“Our true nationality is mankind.”H.G.

በትግራይ የኮሮና ወረርሺኝ በድብቅ እንደሚያዝ ተሰማ፤ 60 የጤና ባለሟዎች በኮቪድ 19 ተጠቅተዋል ይባላል

በትግራይ የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ በድብቅ እንደሚያዝና በሃይደር ሆስፒታል ከስልሳ በላይ የጤና ባለሙያዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ፈንቅ ል በመባል የሚታወቀው የወታቶች እንቅስቃሴ አመራሮች የሆስፒታል ምንጮቻቸውን ጠቅሰው ተናገሩ። እስር ቤት ውስጥ ወረሽኙ እየተራባ መሆኑንንም አመልክተዋል። የክልሉ መንግስትም ሆነ ይህን ሪፖርት እንዲሰጥ የተቋቋመ ተቋም ይህን አስመልክቶ ያለው ነገር የለም።

ንቅናቄው በማህበራዊ ገጹ እንዳስታወቀው ሰላሳ የሚሆኑ ሃኪሞች በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከወረሽኙ ጋር በተያያዘ ለሁለት ሳምንታት ተዘግቶ የነበረው የሃይደር ሆስፒታል ውስጥ ከዛም የዘለቀ ቁጥር ያላቸው ወገኖች እንደሚገኙ ተገልጿል።

በትግራይ የሚደረሱ ሰማላዊ ሰልፎችና ወታደራዊ ትርዕይቶች ለወረሺኙ መስፋፋት ዋና ምክንያት መሆኑንን ንቅናቄው ጠቅሶ፣  ስለፍ እያዘጋጀ ጦርነት የሚጎስመው ህወሃት ተተያቂ እንደሆነ ይፋ አድርጓል።

የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የህብረተሰብ ጤና ትምህርት ቤት ባልደረባ የነበሩት ዶክተር ፍሰሃየ አለምሰገድ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሞያቸው ህብረተሰባቸውን በማገልገል ላይ እያለ በኮሮና ቫይረስ በሽታ ተይዘው የሕክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ህይወታቸው ማለፉን ተከትሎ ንቅናቄው ይህ ማሳያ እንደሆነ አመልክቷል። ሰላሳ ሃኪሞችና ተቸማሪ ሰላሳ የሚሆኑ የህክምና ባለሙያዎች በቫይረሱ መተቃታቸውና በሚስጢር መያዙ እንዳሳሰባቸውም ጠቁመዋል።

Related stories   ፋኦ በትግራይ ክልል ለአርሶ አደሮች የእህል ዝርያዎችን ማሰራጨትና እንስሳቶችን መከተብ ጀመረ

Image may contain: 1 person, closeupየጤና ሚንስቴር

ጤና ሚኒስቴር የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የህብረተሰብ ጤና ትምህርት ቤት ባልደረባ የነበሩት ዶክተር ፍሰሃየ አለምሰገድ ህልፈተህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልጻል ።ዶክተር ፍሰሃየ አለምሰገድ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሞያቸው ህብረተሰባቸውን በማገልገል ላይ እያሉ በኮሮና ቫይረስ በሽታ ተይዞ የሕክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ከቆዩ በኋላ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ ለዶ/ር ፍሰሃየ አለምሰገድ ቤተሰብ እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ሁሉ መጽናናትን እንመኛለን!


 

ህወሃት ፈንቅል ይህን ዜና ይፋ ካደረገ በሁዋላ የተወሰኑ የህክምና ባለሙያዎች በቫይረሱ መተቃታቸውን እንዳመነ ፈንቅል አመልክቷል። አያይዞም በእስር ቤቶች ውስጥ በቫይረሱ የተጠቁ  ወገኖች መገኘታቸውን ከጥበቃ ሰራተኞች መረጃ መገኘቱንም አውስቷል። ይህ ሁሉ እየሆነ ባለበት በአሁኑ ወቅት የመቀሌውና የማይጨው ሰልፍ ሳያንስ በመጪው እሁድ የውቅሮ ህዝብ ወታደራዊ ልብስ ለብሶ ሰልፍ እንዲወጣ መታዘዙን አውግዟል።

Related stories   የትግራይ ክልል ባቀረበው ፍላጎት መሠረት የአፈር ማዳበሪያ መቶ በመቶ እንዲቀርብ መደረጉ ተገለጸ

ፈንቅል ይህን ይበል እንጂ ከትግራኡ ክልል ጤና ቢሮም ሆነ ከክልሉ አስተዳደር ስልሳ የሚጠጉ የህክምና ባለሙያዎች በቫይረሱ ስለመተቃታቸው በይፋ የተባለ ነገር የለም። በአብዛኛው የህወሃት ደጋፊዎች የፈንቅልን ዜና ሲያጠጥሉ መስማትም የተለመደ ነው። ፈንቅል የፊታችን እሁድ የትግራይ ተወላጆችን በወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ለማማከር ስብሰባ መጥራቱ አይዘነጋም።

በተያያዘ ዜና ምንጫቸውን ያልተቀሱ የማህበራዊ ሚዲያ አካላት አቶ ስብሃት ነጋ በቫይረሱ መለከፋቸውን እየገለጹ ነው። ከፈንቅልም ይህ ተሰምቷል። ይሁን እንጂ አቶ ስብሃትን አስመክቶ በይፋ የተባለና ሃላፊነቱን ወስዶ ያረጋገጠ ተቋም እስካሁን አልተደመጠም።

በሌላ የኮቪድ ዜና የጤና ሚኒስቴር ዛሬ በኢትዮጵያ ለ9203 ሰዎች ምርመራ አካሂዶ 552 ሰዎች በቫይረሱ መጠቃታቸውን በእለታዊ ሪፖርቱ አስታውቋል። 15 ሰዎች ሲሞቱ በድምሩ የሟቾች ቁጥር 380 መድረሱን ይፋ አድርጓል። በጥቅሉ 21.452 ሰዎች በቫይረሱ የታያዙ ሲሆን 9415 አገግመዋል። አሃዙ በየእለቱ የሚጨምር ከመሆኑ የተነሳ ህዝብ የሚችለውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ምክር እየተለገሰ ነው።


Subscribe to our newsletter!

[newsletter_form type=”minimal” lists=”undefined” button_color=”undefined”]
0Shares
0