“Our true nationality is mankind.”H.G.

ጥቁር እና ነጭ – « በኢትዮጽያ ልክ »

ቀውሱን የሚፈታ ወይም ለቀውስ ግዜ የተሰራ ሌላ ጠንካራ መሪ በሌላኛው ጠርዝ / The other side of coin , Head or Tails / ያስፈልጋል ። ይህ እሳቤ ደግሞ ሀገራችን ሁለት ዶክተር አብዮችን ትጠይቃለች / ለጥቁርና ለነጩ / እንደማለት ሊሆን ነው ። ይህ መቼም ፖለቲካዊ ምጸት / Satire / ነው


By Alemayehu Gebeyehu

« በኢትዮጽያ ልክ » ዶክመንታሪ የታዩ የመናፈሻና የመዝናኛ ስራዎች በእጅጉ አስደሳቾች ናቸው ። በአንድ በኩል የከተማዋን ገጽታ ሳቢና ማራኪ ፣ በሌላ መልኩ የነዋሪዎቿንም ሆነ የጎብኚዎችን የመዝናናት መንፈስ ምቹ በማድረግ የላቀ ሚና ይጫወታሉ ።

ሞዴል ስራዎቹ የዶ/ር አብይን የልማት አተያይና የምናብ ስፋታቸውን አንጸባርቋል ። ህልም በወረቀት ላይ ሰፍሮ እንዴት በአጭር ግዜ ተግባራዊ ሊደረግ እንደሚችል ትምህርት የሚወሰድባቸው ናቸው ። በመሆኑም ስስት ያልገባበት ምስጋና መወደስ ይገባቸዋል ። የድሃ ሀገር መሪዎች በሁሉ ዘርፍ ጨካኝ ውሳኔ ሰጪ መሆን ይጠበቅባቸዋል ። መሪዎች ወለም ዘለም የሌለው አመራር ሰጪ ከሆኑ ድህነትን ለማስገበር በሚደረገው ጥረት ላይ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ ። በአስቸጋሪ ተራራና መልከአምድር ላይ የተሰሩ አይነግቡ የልማት ውጤቶች ያለጭካኔ የተገኙ ውጤቶች አይደሉም ። ዶ/ሩ ጨክነው በማቀድ እንዲፈጸም በመጣራቸው የልማቱ ባለሙያዎችም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ አይን የሚሞሉ ስራዎችን እንዲያከናውኑ መንገድ ከፍቶላቸዋል ።

Related stories   አገርን የከዱ ተደመሰሱ፤ የሳተላይት መገናኛና መድሃኒት " ጁንታው" እጅ ሳይገባ ተያዘ

በኢዮቤልዩ ቤተመንግስት የታዩት ቅርሶችና ሃብቶች ሌሎች አስደማሚ ጉዳዮች ነበሩ ። ሁለት ነገሮች ገርመውኛል ። አንደኛው ገንዘብ ፣ መሬት ፣ መርከብ ወዘተ አይምርም የሚባለው ወያኔ በዘመኑ የሃይለስላሴን የወርቅና የብር ሃብቶች እንዴት ንቆ አለፋቸው ? ከሁለት መቶ በላይ የተቆጠሩት ምርጥ አውቶሞቢሎች ትልቅ ቅርስ በመሆናቸው ለጨረታ ቢቀርቡ ቅርስ አሰባሳቢ ፈረንጆች በርካታ ቢሊየኖችን እንደሚከፍሉባቸው ግልጽ ነው ። መርከብን የሸጠ አእምሮ ይህን ሳያስብ መቅረቱ ወይ እንደ ተአምር ይቆጠራል አሊያም « የአክሱም ሃውልት ለደቡቡ ምኑ ነው ? » ያሉት አቶ መለስ ዜናዊ የተደበቀ ስብእና አላቸው ።

ዶ/ር አብይ የአጼ ሃይለስላሴን ሃብት በማልማት ረገድ እንዴት ቅድሚያ አልሰጡትም የሚለው ሃሳቤ ነው ሁለተኛው ግርምቴ ። ምክንያቱም በእኔ እምነት ለሀገሪቱ በርካታ የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት ረገድ የቤተመንግስቱ ቅርሶች ከመናፈሻዎቹ የሚበልጡ ናቸው ። ፈጥኖ ከሚገኝ ገንዘብ ዘⷝይቶ የሚደርስ አእምሯዊ ሃብት ይሻላል ካልተባለ በቀር ። የውጭ ሀገር ልምዶች እንደሚያሳዩት ቱሪስቶች ይህን መሰል እድሜ ጠገብ ከገበያ የወጡ መኪናዎችንና የታሪካዊ መሪን ሃብት ለመጎብኘት ታላቅ ጉጉት አላቸው ።

Related stories   የመ/ሰራዊትን መለያ ለብሶ ከሱዳን ወደ ወልቃይት ሊገባ የነበረ የትህነግ የሽብር ሃይል ተደመሰሰ፤

ዶ/ር አብይ ልማት ለማከናወን ቆራጥ መሆናቸውን ካሳዩን በሰላምና ፍትህ ጥያቄ ላይ መለሳለስ ለምን አስፈለጋቸው መባሉ አይቀሬ ነው ። ምክንያቱም ሁለቱ ርእሰ ጉዳዮች የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ስለሆኑ ። ጎፈርና ዘውድ ወይም ጥቁርና ነጭ እንደማለት ። ነጩን አሸንፈው ለጥቁሩ እጃቸውን የሰጡት ፍላጎት በማጣት ነው ወይስ በአቅም ማነስ ወደሚል ጥያቄ ስለሚያንደረድር ። በሁለት አመት ውስጥ በከተማ ልማት ተአምር የተሰኘ ውጤት ሲገኝ በሁለት አመት ውስጥ ‹ አትዮጽያ ውስጥ መንግስት የለም እንዴ ?› ያስባለ ዘግናኝ ግፍ ፣ በደልና ጭፍጨፋ በተደጋጋሚ አስተናግደናል ። አንዱ ላይ ጠንክሮ ሌላውን ቸል ማለት እንደሳቸው ፍልስፍና ‹ የተደመረ › ውጤት አያስገኝም ። ምነው ቢሉ መንግስታዊ ይለፍ የተሰጠው ግፈኛውና ጨፍጫፊው ቡድን ነገና ከነገ ወዲያ እነዚሁኑ የልማት ስራዎች አያወድምም ብሎ ለመከራከር ዋስትና ስለማይሰጥ ።

Related stories   ትህነግን በብሄራዊ ውይይት እንዲሳተፍ የሚደረግ ግፊት መኖሩን መንግስት ይፋ አደረገ፤ " ፍጹም ተቀባይነት የለውም" ብሏል

በልማቱ ላይ የታየው የጭካኔ አመራር ሰላምና ፍትህን በማስጠበቅ ረገድም ጨከን ያለ አመራርና ክትትል ቢሰጠው ኖሮ ውጤቱ የተለየ እንደሚሆን ይታመናል ። በአንድ ስርአት ውስጥ ሁለቱ ዘርፎች ሁለት የተለያየ ሳይንሳዊ እይታ የሚፈልጉ ናቸው ከተባለ ግን ዶ/ር አብይ የሰላም ግዜ ብቻ ጎበዝ መሪ ናቸው ወደሚባለው አመክንዮ ይወስደናል ። ይህ ማለት በተረኝነት የናወዙ ሽብር ፈጣሪዎችና ጦርነት ደላቂዎች ሀገርን ካመሱ ለቀውሱ የማያዳግም ሳይንሳዊ ምላሽ ሰጥቶ ፊትን ወደልማት ለማዞር ይክብዳል እንደማለት ነው ። ቀውሱን የሚፈታ ወይም ለቀውስ ግዜ የተሰራ ሌላ ጠንካራ መሪ በሌላኛው ጠርዝ / The other side of coin , Head or Tails / ያስፈልጋል ። ይህ እሳቤ ደግሞ ሀገራችን ሁለት ዶክተር አብዮችን ትጠይቃለች / ለጥቁርና ለነጩ / እንደማለት ሊሆን ነው ። ይህ መቼም ፖለቲካዊ ምጸት / Satire / ነው ። ይህ እንዳይሆን ያኛውንም ጠርዝ ይድፈሩ ነው የምለው ። በህግ ክፍተት ላይ የጨከነ አልሚ ይሁኑ ነው የምለው ። መደመር የረሳውን የበደል መቀነስ መላ ያበጁለት ነው የምለው ።

 

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0