የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቶ ጃዋር መሀመድ እና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ 14 ተጠርጣሪዎች ላይ አቃቤ ህግ የቅደመ ምርመራ ምስክሮችን እንዲያሰማ ብይን ሰጠ።

አቶ ጃዋር መሀመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ ሐምዛ አዳነን ጨምሮ 14 ተጠርጣሪዎች በዛሬው እለት በፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ከትናንት በስቲያ ሐምሌ 30/ 2012 ቀርበዋል።

ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ጃዋርን ጨምሮ አጠቃላይ 14 ተጠርጣሪዎች አቶ ጃዋር መሃመድ በሚል መዝገብ በመዝገብ ቁጥር 215585 ላይ የቅድመ ምርመራ መዝገብ የከፈተ ሲሆን፤ በዚህ መዝገብ ላይ ሁከትና ብጥብጥ በማነሳሳት ወንጀል የተጠረጠረ ጋዜጠኛም ተካቷል።

አቃቤ ህግ አቶ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ በ14ቱም ተጠርጣሪዎች ላይ በመዝገብ ቁጥር 215585 የቀዳሚ ምርመራ እንዲደረግባቸው ጠይቋል።

በተጨማሪም የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በዚህ መዝገብ ላይ በአጠቃላይ በተጠርጣሪዎች ላይ የሚመሰክሩ 15 ምስክሮች ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን፤ እንዲሁም 5 ምስክሮች ደግሞ ከመጋረጃ በስተጀርባ የምስክርነት ቃላቸውን እንዲሰጡ ሲል አቤቱታ አቅርቧል። በዝግ ችሎት ምስክሮቹ ቃላቸውን እንዲሰጡም ጠይቋል።

የሁሉም ተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸው አቃቤ ህግ ያቀረበው አቤቱታ ላይ መቃወሚያቸውን አቅርበዋል።

በዚህም በዝግ ችሎት ተብሎ ለቀረበው አቤቱታ በግልፅ ችሎት ምስክሮቹ እንዲሰሙ እንደሚፈልጉ እና አቃቤ ህግ የሚያቀርባቸው ምስክሮች ጭብጥ ለመከላከል እንደሚያመች እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

እንዲሁም ምስክሮቹ ከመጋረጃ በስተጀርባ የምስክርነት ቃል መስጠት እንደሌለባቸው እና ስም ዝርዝራቸውም ተለይቶ ተሰጥቷቸው አውቀዋቸው የምስክርነት ቃላቸውን ሊሰጡ እንደሚገባም ገልፀዋል።

ክሱ ስልጣን ባለው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሚቀርብ መሆኑን ተከትሎ የቀዳሚ ምርመራ የምስክር ቃልም ለክሱ መከላከል እንዲያስችላቸው አስቀድመው ሊያውቁት እንደሚገባም መቃወሚያዎችን አንስተዋል።

ተጠርጣሪ አቶ በቀለ ገርባ፣ “የማስመዘግበው አቤቱታ አለኝ፤ ሃሳቤን ፍርድ ቤቱ ይቀበለኝ” ያሉ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ “በጠበቆቻችሁ በኩል በቂ ሃሳብ ተነስቷል” ሲል አልተቀበላቸውም።

የግራ ቀኙን ክርክር የመረመረው የፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ብይን ሰጥቷል።

Source ENA

ግፉን ሳትጠየፉ የወንጀሉ መጠሪያ እንቅልፍ ለነሳችሁ

ጂኖሳይድ ተፈጽሟል ወይስ አልተፈጸመም? በማሳያዎች እንፍረድ

በቀለ ገርባ በዘር የእርስ በርስ ግጭት በማነሳሳት ወንጀል እንደሚከሰሱ አቃቤ ህግ ይፋ አደረገ

በአዲስ አበባ ልዩ የመሬት ኦዲትና ምዝገባ ይጀመራል፤ መኖሪያ ቤት እየተጠባበቁ ያሉ ነዋሪዎች በማህበር ተደራጅተው ቦታ ያገኛሉ

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *