“Our true nationality is mankind.”H.G.

ምስራቅ ዕዝ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጠ፤ የጥፋት መንገድን በትዕግስት እንደማይመለከት አስታወቀ

ከምስራቅ እዝ ጠቅላይ መምሪያ የተሰጠ ጥብቅ ማሳሰቢያ
የተከበራችሁ የድሬዳዋ አስተዳደር ነዋሪዎች፤ እንደሚታወቀው የቀጠናችን ሰላም አስተማማኝ እንዲሆን እስካሁን ከሰራዊታችሁ ጋር በጋራ በመሆን ባካሄዳችሁት ያልተቋረጠ ጥረት የአካባቢያችን ሰላም እየተሻሻለ እንደመጣ የሚታወቅ ጉዳይ ነው::
በተለይም የአካባቢው ሽማግሌዎች እና ወጣቶች ባደረጋችሁት ትብብር በቀጠናችን ሊደርሱ የሚችሉ አደጋዎችን በጋራ እየተከላከልን መጥተናል::
ሠራዊታችን በአንድ መልኩ የተሰጠውን ህገ-መንግስታዊ ሃላፊነት በትዕግስት እና በአርቆ አስተዋይነት ለመፈፀም በርካታ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል::
እንደሚታወቀው ሠራዊታችን የህዝባችንን ሠላም እና ደህንነት የመጠበቅ ህገ-መንግስታዊ ኃላፊነት እና ግዴታዎች የተሸከመ ሰራዊት ሲሆን ከማንኛውም ፖለቲካ ፓርቲ እና ድርጅት ወገንተኝነት በፀዳ መልኩ ተልእኮውን እየተወጣ ይገኛል::
ስለሆነም ማንኛውም ዜጋ አለኝ የሚለውን ተቃውሞ በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድ ህጋዊ አቅጣጫና ስርዓት ተከትሎ እንዲፈፅም ሀገራዊና ህገ-መንግስታዊ ግዴታችንን እየተወጣን እንገኛለን::
ማንኛውም አካል ህገ-መንግስቱንና ህጋዊ መንገድን ያልተከተለ አቅጣጫን የሚያራምድ ከሆነ ደግሞ በህጋዊ መንገድ የመቆጣጠር ሃላፊነት የሁሉም ዜጋና የሁሉም የፀጥታ ሀይል ሀላፊነት መሆኑ የሚታወቅ ነው::
በዚሁ መሰረት ከሰላማዊ ህጋዊና ዲሞክራሲያዊ ውጪ የሚደረገውና ማንኛውም ብጥበጣና አመፅ ተቀባይነት የሌለው ሲሆን አሁንም ህዝባችን እንደተለመደው ማናቸውንም እንቅስቃሴ በሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ መንገድ እንዲከናወንና ፀጥታ የማስከበር ሀላፊነታችንን በጋራ እንድንወጣ ለማላው ህዝባችንን ጥሪ እያቀረብን ከዚሂ ውጪ የሚደረግ የጥፋት መንገድ ግን በትዕግስት የማንመለከተው መሆኑን እንገልፃለን::
ስለሆነም መላው የአስተዳደሩ ነዋሪዎች፣የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች የህግ የበላይነትን ለማስከበር ከመከላኪያ ሰራዊታችን ጎን በመቆም አጥፊዎች ለህግ እንዲቀርቡ በጋራ ለመስራት በድጋሚ ጥሪያችንን እናቀርባለን::
የምስራቅ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ
ነሀሴ 12 ቀን 2012 ዓ.ም

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   “የግድቡ ግንባታ ውሃ ይቀንስብኛል የሚለው የግብጽ ጩኸት የማጭበርበሪያና የተለመደ የሃሰት ክስ ነው››
0Shares
0