“Our true nationality is mankind.”H.G.

ኦነግ ሁሉም ዓይነት የህብረተሰብ ክፍል በግንባሩ እንዲሳተፍ ተሃድሶ መጀመሩን ገለጸ፤ ሸኔ ከ600 በላይ አባላቱን እንዳሰረበት ይፋ አደረገ

ኦነግ ራሱን አድሶ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችን የሚያስተናገድ አሰራር ለመከተል እየሰራ መሆኑንን አመለከተ። ከኦነግ ሸኔ ጋር የመዋቅር ግንኙነት እንደሌለውና ከስድስት መቶ በላይ አባላቱን እንዳሰረበት አስታወቀ። ኦነግ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሊቀመንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ አልተገኙም። መግለጫውንም እንደማያውቁት ነው የሚነገረው።

ግንባሩ ዳውድ ኢብሳን ከሃላፊነት ስለማውረዱም ሆነ የትኛውም ዓይነት ለውጥ ስለማካሄዱ ይፋ ባያደርግም ዛሬ በሂልተን ሆቴል የተካሄደው ጋዜጣዊ መግለጫ በድርጅቱ ውስጥ የአቋም ለውጥ መኖሩን አመላካች ነው። እሳቸው በመግለጫው ላይ ላለመገኘታቸው የቀረበው ምክንያት ደግሞ ” ሃምሌ 21 እና 22 የግንባሩ ማዕከላዊ ኮሚቴ ያደረገውን አስቸኳይ ስብሰባ እውቅና በመንፈጋቸው ሳቢያ በአመራሮቹ መሃል ያለው ክፍተት አጥንቶ ውሳኔ እንዲሰጥ ጉዳዩ በፓርቲው የህግ ኮሚቴ እየታየ ነው” የሚል ነው። ምላሹን ከዚህ ቀደም አቶ ዳውድ ለቢቢሲ ካሉት ጋር የሚመሳሰል መሆኑ ግንባሩ በይፋ ያልተነገረ ሹም ሽር አካሂዶ ይፋ ለማድረግ ቀን እየጠበቀ መሆኑንን አመላካች እንደሆነ አስተያየት እየተሰጠ ነው። መጠነኛ ማስተካከያ የተደረገበት የጀርመን ሬዲዮ ዜና ከዚህ በታች ይነበባል።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) በመንግስት ታስረዋል ያለውን አመራሮች፣ አባላት፣ ደጋፊዎች፣ እንዲፈቱና ተዘግተውብኛል ያላቸው ጽ/ቤቶች እንዲከፈቱለት ጠየቀ፡፡

ግንባሩ ዛሬ በአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በህዝብ እና በመንግስት መካከል ልዩነትን በማስፋት ወደ ስልጣን ለመምጣት ጥረት ያደርጋሉ ያሏቸውን የፖለቲካ ድርጅቶች በመቃወም፤ መንግስትም ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን እገነባለሁ ሲል የገባውን ቃል ተግባራዊ ሊያደርግ ይገባል ነው ያለው፡፡

Related stories   የመ/ሰራዊትን መለያ ለብሶ ከሱዳን ወደ ወልቃይት ሊገባ የነበረ የትህነግ የሽብር ሃይል ተደመሰሰ፤

የኦሮሞ ህዝብ አሁን ላይ ከየትኛውም ጊዜ በላ ነጻነትና ሰላምን ይሻል ያለው የኦነግ መግለጫ ተፈላጊውን ሰላም ለማረጋገጥ የህዝቡን አንድነት የሚያጠናክር የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራር በጋራ መስራት አስፈላጊ መሆኑንን አመልክቷል።
ፓርቲው በመግለጫው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አሁን ላይ አሳሳቢና ውስብስብ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝ ይፋ አድርጓል። ከውስጥና ከውጭ በድርጅቱ ላይ የተጋረጡትን ችግሮችን በአሸናፊነት ለመወጣት በሰላማዊ መንገድ የጀመረውን ትግል አጠናክሮ ለመቀጠል ቁርጠኛ መሆኑንም አስገንዝቧል፡፡

መግለጫው አክሎም ኦነግ የሃገሪቱን ህግና የፓርቲውን መተዳደሪያ ደንብ በማክበር ድርጅቱን በማደስ ይበልጥ ዴሞክራሲያዊ፣ አሳታፊና ሁሉንም ህብረተሰብ ያቀፈ ድርጅት እንዲሆን በማስቻል ረገድ እየሰራ መሆኑን ይፋ አድርጓል። ድርጅቱን ማደስ ሲል በምን ረገድና ምን ዓይነት ለውጥ በማካሄደ እንደሆነ አልዘረዘረም።
በኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል የጎላ ልዩነት እንደሌለ ከዚህ ቀደም ከተደረጉ ውይይቶች ለመረዳት ችያለሁ ያለው ፓርቲው፤ ያሉትን ጥቃቅን ልዩነቶች በመፍታት በጋራ ለህዝብ ጥቅም መቆም እንደሚገባ አሳስቧል፡፡

Related stories   “የግድቡ ግንባታ ውሃ ይቀንስብኛል የሚለው የግብጽ ጩኸት የማጭበርበሪያና የተለመደ የሃሰት ክስ ነው››

ከተለያዩ ማህበረሰብ አቀፍና ለዴሞክራሲ እኩልነት እንታገላለን ከሚሉ የፖለቲካ ተቋማት ጋር ምክክር ለማድረግም ዝግጁነቱን በመግለጽ፣ ይህንንም ለማድረግ ጊዜው አሁን እንደሆእነ በመግለጫው አትቷል።
ፓርቲው አክሎም እንዳብራራው በተለያዩ ጊዜያት መንግስት አንድ እግር በሰላማዊ ትግል ሌላኛውን እግር ደግሞ በጫካ በማድርግ እንዲሁም ስልጣንን በአቋራጭ ለመቀማት ይንቀሳቀሳል ከሚለው ህወሃት ጋር በትብብርም ሆነ አብሮ በመስራት የሚነሳው ክስ መሰረተ ቢስ መሆኑንን ገልጿል።

“ከህወሃት ጋር የጥርጥር እና የስጋት እንጂ የትብብርም ሆነ አብሮ የመስራት ታሪክ የለኝም” ያለው ኦነግ በጫካ የትጥቅ ትግል በማድርግ ላይ ይገኛል ስለተባለው የኦነግ ሸኔ መዋቅርን አስመልክቶ  ከእውቅናው ውጭ መሆኑን አብራርቷል፡፡ እንዳውም በዚህ መዋቅር በሚፈፀሙ እና በሚጠረጠሩ ወንጀሎች ከ600 በላይ አመራርና አባላቶቼ ታስሮብኛል ብሏል።

ዛሬ በሂልትን ሆቴል በተካሄደው ጋዜጣዊ መግለጫ የተገኙት የግንባሩ ምክትል ሊቀመንብር አቶ አራርሶ ቢቂላ፣ የፓርቲው ቃል አቀባዮች አቶ ቶሌራ አደባ እና አቶ ቀጄላ መርዳሳ ናቸው ብቻ ናቸው።

አቶ አራርሳ በመግለጫው ላይ የግንባሩ ሊቀመንብር አቶ ዳውድ ኢብሳ ያልተሳተፉበት ሚስጤር ምን ይሆን? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄም ሃምሌ 21 እና 22 የግንባሩ ማዕከላዊ ኮሚቴ ያደረገውን አስቸኳይ ስብሰባ እውቅና በመንፈጋቸው በአመራሮቹ መሃል ያለው ክፍተት በፓርቲው የህግ ኮሚቴ እየታዬ መሆኑ ነው ያስረዱት።

Related stories   አውሮፓ ህብረት - ላለፉት 28 ዓመታት በኢትዮያ ተላላኪ መንግስት እንደነበር ለኢትዮጵያ ህዝብ አመነ

አቶ ዳውድ አሁን ላይ በሰላማዊ ሁኔታ በቤታቸው እንደሚገኙ በመግለጽ፤ ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ ለደህንነታቸው አስግቷል በተባለው ሁኔታ በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች እየተጠበቁ መደበኛ ስራቸውን በተፈለገ ደረጃ ማከናወን ባለመቻላቸው፤ የፓርቲው መዋቅር የእለት ተእለት ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ጨምረው ገልጸዋል።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ ከተመሰረተበት የፈረንጆቹ ሰኔ 11 ቀን 1976 ጀምሮ ከ40 ዓመታት በላይ በትጥቅ ትግል ካሳለፈ በኋላ በሃገሪቱ የተስተዋለውን የመንግስት ለውጥ ተከትሎ ሰላማዊ ትግል ለማካሄድ በ2011 ዓ.ም መጀመሪያ ወደ ሃገር ቤት መመለሱ ይታወሳል፡፡

 

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0