“Our true nationality is mankind.”H.G.

በእነ እስክንድር ነጋ ላይ ክስ እንዲመሰረት ብይን ተሰጠ

NtJDO

በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ተረኛ ችሎት አቃቤ ህግ በአቶ እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮልና ቀለብ ስዩም ላይ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ ክስ እንዲመሰርት ብይን ሰጠ። አቃቤ ህግ ሁለት የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን አሰምቶ አጠናቋል።

ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት ክስ እስከምመሰርት ድረስም ተጠርጣሪዎች በማረፊያ ቤት ይቆዩልኝ ብሎ አቃቤ ህግ ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

ተጠርጣሪዎች በበኩላቸው ክስ እስከሚመሰረትብን ድረስ በዋስ ወጥተን በውጭ እንከታተል ሲሉ ያመለከቱ ሲሆን አቃቤ ህግ ተጠርጣሪዎቹ ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት ክስ ሲመሰረት የተጠረጠሩበት ወንጀል ዋስትና የሚያስከለክል በመሆኑ በማረፊያ ቤት እንዲቆዩልኝ ሲል የዋስትና ጥያቄውን ተቃውሟል።

ጉዳዩን የተከታተለው ፍርድ ቤትም ተጠርጣሪዎች ክስ እስከሚመሰረት ድረስ በማረፊያ ቤት እንዲቆዩ እና አቃቤ ህግ በ15 ቀናት ውስጥ ክስ እንዲመሰርት ብይን ሰጥቷል።

ፋና

Share and Enjoy !

0Shares
0
0Shares
0