ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

ኦነግ ዳውድ ኢብሳን ማገዱን በይፋ አስታወቀ፤ ቀበሌና ሰፈር ውስጥ የተቀረቀረው ኦነግ ወደ ተሃድሶ?

ተዳፍኖ የቆየው የኦነግ የውስጥ ለውስጥ ፍትጊያ ወደ መቋጫው ያመራ ይመስላል። አቶ ቀጀላ መርዳሳ ዛሬ ማለዳ ሸገር ላይ ቀርበው አቶ ዳውድ ኢብሳ መታገዳቸውን ይፋ አድርገዋል። በዛው አንድበታቸው የህግና ቁጥጥር ኮሚቴው ውሳኔው ይፋ እስከሚሆን ነው እግዱ ሲሉም ጠቅሰዋል። እሳቸው በዚህ መልኩ ቢያቀርቡትም ዜናው የኦነግ የውስጥ ለውስጥ ትርምስ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ ማምራቱን አመላካች እንደሆነ ነው።

ለሁለት አስርት ዓመታት ኦነግን በመምራት የኖሩት አንጋፋው ዳውድ የድርጅቱን ደንብ ጥሰዋል በሚል ነው የታገዱት። በማህበራዊ ገጾችና ሚዲያዎች የባልደረቦቻቸውን ስም እንዳጠፉ፣ እሳቸው እያወቁት የተካሂደውን ስብሰባ ” ከእኔ እውቅና ውጭ ነው” በማለት መካዳቸው በድርጅቱ ደንብ መሰረት ከፍተኛ የዲሲፒሊን ግድፈት መሆኑንን አቶ ቀጀላ አስታውቀዋል።

Subscribe to our newsletter!

[newsletter_form type=”minimal” lists=”undefined” button_color=”undefined”]

በድርጅቱ የዲሲፒሊን ግድፈት ሲከሰት አጣርቶ ውሳኔ የሚሰጠው የዲሲፒሊንና ቁጥጥር ኮሚቴ ጉዳዩን እንደያዘው አቶ ዳውድም ቀደም ባሉት ጊዚያት መግለጻቸው የሚታወሰ ነው። ዜናውን አስገራሚያ ያደረገው አቶ ዳውድ በደኮሚቴው እንዲቀርቡ የወሰኑት ምክትል ሊቀመንበሩ መሆናቸው ነው።

Related stories   ዶክተር አብራሃም በላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ!

ቀደም ባሉት ቀናት ቢልተን ሆቴል በተሰጠ መግለጫ ቀደም ሲል ያልተለመዱ አዳዲስ ሃሳቦች መነሳታቸው፣ ከዛም ቀናት በሁዋላ የዳውድ መታገድ ከተድበሰበት መውጣቱ ኦነግ በአንድ የሽግግር ሂደት ላይ መሆኑንን አመላካች እንደሆነ አመላካች መሆኑንን ስለ ድርጅቱ የሚያውቁ እየገለጹ ነው።

አምስት ቦታ የተበጣጠሰው ኦነግ በ1982 ወደ አንድ እንዲመለስ አስፈላጊው ሂደት ካለቀና ፊርማ ከሰፈረ በሁዋላ አቶ ዳውድ እንዳከሸፉት የሚያውቁ እንደሚሉት የሂልተኑ መግለጫ በኦነግ ቤት ውስጥ ለውጥ እየተካሄደ መሆኑንን የሚያረጋግጥ ነው።

ከድርጅቱ ያለ አግባብ የተገፉ ልምድ ያላቸውን የቀድሞ አመራሮች እያማከረ እንደሆነ የሚታማው ኦነግ ጊዜው ወደ አንድ የሚመጣበት መሆኑንን በሂልተኑ መግለጫ ማንሳቱ፣ ከሰላማዊ ትግል ውጪ ያሉትን መንገድ ማውገዙ፣ ኦነግ ሸኔ ከ600 በላይ አባሎቹን እንዳሰረበት ማስታወቁና ድርጅቱ ለማናቸውም ዜጎች ክፍት እንዲሆን ጥሪ መቅረቡ አቶ ዳውድ የማያውቁት ወይም ሊያስቆሙት የማይችሉት ለውጥ እየተቀጣጠለ መሆኑንን አመላካች ነው።

ኦነግን በአካባቢ ልጆች ከበው ሆሮ ወለጋ አንድ ወረዳ ቀርቅረውታል በሚል የሚተቹት ዳውድ እሳቸውን ያገደው ቡድን ከቀድሞ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ግንኙነት መጀመሩና በኦሮሞ ጉዳይ ተመሳሳይ አቋም ካላቸው ድርጅቶች ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ለማድረግ ፈቃደኛ መሆኑ የዳውድን የድርጅቱ ቆይታ ጥያቄ ውስጥ የከተተ ሆኗል።

Related stories   አፍሪካ ህብረት ቁርጠኛነቱን አሳይቷል፤ አውሮፓ ህብረት ምርጫ አልታዘብም አለ

ለድርጅቱ ቅርብ የሆኑ እንዳሉት ኦነግ ውስጥ የተፈጠረው አለመግባባት የቆየ ነው። ድርጅቱ ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንታገል የሚሉና ከኦነግ ሸኔ ጋር በሽርክና እንቀጥል የምሉ ሃይሎች ሲሳሳቡ ቆይተዋል። በተለይም ዜግነት መቀየር ያልፈለጉና ወደ መኖሪያ አገራቸው የተመለሱ የድርጅቱ አባላት በጠመንጃ ትግል ማመናቸውና ሸኔን በይፋ በፋይናንስ ለመርዳት መንቀሳቀሳቸው ያላስደሰታቸው ይህንኑ ሲወቅሱ ቆይተዋል።

አሁን ዳውድን ያገደው ቡድን ለዚህ የመስላል ” ኦነግ በውጭ አገር አመራር የለውም” ሲል በይፋ ያስታወቀው። ውጪ ባሉ ወገኖችና በተወሰኑ የኦነግ አመራሮች የሚደገፈው ሸኔ አባላቱን እንዳገተበት፣ እንደማይደግፉት ትኩረት ሰጥቶ የተናገረው። የኦነግ የውጭ ምዕራፍም ቢሆን በተመሳሳይ በሁለት ሃሳብ ተከፍሎ እንደሚገኝ የሚናገሩት ክፍሎች ” ኦነግ ወደ መጨረሻው የለውጥ ጎዳና እያመራ ነው” ሲሉ እየተደመጡ ነው።

Related stories   የ80ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን በአዲስ አበባ ተከበረ

ኦነግ ቅርፊቱን ልጦ ወደ ለውጥ እያመራ መሆኑ ይፋ የሚታይ ቢሆንም አቶ ዳውድ አሁን ድረስ እየሆነ ላለው ጉዳይ እውቀና አይሰጡም። ቢቢሲ አማርኛ ከስር ስር እየተከተለ የሚያነጋግራቸው አቶ ዳውድ መታገዳቸው ይፋ መሆኑንን ተከትሎ ምን እንደሚሉና ምን እርምጃ እንደሚወስዱ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም። ኦነግ ግን በምክትል ሊቀመንበሩ እየተመራ መሆኑንን ድርጅቱ አስታውቋል።

በምክትል ሊቀመነበሩ የሚመራው ኦነግ ከተከፋፈለው ኦነግ አመራሮች፣ ከቀድሞው መስራች አመራሮች ጋር የጎንዮሽ ንግግር ማድረግ የጀመሩ ሲሆን ጠቅላላ ጉቤል ለማካሄድ እየሰራ መሆኑ ታውቋል።

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0
Read previous post:
Ethiopia: State Aspires to Cover 135 Thousand Hectares of Land With Crops

By Lakachew AtinafuGambela State Agriculture and Natural Resource Bureau said the seed coverage in the...

Close