚቆም አይደለም። ቡድኑ ተይዞ ወደ ፍርድ ቀርቦ በፍርድ ቤት የሚገባውን ቅጣት እስኪያገኙ ድረስ የአገርን ጥቅም አሳልፎ ከመስጠት ወደ ኋላ አይልም። ስለዚህ የግብጽ ፍላጎት ስለሆነ በዚህ ሁኔታ ችግሩ ተከሰተ። የሀጫሉ ግድያ በሰኔ ወር መፈጸሙ ዋናው ምክንያት ይህ ነው።

አዲስዘመን፡– እርስዎየወንጀለኛውቡድንየሚሉትአካልሁሌምወንጀልእየፈጸመእንዲቀጥልሊፈቀድልይገባልብለውያስባሉ ?

ሌተናልጄነራልባጫ፡መንግስት የወንጀለኛው ቡድን የትም ይሁን የትም የገባበት ገብቶ ይዞ ፍርድ ቤት ማቅረብ አለበት የሚል እምነት አለኝ። ከአሁን በኋላ ጊዜ መስጠት አያስፈልግም። እስካሁን መንግስት በጣም ትግስት አድርጓል። ትግስቱ አሁንም መቀጠል አለበት። ምክንያቱም መንግስት ታጋሽ ካልሆነ በስተቀር አምባገነን ነው የሚሆነው።

ግን መንግስት የሚታገሰውና የማይታገሰውን መምረጥ አለበት። ወንጀልን በፍጹም መታገስ የለበትም። ወንጀል ከሆነ የወንጀል ትንሽ የለውም። አንድን ሰው እንቁላልን በሰረቀ ቀን ካልቀጣኸው ነገ ጧት በሬ ወይም መኪና ሲሰርቅ እሪ ብትል ዋጋ የለውም። ስለዚህ መንግስት ትግስት ማድረጉ ትክክል ቢሆንም ወንጀል ላይ በተለይም ልታልፈው በማይገባ ወንጀል ትግስት ማድረግ የለበትም። በእርግጥ መንግስት ሁሉንም ወንጀለኛና የሚፈጠሩ ችግሮችን የሚይዝበት ጥበብ አለው። ወንጀል ላይ ግን ትግስት አያስፈልግም የሚል እምነት አለኝ።

ምክንያቱም የኔት ወርክ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ወንጀል የሚፈጸመው ተመሳሳይ ቡድን ነው። መንግስት ይህን ከያለበት መልቀም አለበት። ወንጀለኞችን ለፍርድ ለማቅረብ ደግሞ ከሰሜን ትግራይ አንስቶ እስከ ደቡብ ዶሎ ድረስ፣ ከምስራቅ ዋርዴር እስከ ጋምቤላ ድረስ በሙሉ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይተባበረዋል። ለዚህ ትግስት አያስፈልግም። በፊትም ቢሆን መንግስት ወንጀለኛ ቡድኑን ያልያዘው በትግስት ይመስለኛም። የቆየበት ምክንያት ሊኖረው ይችላል። አሁን ግን ወቅቱ ነው። ከአሁን በኋላ ወንጀል እየፈጸሙ እንዲቀጥሉ መፍቀድ የለበትም።

አዲስዘመን፡– የህዳሴውግድብለኢትዮጵያየልማትምንጭብቻሳይሆንየደህነትስጋትምሊሆንይችላልየሚሉወገኖችአሉ።በዚህዙሪያምንአስተያየትአልዎት?

ሌተናልጀኔራልባጫ፡-የህዳሴው ግድብ የኢትዮጵያ የልማት ምንጭ ብቻ ሳይሆን የደህነት ስጋትም ጭምር በሚለው ጉዳይ ላይ በከፊል እስማማለሁ። እርግጥ ነው የህዳሴው ግድብ ለኢትዮጵያ የዘላቂ ልማት ምንጭ ነው። ሆኖም የዘላቂ የደህንነት ስጋት ምንጭ ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም ግብጽ የህዳሴው ግድብ የመጀመሪያው ውሃ ሙሌት በመጠናቀቁ ኤሌክትሪክ ማመንጨት ሲጀምር የምትደራደረው በቀጣዩ ተግባር እንጂ ስራ በጀመረው ጉዳይ ላይ አይሆንም። የደህንነት ስጋት ምንጩም ሙሌት ካደረግና ሳናደርግ አንድ አይሆንም።

ግብጾች የመጨረሻ ርብርብ ያደረጉት፣ መፈንቀለ መንግስት አድራጊው ወንጀለኛ ቡድን የተኮሰው የመጨረሻዋ ጥይት ሀጫሉን የገደለበትና ያን ተከትሎ የመጣውን ግጭት ነው። ከዚህ በኋላ አትደገምም። ይህ ማለት ግን ትንኮሳ ያቆማሉ ማለት አይደለም። ነገር ግን ስጋቱ በግብጽ በኩልም በእኛ በኩልም ውሃ መያዝ ስለጀመርን እየቀነሰ ይሄዳል። ውሃ ከያዝን በኋላ ረብሻ አድርጎ መንግስት ቢቀየር ሌላ መንግስት ቢመጣ እንኳ ህዳሴው ግድብ ይጠናቀቃል። የህዳሴው ግድብን ፈጥነን ስራችንን በጨረስን ቁጥር ስጋታችን ይቀንሳል። ከተጠናቀቀ በኋላ ግን ስጋቱ መቶ በመቶ ባይጠፋም ትርጉም ያለው አይሆንም። ግብጾችም ፋይናንስ አያደርጉትም።

ስለዚህ ግብጾች በአገራችን ረብሻ ለመፍጠር የሚያወጡት ወጪ አይኖርም፣ ለእኛም ስጋታችን ይቀንሳል፤ እነሱም እጃቸውን እየሰበሰቡ ይሄዳሉ። ምክንያቱም በሁለት መንገድ ነው። አንደኛው ግብጽ በእግረኛ ጦር ልትወጋን አትችልም። ከእኛ ጋር ጎረቤት አገር ቢሆኑና ቢገጥሙን ኖሮ እኛን ማሸነፍ አይችሉም። እኛ ወደፊት ሊገጥመን ለሚችል ጦርነት ነው እየተዘጋጀን ያለው። በመሬታችን፣ ለእውነታችንና ለጥቅማችን ነው የምንዋጋው። እስከ ዛሬ ድረስ በጦርነት ስለቆየን ልምዱ አለን። በዚህ ምክንያት ግብጾች ጎረቤት ሆነው ቢገጥሙንም እኛ እናሸንፋለን። እንጂ ከጣሊያን በፊት ወግተውን አሸንፈናቸዋል በሚል አይደለም።

ዛሬ ብንዋጋ እንኳን እኛም ሆነ ግብጽ ከዚያን ጊዜዎቹ ኢትዮጵያና ግብጽ አይደለንም። ምክንያቱም የምተዋጋው ጦርነት ያላፈውን ሳይሆን ዘመን ያመጣውን ነው። ድሮ አሸንፈናል፤ ዛሬም እናሸንፋለን ሳይሆን ዛሬ የምናሸንፍበት ተጨባጭ ሁኔታ ላይ ስላለን ነው። ስለዚህ እኛና ግብጽ ጎረቤት ስላልሆን የእግረኛ ጦርነት አንጋጠምም። በማንኛውም ወታደራዊ ትንታኔ ግብጽ ተወረናለች የሚለው ሀሳብ ተቀባይነት የለውም። ስለዚህ ግብጽ የምታደርገው ነገር እኛው አገር ሆኖ የእኛ ዜጋ ተጠቅማ ወይም አገርን ሲመሩ የነበሩ ሰዎችን ተጠቅማ ነው።

Subscribe to our newsletter!

[newsletter_form type=”minimal” lists=”undefined” button_color=”undefined”]

ምክንያቱም ግብጾችን ወክለው የሚዋጉ ተላላኪዎች ስላሏቸው ለእነሱ ፋይናንስ ማድረግ ብቻ ይጠበቅባቸዋል። ለዚህ ደግሞ ማረጋገጫው የግብጽ ቴሊቪዥን በአገራችን ቴሌቪዥን ሲተላለፍ ነው የሰማነው፤ ያያነው። ስለዚህ ግብጾች ይህን ሀይል ነው ስፖንሰር የሚያደርጉት እንጂ እነሱ በቀጥታ ጦርነት አይከፍቱም። ስለዚህ ህዳሴው ግድብ የስጋት ምንጭ ነው የሚባለው ነገር ስጋቱ ሙሌቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ ነው። የህዳሴው ግድብ የስጋት ምንጫችን ሆኖ የሚቀጥለው ግድቡ እስኪጠናቀቅ ድረስ ነው። ይህ ደግሞ በእኛ የመገደብ ፍጥነት ላይ ይወሰናል። ከዚያ በኋላ ነገሩ ይቀየራል።

አዲስዘመን፡ግብጽበኢትዮጵያየውስጥጉዳይከመግባትእንድትቆጠብምንይመክራሉ?

ሌተናልጄነራልባጫ፡ ግብጾች ሊያውቁት የሚገባ ነገር አለ። አንደኛ የአባይ ተፋሰስ ከሆኑ አገሮች ጋር የመነጋገር ፤ ከእነሱ ጋር ተወያይቶ ችግርን የመፍታት መንገድ ብትከተል ያዋጣታል። ከዚህ ውጭ በቀኝ ዘመን አስተሳሰብ በመመራት ከአባይ ተፋሰስ አገራት ውጭ አሁንም በምዕራባዊያን ሆነ በሌሎች አገሮች ተጸዕኖ እፈጥራለሁ፤ ለውጥ አመጣለሁ የሚል ነገር አክትሟል። ቢያቆሙና ቢቀርባቸው ይሻላል። አሁንም ምዕራባዊያንም እንኳ ማክተሙን እያሳዩአቸው ነው።

የቀደሙ የኢትዮጵያ መንግስታት አባይን የማልማት ፍላጎት ቢኖራቸውም አቅሙ ስሌላቸው ማድረግ አልቻሉም። አሁን ግን ፍላጎቱም፣ አቅሙና ችሎታም አለን። በኢትዮጵያ የጸጥታ ጉዳይ የምታደርገውን ጣልቃ ገብነት ማቆም አለባት። ኢትዮጵያ በውይይትና በፍትሀዊነት ስለምታምን እንጂ የአባይን ተፋሰሶች አሟጦ በማልማት አባይን ወንዝ ሳይሆን ጅረት ማድረግ ይቻላል። ስለዚህ መስታወት ቤት ቁጭ ብለህ ወደ ሰው ድንጋይ አትወርውር ቢባልም ግብጾች ይህን ነው የሚያደርጉት። በኢትዮጵያ ጸጥታ ተላላኪ በመላክና ስፖንሰር በማድረግ የማታደርገውን ጣልቃ ገብነት ማቆም አለባት። አለበለዚያ ግን ኢትዮጵያ በሌላም መልኩ ቢሆን አጸፋውን መመለሷ አይቀርም።

ይልቅስ ግብጾች የእነሱን የባንዳ ቡድን ስፖንሰር ከምታደርግ ኢትዮጵያ የምታካሄደውን አረጓዴ አሸራ ስፖንሰር ብታደርግ የተሻለ ነው። አባይ ወንዝ እንዳይደርቅና በኢትዮጵያ የድርቅ አደጋ እንዳያጋጥም በአረጓዴ አሻራ መሳተፍና ስፖንሰር ማድረግ አለባት። ያኔ ነውዝናብ የማይቆመው ፤አባይም በቂ ውሃ ይዞላቸው የሚሄደው። እንዲሁም ደለል እንዳያስቸግራቸው ኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደውን የእርከን ስራ ስፖንሰር ማድረግና በአካልም መሳተፍ ይኖርባቸዋል። ከአሁን በኋላ የሚያወጣቸው ይህኛው መንገድ ነው። ኢትዮጵያዊያንም ግብጽዊያንም የአባይ ልጆች ናቸውና።

አዲስዘመን፡የተፎካካሪፓርቲዎችየሽግግርመንግስትመቋቋምአለበትሲሉይደመጣል፤የሽግግርመንግስትከአገርጸጥታናደህነትአኳያምንችግርሊያመጣይችላል ?

ሌተናልጀነራልባጫ፡ከመስከረም 30 ቀን 2013 ዓ.ም በኋላ መንግስት የለም የሚሉ ሰዎች የሽግግር መንግስት መቋቋም እንዳለበት ሲወተውቱ ይሰማል። ይህ የሽግግር መንግስት ከሁሉም ፓርቲዎች ተወጣጥቶ መቋቋም አለበት ነው የሚሉት። የሽግግር መንግስት ቢቋቋም የራሳችን ፓርቲዎችና ሰዎች ለግብጽ እየሰሩ እንዴት አድርገው ነው የኢትዮጵያን ጥቅም የሚያስከብሩት? እንዴት አድርገው ነው የአገራችንን ሉዓላዊነት ማስከበር የሚቻለው? እንዴት አድርገን ነው የግብጽን ጣልቃ ገብነት መከላከል የምንችለው? እንዴት አድርገን ነው የህዳሴን ግድብን ከፍጻሜ ማድረስ የምንችለው? የሚሉትን ጉዳዮች ፖለቲከኛ ነይ ባዮች ሶስቴ አራቴ ማሰብ አለባቸው። ለሚናገሩት ንግግርም ተጠያቂነት መውሰድ አለባቸው።

ይች አገር ነገ ጠዋት የሚመሯት አገር ነች። የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ጥሩ ፕሮግራም ካላቸውንና የህዝብን ልብ ከገዙ ወደ ስልጣን የማይመጡበት ምክንያት የለም። ሲለፉ ውለው ቢያድሩ ወደ ስልጣን የማይመጡት ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም በፊት በነበረው መንግስት ነው። ዛሬ ግን እንዳዛ አይነት ነገር የለም። ስልጣን ላይ ያለው የሽግግር መንግስት ቢሆን ኖሮ ሀጫሉ ግድያ ተከትሎ የመጣውን ሁከት ማቆም አይቻልም። ምክንያቱም የሁከቱ ባለቤት የመንግስት ስልጣን የያዙ ሰዎች ስለሚሆኑ ነው። በሬህን ከሰረቀ ሰው ጋር ፍለጋ አትሄድ ፤በሬህን አታገኘውም እንደሚባለው እነሱ ሁከት ቀስቅሰው ራሳቸው መንግስት ሆነው ሁከቱን መቆጣጠር ስለማይቻል ነው። ከመስከርም 30 ቀን 2013ዓ.ም በኋላ የሽግግር መንግስት ይቋቋም የሚሉ ፓርቲዎች ከዚህ ሁከት መማር አለባቸው የሚል አስተያየት አለኝ።

አዲስዘመን፡ህወሓትበትግራይክልልምርጫለማካሄድዝግጅትእያደረገነው።ይህከጸጥታናከህግአኳያምንአድምታአለው?

ሌተናልጀነራልባጫ፡ በትግራይ ክልል ምርጫ እናደርጋለን የሚለው ነገር ከጸጥታም ከህግም አኳያ በአግባቡ መታየት አለበት የሚል እምነት አለኝ። ምክንያቱም ትክክል ስላልሆነ ነው። አንደኛ ትክክል ያልሆነበት ምክንያት ምርጫን የሚመራው በፌዴራል መንግስት የተቋቋመው የምርጫ ቦርድ እንጂ ተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲ አይደለም።

 ማንኛውም ተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲ ምርጫ ማዘጋጀት አይችልም። ምርጫን የሚያዘጋጀው ከፖለቲካ ፓርቲ ነጻ የሆነ በፌዴራል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚቋቋም በአገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን ነው። ከዚህ ውጭ ፖለቲካ ፓርቲ ስልጣን ላይ ቢሆንም ምርጫን አያዘጋጅም። ስለዚህ ምርጫ እናዘጋጃለን የሚሉት ወንድሞቻችን እነሱ የፖለቲካ ፓርቲ እንጂ መንግስት አይደሉም። የረሱትና ያላወቁት ነገር የፖለቲካ ፓርቲ መሆናቸውን ነው። በክልል አሸናፊ ፓርቲ ቢሆኑም ምርጫን የማዘጋጀት ስልጣን የላቸውም። ይህ አንድ የጸጥታ መደፍረስ ምንጭ ነው የሚሆነው።

እናም ምርጫ የሚያደረጉ አይመስለኝም፤ ሊሆን የማይችል ነገር ነው። ጉዳዩንም አስበውበት የሚቀይሩ ይመስላሉ። ምክንያቱም መብትም ስልጣንም የላቸውም። ምርጫ የሚያደርጉ ከሆነ ግን ስርዓት አልበኝነት ይመጣል። አንድ ክልል ከፌዴራል መንግስቱ ጋር በስምምነት ነው መስራት ያለበት። ህገ መንግስቱን በመጣስ ከህግ ውጭ የሚሄድ ከሆነ ደግሞ በህገ መንግስቱ ውስጥ መፍትሄ አለው። ስለዚህ የዚህ አይነት ስርዓት አልበኝነት በሚመጣበት ጊዜ በህገ መንግስቱ ባስቀመጠው መፍትሄ መሰረት ይስተካከላል።

አዲስዘመን፡አሁንከሚታየውየፖለቲካእሰጣገባአኳያኢትዮጵያወደፊትየእርስበእርስጦርነትሊያጋጥማትይችላልየሚሉወገኖችአሉ።በዚህጉዳይላይምንአስተያየትአልዎት?

ሌተናልጄነራልባጫ፡ የፌዴራል መንግስት ከማንኛውም ክልል ጋር ጦርነት ሊገጥም አይችልም። የትኛውም ክልል የፌዴራል መንግስትን ጦርነት አይገጥምም። ይህን የሚያደርግ ከሆነ ዓላማው ሌላ ነው የሚሆነው። እንደዛ አይነት ነገር ይመጣል ብዬም አላስብም። እናም እኔ እንደዛ አይነት ነገር ይመጣል ብዬ ባላስብም ህብረተሰቡ ውስጥ ጦርነት ሊኖር ይችላል የሚሉ አስተሳሰቦች ሊኖሩ ይችላሉ።

በኢትዮጵያ ጦርነት ሊኖር አይችልም። ምክንያቱም የፌዴራል መንግስቱን የሚወጋ አካል ካለ ከሁሉም ክልሎች ጋር ይዋጋል ማለት ነው። የፌዴራል መንግስትን ወጋ ማለት እኮ ሉዓላዊነትን መጣስ ወይም መፈንቀለ መንግስት ማድረግ ነው። ስለዚህ ጦርነት የሚባለው ነገር አይሆንም። አንደኛ ማንኛውም ክልል የፌዴራል መንግስቱን መግጠም የሚችል አቅም የለውም። ክላሽን አሸክመህ ከታንክና ከሚሳኤሎች ጋር የምታጋጥመው ሰው አይኖርም። እንደዚህ አይነት ነገር ውስጥ የሚገባ ወጣትም ያለም አይመስለኝም።

200ሺ ይሁን 400ሺ ወጣቶችን ሰብስበህ ጠብመንጃ ብታሸክምም ዋጋ የለውም። ጦርነትን የምታሸንፈው መሳሪያ በመከመር፣ የሰው ሀይል በማብዛት እና ዘራፍ በማለት አይደለም። ጦርነቱን የምታሸንፈው ከጦርነት ውጭ ይህን ነገር ላገኝ አልችልም ብለህ ህዝቡን የምታሳምንበት ነገር ካለህ ነው። ወደ ጦርነት የሚወስድ ነገር ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ የለም።

ሌላው በጦርነት ካልሆነ በስተቀር ሀሳቤን ወደ መድረክ ማቅረብ አልችልም የሚለው የፖለቲከኛ አስተሳሰብ አይደለም። ይህ በሶማሊያ ስናያቸው የነበሩ የጦር አበጋዞች ስራ ነው። ስለዚህ ከጦርነት ውጭ ሀሳቤን ተግባራዊ ማድረግ አልችልም ብለህ ህዝቡን የምታሳምንበት ጉዳይ ሊኖርህ ይገባል።

ሌላው በየት አድርጎ ነው የሚዋጋው። ለምሳሌ አንድ ክልል ከፌዴራል መንግስት ጋር ጦርነት እገጥማለሁ ብሎ ለጦርነት ቢነሳ መጀመሪያ ከራሱ ክልል ጋር ነው የሚጋጨው። ሁለተኛ ከመላ ኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ይጋጫል። ሶስተኛ ኢትዮጵያ ጎረቤት አገሮች ሁሉ ጋር ይዋጋል ማለት ነው። ይህን አደርጋለው የሚል ካለ ሞኝ ነው። ምክንያቱም በምንም ታምር አይችልም። ማንም ሰው ከእንደዚህ አይነት ራስን የማጥፋት እርምጃ ይገባል ብዬ አላስብም።

ስለዚህ ጠበጃ ማስጮኸ ጦርነት አይባልም። ጦርነት አስተሳሰብ ነው። ጦርነት ሁለት ጦር ሜዳ የሚያዋጉ ሀይሎች የሀሳብ ፍጭት ነው። ስለዚህ አንድ ክልል ተነስቶ የፌዴራል መንግስትን በጦርነት አፈሙዝ አሸንፌ የሆነ ነገር አደርጋለሁ የሚል ካለ የእሳት ራት ነው የሚሆነው። ህግም አይፈቅድለትም።

ስለዚህ ጦርነት ይመጣል ብዬ አንድ ቀንም ሰግቼ አላውቅም። ምክንያቱም የፌዴራል መንግስቱን አስተሳሰብ አውቃለሁ፣ የክልሎችንም አቅም አውቃለሁ፤ የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ማለትም የኤርትራን፣ ኬንያ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳንና ሶማሊያ በኢትዮጵያ ውስጣዊ ሰላም ላይ ያላቸውን አቋም አውቃለሁ።

አዲስዘመን፡– እርስዎበተለያዩጦርነቶችበአዋጊነትእንደመሰለፍዎጦርነትንእንዴትይገልጹታል?

ሌተናልጀነራልባጫ፡ ጦርነት ሰው ይበላል፣ ኢኮኖሚ ይበላል፣ ጦርነት ቀን ከቀን አውዳሚ ነው። ድህነትን ያባብሳል። ተቋማትን ያፈርሳል።

አዲስ ዘመን ሐምሌ 30/201 ጌትነት ምህረቴ

Subscribe to our newsletter!

[newsletter_form type=”minimal” lists=”undefined” button_color=”undefined”]

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *