የዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ ከማስቻሉ በፊት ኦ ኤም ኤን አቶ ጃዋር መታመማቸውን፣ ፊታቸው ማበጡንና ድካም ድካም ስለሚሰማቸው ቤተሰቦቻቸውን ለማነጋገር አለመቻላቸውን ጠቅሶ በድገተኛ ዜና አሰምቶ ነበር። በዚሁ ዜና “የአቶ ጃዋር እህት ነኝ” በስልክ አየሁ ያሉትን ከገለጹ በሁዋላ ” ምንው ዝም አላቹህ፣ ተነሱ፣ ጃዋር እስር ቤት ሆኖ ዝም ይባላል ወይ … ” የሚል ጥሪ አቅረበው ነበር።

እህታቸው እንዳሉት ዛሬ ችሎት የቀረቡት አቶ ጃዋር መታመማቸውን አስታውቀዋል። ቢቢሲ እንደዘገበው አቶ ጃዋር ቶሎ ወደማረፊያ ቤት መመለስ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል። ወደ ውጪ ወጥተው እረፍት እንዲያደርጉ ጠይቀው ችሎቱ በመፍቀዱ ወደ ውጪ ወጥተው አየር እንዲወስዱ ተደርጓል።

አቃቤ ህግ ችሎቱ መስተጓጎሉን ጠቅሶ መግለጫ አውጥቷል ሙሉውን እዚህ ላይ ይንብቡ በመግለጫው ሆን ተብሎ በረባ ባልረባ ምክንያት የፍርድ ሂደቱ እንዲስተጓጎል መደረጉን የገለጸው ማስረጃ ” ህዝብ እንዲያውቅ ” ሲል ” ባሰራጨው መግለጫ “…አላግባብ ከሚቀርቡ አቤቱታ እና ይግባኞች ጀምሮ፣ አልተዘጋጀንም ተለዋጭ ቀጠሮ ይሰጠን፣ ዳኛው ፈገግ ብሏል እና ይቀየርልን በማለት በሰበብ አስባቡ የፍርድ ሂደቱን ለማደናቀፍ በተጠርጣሪዎቹ በኩል የሚደረግ ጥረት እንዳለ ግልጽ ሆኗል” ብሏል። አያይዞም ” ይህን እውነታ ህዝቡም ሆነ የሚመለከታቸው አካላት እንዲገነዘቡ እና በአፋጣኝ ፍትህ እንዲረጋገጥ ከምናደርገው ጥረት ጎን እንዲሰለፉ ጥሪያችንን እያቀረብን ማንም ይሁን ማን ከህግ በላይ መሆን የማይቻል መሆኑን በአጽንኦት ለመግለጽ እንወዳለን” የሚል ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

Related stories   “ትህነግ ከጁንታነትም ወርዶ በየጫካው ተሹለክላኪ የእህል ሌባ ሆኗል፣ ከያለበት እየታደነ ነው “ሜ/ጀ መሐመድ ተሰማ

አቶ ጃዋር በአሜሪካን አገር የሚገኙ ቤተሰባቸውን “በቪዲዮ ኮንፍረንስ ማናገር እፈልጋለሁ ” ሲሉ ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ጠይቀዋል። ጨምረውም በራሳቸው ሐኪም ህክምና ማግነት እንዲችሉ እንዲደረግ  ጥያቄ ማቅረባቸውን ችሎቱን የተከታተሉ ሚዲያዎች ዘግበዋል። ዳኛውም ትዕዛዝ ሰጥተዋል።

ቀጠሮ የያየዘው በእነ አቶ ጃዋር መሀመድ መዝገብ የቅድመ ምርመራ ጉዳያቸው እየታየ ያሉ 14 ተጠርጣሪዎች ላይ አቃቤ ሕግ ምስክሮቹን ለማድመጥ እንዲሁም ችሎቱ ባለፈው ሳምንት ያሳለፋቸውን ትዕዛዞች አፈጻጸም ለመስማት እነደነበር ይታወሳል።

Related stories   አስከሬን እንዲለቀም ታዘዘ - ትህነግ የአጽም ፖለትካ ድራማ ይፋ ሆነ

ዛሬ ለችሎቱ የአምስት ተጠርጣሪዎች ውጤት የቀረበ ሲሆን ጌቱ ተረፈ፣ በሽር ሁሴን፣ ኬኔ ዱኔቻ፣ ሰቦቃ ኦልቀባ፣ ዳዊት አብደታ ኮቪድ-19 እንደተገኘባቸው የሚያረጋግጥ ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተጻፈ ባለ ሁለት ገጽ ደብዳቤ ቀርቧል።

የጃዋር ጠባቂ ከነበረው መካከል አንዱ ታምራት ሁሴን ኮቪድ-19 እንደተገኘበት ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ አሳውቋል። በሌላ በኩል ፍርድ ቤቱ የተቀሩት ዘጠኝ ተጠርጣሪዎች የኮሮናቫይረስ ምርመራ ውጤት እንዲቀርብ ከዚህ በፊት ማዘዙን አስታውሶ ፖሊስ ይህንን ውጤት በቀጣይ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ይዞ እንዲቀርብ የቃል ትዕዛዝ ሰጥቷል።

አቶ ጃዋር አሞኛል በማለት በተደጋጋሚ ችሎቱን በማቋረጥ እየወጡ ምስክር ማዳመጥ ባለመቻሉ ለሐሙስ ነሐሴ 14 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

Related stories   ደመቀ መኮንን በፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሚመራ የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ጋር ተወያዩ

Subscribe to our newsletter!

[newsletter_form type=”minimal” lists=”undefined” button_color=”undefined”]

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *