ከትግራይ ክልል የከዱ የፀረ ሽምቅ እና የልዩ ኃይል አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ወደ አማራ ክልል መግባታቸው ተሰማ። ከሰሞኑ ወደ ክልሉ የገቡ የፀረ ሽምቅ እና የልዩ ኃይል አባላት ሰላሳ መሆንቸውን ያስታወቀው ክልሉ ነው። የትግርያ ክልል እስካሁን ያለው ነገር የለም።

የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ከጉዳዩ ጋር አግባብነት ያላቸውን ሃላፊዎች ጠቅሶ እንዳስታወቀው ወደ አማራ ክልል ሽሽተው የገቡት የትግራይ ታጣቂዎች መካከል ሃያዎቹ  አስራ ሰባት ክላሸንኮቭ እና ሦስት ሽጉጦችን እንደታጠቁ የገቡት በደባርቅ በኩል ነው።

Related stories   በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 110 ሺህ ዶላር ተያዘ

የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወርቁ ለምለሙ ለአብመድ ታጣቂዎቹ ወደ አማራ ክልል ሸሽተው አማራ ክልል መግባታቸውን ማረጋገጫ ሰጥተዋል። ለጊዜው ቁጥራቸው የማይታወቅ ተጨማሪ የትግራይ የጸረ ሽምቅና የልዩ ኃይል አባላትም እየከዱ እየገቡ መሆኑ አስተዳዳሪው ገልጸዋል።
አስሩ የትግራይ ልዩ ሃይል አባላት ወደ አማራ ክልል የገቡት በጠገዴ በኩል ነው። ከእነዚህ መካከል ዘጠኙ ከነሙሉ ትጥቃቸው አንዱ ያለ ጦር መሳሪያ እንደገቡ ነው የተገለጸው።
የጸጥታ አባላቱ ሕዝቡ ሀሳቡን በነጻነት ማራመድ አለመቻሉን እና በክልሉ እየተካሄደ ያለውን የጦርነት ቅስቀሳ በመቃወም መክዳታቸውን እንደ ምክንያት እንደገለጹ ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል። “ምርጫ ይካሄድ” የሚለውን ሀሳብ ያልደገፉ በርካቶች ስለመታሰራቸውም እነዚሁ የልዩ ሃይል አባላት መናገራቸውን አቶ ወርቁ አክለው ተናግረዋል።

Related stories   አፍሪካ ህብረት ቁርጠኛነቱን አሳይቷል፤ አውሮፓ ህብረት ምርጫ አልታዘብም አለ

ቀደም ሲል በቆቦ በኩል በተመሳሳይ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ኮብልለው መግባታቸው መገለጹንና የዛሬውን ዜና አስመልክቶ ከትግራይ ክልል በኩል የተሰጠ ምላሽ ወይም ማስተባበያ የለም።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *