“Our true nationality is mankind.”H.G.

” የሸዋ ኦሮሞዎች በተለይ ቱለማዎች ነፍጠኛ ናቸው ” ሴና ጀምጀሞ ንግግራቸው ተቃውሞ አስነስቷል

የሸዋ ኦሮሞዎች በተለይም ቱለማዎች ከነፍጠኛ ተርታ እንደሚመደቡ ስልሳ የሚጠጉ የኦሮሞ ሴቶችና የወጣት ድርጅቶችን የሚያስተባበረው የኦሮሞ ውርስ አመራር ተሟጋች ማህበር ዋና ዳይሬክተር ሴና ጀምጀሞ በይፋ ተናገሩ። ንግግራቸው ከወዲሁ ቅሬታ አሰነስቷል። ዳይሬክተሯ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከሁለት ወር በሁዋላ በመሪነት ለመቀመጥ ስለማይችሉ ባስቸኳይ የሽግግር መንግስት እንዲመሰርቱ ጥሪ አሰምተዋል።

ሴና ከቪኦኤ አማርኛ / ለ14 ደቂቃ ጀመሮ ያድምጡ/ጋር በትናንትናው እለት ባደረጉት ቃለ ምልልስ ” ኦሮሞዎች በተለይም ቱለማዎች ነፍጠኛ ናቸው” ያሉት ነፍጠኛ ስለሚባለው ስያሜ እንዲያብራሩ ሲጠየቁ ነው።

የተወሰኑ የማህበረሰብ አባላት ላይ በመሳሪያ ሃይል የማይፈልጉትን እንዲቀበሉ ወይም እንዲጫንባቸው የሚያደርጉ ነፍጠኞች እንደሚባሉ ያስረዱት ሴና ጉራጌ፣ አማራው  … በማለት ዘርዝረው ነፍጠኞች እንደነበሩባቸው ጠቅሰዋል። አያይዘውም ኦሮሞች በተለይም ቱለማዎች ነፍጠኞች መሆናቸውን በይፋ ገልጸዋል።

በቁጥር ከፍተኛ እንደሆኑ የሚነገርላቸውንና ከሜጫ ጋር ወንድማማች የሆኑትን ቱለማዎች ለይቶ በነፍተኛነት መመደብ ሴናን ዋጋ እንደሚያስከፍላቸው መግለጫቸውን የሰሙ ለዛጎል ተናግረዋል። የዲሲ ነዋሪ የሆኑትና የዘረወትር የዛጎል ተባባሪ አቶ ገመቹ “ይህ ከኦሮሞም የተለየን ኦሮሞዎች ነን የሚለው አስተሳሰብ በተለይም ከአንድ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ነኝ ከምትል እህታችን ኦሮሞ መሰማት ያሳዝናል” ብለዋል።

አቶ ገመቹ አክለውም ንግግሩ አዲስ እንዳልሆነባቸው አስረድተዋል። ሰላሌን፣ ከረዩን ጨምሮ ድፍን ምስራቅን ሰሜን ኦሮሚያን፣ አርሲ፣ደቡብ ኦሮሚያን አጠቃሎ በነፍጠኛነት መፈረጅ ከዲቃላ ፖለቲካ አራማጅ ሃይሎች ጋር ያላቸውን ህብረት የሚያሳይ ውስጥ ውስጡ የሚብላላ ሃሳብ ነው። ቱላማዎች የራሳቸውን መልስ ይሰጣሉ። ጉዳዩ በቀላል የሚታይ አይሆንም ብለዋል።

Related stories   ይናገር ደሴ -"እየተዶለተብንና እየተቀመመልን ያለው ኢትዮጵያን የመበተን ሴራ ጉዳይ ለእኛ ኢትዮጵያውያን አዲስ ነገር አይደለም"

በሌላ በኩል ሴና የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከሁለት ወር በሁዋላ በስልጣን መቀጠል ስለማይችሉ ባስቸኳይ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ማድረግ እንዳለባቸው አመልክተዋል። በቅርቡ በኦሮሚያ የተፈጸመውን ማንነትና እምነት ላይ ያተኮረ ጥቃት ” ልቤን ሰብሮኛል” ሲሉ ነው የኮነኑት። ትግሉ ከስርዓቱ ጋር እንጂ አብረውን ከኖሩ ጎረቤቶች ጋር ሆኖ ሳለ የተፈጸመው ግድያ ” መውረዳችንን ይሳያል፤ ያሳዝናል” በማለት ገልጸውታል። አያይዘውም የታሰሩ የፖለቲካ መሪዎች በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጥሪ አቅረበዋል።

ጥያቂው ሴናን ሲጠይቃቸው “በ21ኛው ክፍለ ዘመን ባረጀ ትርክት መኖርና መጋጨት ያለ አንዳች ምክንያት የሞተ ፈረስ እንደመጋለብ ይቆጠራል” ሲል ነበር አስተያየት ሰጪዎችን ጠቅሶ ጥያቄውን የሰነዘረላቸው ሊንኩን በመጫን ከ14ኛው ደቂቃ በሁዋላ ያለውን ያድምጡ

የቱለማ ኦሮሞዎች ራሳቸውን በማደራጀት ኢትዮጵያዊነታቸውን ለድርድር የማያቀርቡ፣ በአብሮነት የሚያምኑ መሆናቸውን በተደጋጋሚ መግለጻቸው ይታወሳል።

ሊንኩ ይህ ነው ይጫኑ

ሴና ከዚህ ቀደም ይህን አስተያየት ጽፈው ነበር ሙሉውን ኦፕራይድ ላይ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑና ይመለከቱ።

Related stories   መካከለኛዉ ምሥራቅ ሌላ ዘመን ሌላ ጥፋት

Focus on Oromia

Abiy faces so much expectation and a great responsibility within a very limited time but, he is not a magician. He can’t change a 28-year-old system overnight. Nevertheless, every step he takes will matter for his party, for his people, for EPRDF and for the country as a whole. Now more than ever, he cannot become complacent.

Both Abiy and his party must understand, they cannot deliver anything meaningful if the old system remains intact. The old guard cares more about EPRDF’s legacy and organizational culture than the country’s future. Abiy may have saved the OPDOs from exiting EPRDF but he should not let the party undermine him as they did with his predecessor, Hailemariam Desalegn.

The OPDO knows that the current system exists only if they are in it. TPLF knows that too but it largely gave into OPDO’s demands with the hope of placing their trustees in positions of power, making it impossible for Abiy to implement his vision. He must stay vigilant, guard against TPLF’s factionalism and cronyism. Meanwhile, Lemma should be given the space to finish and consolidate the reforms now underway in Oromia. He stepped aside and nominated Abiy for the premiership arguing that he needed more time to build a strong Oromia. He is right. True change lies in Oromia whether that is political freedom or economic empowerment. It is also here we must focus our attention.

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0