በአገራችን በተለያዩ ወቅቶች በተለያዩ ስፍራዎች የጅምላ ግድያ ተፈጽሟል። ሰዎች በብሂራቸው፣ በማንነታቸውና በምነታቸው ተለይተው ጉዳት ደርሶባቸዋል። ይህ አካሄድ ቀደም ሲል ከነበረው ስርዓት የአገዛዝ እምነት መነሻ ምክንያትና አንዳንዴም ሆን ተብሎ ይፈለግ ስለህነበር ብዙም ርቀት በመሄድ ጉዳዩን ከስሩ ለማድረቅ ሲሰራ አልታየም። እንደ አሁኑ የሚዲያ መብትም ባለመኖሩ ሁሉም ነገር ድብቅ፣ ሚስጢርና ሆድ ይፍጀው አይነት ነበር። ወይም በሚፈለገው ደረጃ ተመጥኖ ለሚፈለግ ፍጆታ ብቻ ይፋ ከሚሆነው ውጪ ማወቅ አይቻልም ነበር። 
ሰሞኑንን በኦሮሚያ የሆነውን ተከትሎ በተፈጠረው አሰቃቂ ድርጊት ስያሜ ላይ መግባባት ባይኖርም የሆነውን ሁሉ የሚክድ አንዳችም ቡድን አልተሰማም። ይህንኑ የድርጊቱን ስያሜ ተከትሎ ልጅ ግሩም የሚከተለውን እይታቸውን በንፅፅር አቅርበዋል።
 
This image has an empty alt attribute; its file name is leje-grum-e1596884184824.jpgጂኖሳይድ ተፈጽሟል ወይስ አልተፈጸመም? በእኔ አመለካከት
በጅማ፣ ሆለታ፣ ሻንቡ፣ ከሚሴ ወሎ፣ አሰላ፣ ሻሸመኔ፣ ዓወዳይ፣ አዳባ፣ ባሌ ሮቤ እና ሌሎች አካባቢዎችም ኦሮሞ ባልሆኑ ኢትዮጵያውያን በተለይም በአማራ፣ በጉራጌዎችና ኦርቶዶክስ ኦሮሞ በሆኑ ላይ ጉዳት ብቻ ሳይሆን ግድያዎች ከተጀመሩ ሰንብተዋል። የጅምላ ግድያ ሲፈጸም የዘር ማጥፋት ወይም ጂኖሳይድ መሆኑን ለማረጋገጥ የሁለት ብሔሮች ጥላቻ ብቻ መሆን አይጠበቅበትም።
በተለይ በኦሮሚያ የተፈጸመው ግድያ ትኩረት ያደረገው “ነፍጠኝነት” በሚለው ሰፋ ያለ ይዘት ያለው አባባል ሲሆን ይሄ ደግሞ ጥንት ከአማራነት ጋር ብቻ የሚታይ የነበረ ቢሆንም እሁን ግን ከማንኛውም ብሔረሰብ የመጡ የኦርቶዶክስ አማኞችንም ይጨምራል። ዞሮ ዞሮ ግድያዎቹ ኢላማ ያደረጉት በተወሰኑ ማህበረሰህብ ወይም ቡድን ላይ ነው።
በMontclair State University ተመራማሪ የሆነችው Lauren Geravis እ.ኤ.አ በ2015 ስለ ሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወንጀል ስለ ዘር ማጥፋት ቅድመ ሁኔታዎች በኦሮሚያ የተፈጸሙት ግድያዎች ምን አይነት ገጽታ እንዳላቸው ማብራሪያ ለመስጠት ይረዳናል።
በሩዋንዳ ጂኖሳይድ ከመፈጸሙ በፊት የታዩ ምልክቶች
Stage 1: Classification
የትግራይ፣ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ጉራጌ፣ ደቡብ ወዘተ ተብሎ ህዝብ በህገ መንግስቱ በብሄርና በክልል ተከፋፍሏል። ክፍፍሉን ለማባባስ ስለእያንዳንዱ ብሔረሰብ ድክመቱና ክፋቱ ትርክቶች ተሰርቶለታል።
Stage 2: Symbolization
ብሄራችን መታወቂያችን ላይ አለ፡፡
Stage 3: Dehumanization
ቱስሲዎች ዛፎች፣ እባቦች፣ በረሮዎች ተብለው ይጠሩ ነበር። እነዚህ ስሞች የተሰጡት ሁቱዎቹ ቱስሲዎችን ለመግደል በቂ ምክንያት እንዳላቸው ሆኖ እንዲሰማቸው አድርጓ። ‹በረሮዎቹ› ላይ ጥላቻን ለመግለጽ የተፈጠሩ የሚዲያ ጣቢያዎች ነበሩ፡፡
ቱትሲዎች ከፍተኛ ትምህርት እና በመንግስት የስራ ቦታ መከልከል ተጀመረ።
በሃገራችን አማራ አህያ፣ ነፍጠኛ ፣ትግሬ ቅማላም አምበጣ በሊታ አጋሜ፣ ኦሮሞ ዝንባም ወዘተ በተመሳሳይ እንደ OBN/OMN አይነት ሚዲያዎች ነፍጠኝነትን ስለመጸየፍ ሲናገሩ ኦሮሞ ያልሆኑ ሰዎችን ስለማጥፋት ወይም ስለመጥላት dehumanization መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።
Stage 4: Organization ማደራጀት
– በሩዋንዳ “የጥላቻ ራዲዮዎች” ነበሩ።
– ራዲዮዎች ስለ ቱትሲዎች የስልጣን ቦታን ይዘው ስለነበር ሚዲያው እንዴት መወገድ እንዳለባቸው ይናገሩ ነበረ።
– ሁቱዎች የመንገድ መዝጋትና ቱትሲዎችን መግደል ጀመሩ።
– የሬዲዮ ጣቢያዎች ቱትሲዎች የት አካባቢ እንደሚገኙ መናገር ጅመሩ።
በሃገራችን ብዙ ተከታይ ያላቸው የፌስቡክ አክቲቪስቶች በጠላትነት ያስቀመጡት ከአንድ በላይ ብሄር አለ፡፡ ለህውሃት አክቲቪስቶች የአማራን ክልል ህዝብ እርስ በርስ ማናቆር ቀዳሚ ተግባራቸው ነው፡፡ ለዚህ ትልቁ ማሳያ ተመሳሳይ ቋንቋ፣ ታሪክ ባህል፣ አለባበስ ወዘተረፈ ያላቸውን ቅማንትና አማራን ለማጋጨት የሚያደርጉት ሩጫ ነው፡፡ በአማራነት አክቲቪስቶች ሆነው የኦሮሞን መሳደብ ያልተለመደ እይደለም። በኦነግ አክቲቪስቶች ያለው ከሁሉም የባሰ ነው።
Stage 5: Polarization ማራራቅና ማቃረን
በሩዋንዳ መንገዶችን መዝጋት ተጀመረ፡፡ ስታዲየሞች የፍርሃት ምንጭ ሁኑ። ይህ በሁሉም ለሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወንጀል ከሚከሰቱት ታላላቅ የሽብር ምልክቶች አንዱ ሆኖ ነበረ።
ቱትሲዎች ያሉባቸው ሆስፒታሎች፣ መንገዶች፣ ስቴዲዮሞች አካባቢ ቱትሲዎች ላይ ጥቃት ማድረስ፣ ምሽት ላይ መግደል ተጀመረ።
በመላው ሃገራችን በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ በብሔር ለይቶ ማጥቃት ሲደርስ የነበረ፣ በእግር ኳስ ሜዳ ላይ ሲታይ የነበረው ግልጽ ጥቃትን እንደምሳሌ መጥቀስ ይቻላል።
Stage 6: Preparation ዝግጅት ማድረግ
የሁቱዎች የሬዲዮ ጣቢያዎች ቱትሲዎች የት አካባቢ እንደሚኖሩ እና ለምን መጥፋት እንዳለባቸው እንዲሰሙ ያስገድዱ ነበረ። የሬዲዮ ጣቢያዎች በቱትሲዎች ላይ ጥላቻ እንዲጨምር ከፍተኛ አስተዋጽዎ አድርጓል።
በሃገራችን ለምሳሌ ህውሃትና የህውሃት አክቲቪስቶች የአማራን ህዝብ አንገት የሚያስደፋ ቅጣት ለመቅጣት ዝግጅቱን ለትግራይ ህዝብ በሚዲያ ማሳየት ጀመሩ ሰብተዋል።
Stage 7: Extermination መደምሰስ
ቱትሲዎችን በጥይት፣ በቦምብ ጥቃት፣ በማቸቴ መግደል ተጀመረ። ከ500 ሺህ እስከ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ቱትሲዎች ተገደሉ። ከነበሩበት አካባቢ እንዳይሸሹ መንገዶቹ በሁሉም ማዕዘን ተዘግተው ነበረ።
Stage 8: Denial መካድ
በሩዋንዳ “በዘር ማጥፋት” ፋንታ “የእርስ በእርስ ግጭት” ተብሎ እንዲጠራ ሙከራ ተደርጎ ነበረ። ከ100 ቀናት የዘር ማጥፋት ወንጀል በኋላ ወደ 2 ሚሊዮን የሚጠጉ ሁቱዎች እንዳይቀጡ በመፍራት ሸሹ።
የመንግስት አማካሪዎች (Council Members) የጅምላ ጭፍጨፋውን እንደ የዘር እልቂት አድርጎ ለመሰየም ፈቃደኛ አልነበሩም።
ኢትዮጵያም የኦሮሚያ ፖሊስ የብሔርና የሃይማኖት ግጭት ለማስመስል ሙከራ ተደርጓል በማለት የክህደት ቃል ሰጥቷል። ግድያዎቹ፣ በሰዎችና በንብረት ላይ የደረሱት ጉዳቶች የጅምላ የዘር ጥቃት መሆኑን የመንግስት ባለስልጣኖች እየካዱ ነው። ፖሊስ ጉዳዩን አቅልሎ “ያልተገባ ድርጊት” በማለት አሳንሶታል። ይህ ክህደት ነው።
በኢትዮጵያ በኦሮሞ አክራሪዎች ሲፈጸሙ የነበሩት ዘርንና ኦርቶዶክሳዊነትን ትኩረት ያደረጉ ነበሩ።
ከሩዋንዳ የሚለዩበት ሁለት ነገር አለ። አንደኛው የተገደለው ሰው ቁጥር ማነሱ ሲሆን ሁለተኛው ግድያዎቹ የተፈጸሙት በተለያዩ ጊዜያትና ቦታዎች ስለሆኑ ብቻ ነው። በኦሮሞ አክራሪዎች የተገደሉት ቁጥር እንደ ሩዋንዳ ብዙ ሊሆን ያልተቻለው የሚፈራው ያህል የውጭ ሃይሎች ጣልቃገብነት ባለመኑሩና ከላይ የተጠቀሱትን Organization እና Preparation በበቂ ደረጃ ማድረግ ባለመቻሉ ነው። በአጠቃላይ ስናየው ከላይ የተጠቀሱት የዘር ማጥፋት (ጂኖሳይድ) ስለመፈጸሙ የሚያከራክር ጉዳይ አይደለም። እንደ ሩዋንዳው የጂኖሳይድ አንዱ ገጽታ የመንግስት ተቋማት በወንጀሉ መሳተፋቸው ነው። የኦሮሚያ ፖሊስ የተሳተፈበት፣ ብልጽግና ፓርቲ ውስጥ ያሉ የኦሮሞ አመራሮች የተሳተፉበት ዘርንና ሃይማኖት ላይ ያተኮረ ጂኖሳይድ ነው።
ተጠያቂው ማን ነው?
1ኛ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት
2ኛ ብልጽግና ፓርቲ
በማህበራዊ ገጽ መጠረያቸው ልጅ ግሩም  በኦስሎ ሜትሮ ፖሊታን ዩኒቨርስቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር ናቸው። ጽሁፉ የወሰድነው ከግል ልጅ ግሩም የፌስቡክ ገጻቸው ነው። ጽሁፉ እሳቸውን ብቻ ይወክላል።
 Subscribe to our newsletter!

[newsletter_form type=”minimal” lists=”undefined” button_color=”undefined”]

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *