“Our true nationality is mankind.”H.G.

የኦሮሚያ ብልጽግና አቶ ለማን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮቹን አገደ፤ ራሳቸውን ካረቁ ሊመለሱ በሩ ክፍት ነው!

የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ለሁለት ቀናት በውስጡ የተፈጠሩ ችግሮችን አስመልክቶ  ሲያካሂድ ቆይቶ ማምሻውን ሲያተቃልል አቶ ለማን መገርሳን ጨምሮ ሶስት ከፍተኛ አመራሮችን ከሃላፊነታቸው ማገዱን አስታወቀ።

የፓርቲ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ድርጅቱ ችግሮቹን ለማየት የጀመረውን ስብሰባ ማጠናቀቁን ተከትሎ በሰጡት መግለጫ ፓርቲው በወቅታዊ ሀገራዊ እና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ በመምከር አቅጣጫዎችን አስቀምጧል። እርምጃዎችን እንደወሰደ ይፋ አድርገዋል።

አቶ ለማ መገርሳ፣ ዶክተር ሚልኪሳ ሚደጋ እና ወይዘሮ ጠይባ ሀሰን ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት መታገዳቸውን አቶ ፈቃዱ ይፋ አድርገዋል። ከፍተኛ አመራሩ እና አባላቱ አቋም ይዞ መታገል ላይ ክፍተት እንዳለባቸው መገምገሙን አስታውሰዋል።

Related stories   ማዕድን ቀጣዩ የኢትዮጵያ ጉሮሮ - "የሕዝብ ሃብት ለሚያባክኑ ዝምታ የለም" ታከለ ኡማ

በድርጅቱ ውስጥ ሌብነትም እንደ ችግር መነሳቱን ያወሱት አቶ ፈቃዱ፣ አባላቱም ሆነ አመራሩ ተግባሩን እንዲታገሉ አቅጣጫ መቀመጡን፣ በአመራሩ ውስጥ ውጤት በማስመዝገብ በኩል ክፍተት መኖሩን በግምገማ መነሳቱን አመልክተዋል። በዚሁ መነሻ  እርምጃ እንደተወሰድ ነው የገለጹት። ይሁን እንጂ የትኛው ባለስልጣን በየትኛው ግምገማ እንደተባረረ አልዘረዘሩም።

 

በስብሰባውም ህወሃት እና ኦነግ ሸኔ የታላቁን የኢትዮጵይ ህዳሴ ግድብ ግንባታን እና በሀገሪቱ እየተካሄደ ያለውን ለውጥ ለማደናቀፍ ከውጭ ሀይሎች ጋር ተባብረው እየሰሩ መሆኑን በስፋት መነሳቱንና ለዚህም ፓርቲው ምንማድረግ እንዳለበት መምከሩንም አቶ ፈቃዱ አመልክተዋል።

አቶ ለማ መገርሳ በቪኦኤ ቀርበው ” ተሰሚነት አጣሁ፣ ህዝብ መክሬ የፖለቲካ ውሳኔዬን አሳውቃለሁ” በማለት ከተናገሩ በሁዋላ ድምጻቸው መጥፋቱ ይታወሳል። ዛሬ በወንጀል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር የዋለው ጃዋር መሀመድ አጥብቆ የሚከራከርላቸው አቶ ለማ ” እኔና አብይን ሞት ብቻ ነው የሚለየን” በማለት ደጋግመው መናገራቸው አይዘነጋም። አቶ ለማ የፓርላማ አባል ስላልነበሩ ዶከተር አብይ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ሃላፊነት እንዲይዙ የድርጅት ሊቀመንበርነቱን ስፍራ በፓርቲው ስብሰባ ላይ አምነው መፈቀዳቸው በወቅቱ እጅግ የተደነቀላቸው ተግባር ነበር። አቶ ለማም ሆኑ ሁለቱ የታገዱት ከፍተኛ አመራሮች ራሳቸውን ካረቁ ወደ ፓርቲው እንደሚመለሱ አቶ ፈቃዱ አስታውቀዋል።

Related stories   “የግድቡ ግንባታ ውሃ ይቀንስብኛል የሚለው የግብጽ ጩኸት የማጭበርበሪያና የተለመደ የሃሰት ክስ ነው››

አቶ ለማ ከድርጅት ሃላፊነት ከተነሱ በአሰራር ደንብ መሰረት የመከላከያ ሚኒስትርነታቸውንም እንዲያጡ ይደረጋል።

Subscribe to our newsletter!

[newsletter_form type=”minimal” lists=”undefined” button_color=”undefined”]
0Shares
0