በዋናነት የኦነግ ሸኔ ሰራዊት ይንቀሳቀስባቸዋል በሚባልባቸው አካባቢዎች መንግስት የኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎት በማቋረጥ ግንኙነታቸውን አግዶ ባካሄደው ከበባ የተሳካ ውጤት እንዳስመዘገበ በገለጸ ሰሞን ጃል መሮ በሰይፈ ነበልባል ሬዲዮ በቅርቡ ኦሮሚያን እንደሚቆጣጠሩ ይፋ አድርጎ ነበር። ለዚህ ማስተባበያ ይሁን ምላሽ ባይታወቅም የኦሮሚያ የጸጥታ ቢሮ ሃላፊ ” አሁን የቀረው ቃርሚያው ነው። ኦነግ ሸኔ ክፉኛ ተመቶ የተረፉት ተበትነዋል” ሲሉ መግለጫ ሰጠዋል። የተበተነው ሃይል ይሁን ሌላ ባይረጋገጥም አሁን እንደተሰማው ሰላሳ ሁለት የአማጺው ቡድን አባላት በሰላም እጅ ሰጥተዋል።

ኦፕሬሽኑ ከተጠናቀቀ በሁዋላ መንግስት በይፋ አልገለጸም እንጂ በርካታ የኦነግ ሸኔ ሰራዊት ተማርከዋል። ህጻናት ይበዙበታል። ሰፊ ቁጥር ያለው ሃይልም መደምሰሱን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ በዛው ሰሞን ለዛጎል ጥቆማ ሰጥተው ነበር። እነዚህ ወገኖች እንዳሉት የተበተነው ሃይል ከተሰባሰበ ዳግም ችግር ሊፈጥር እንደሚችል አልሸሸጉም።

ዛሬ ላይ በኦሮሚያ ከአማጽያኑ በኩል የጦር ሜዳ ውሎን አስመልክቶ የሚሰማ ነገር ባይኖርም፣ አማጽያኑ አሉበት በሚባልባቸው አካባቢዎች ሄድ መለስ የሚል እንቅስቃሴ እንዳለ ከስፋዎቹ የሚወጡ መረጃዎች ያስረዳሉ። ይሁን እንጂ ማስረጃዎቹ እንደቀድሞው በሚታወቁ መገናኛዎች በይፋ የሚነገሩ አልሆኑም።

Related stories   የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አገር ለማተራመስ በህቡዕ የተደራጁ በርካታ ግለሰቦችን ከነመዋቅራቸውና መስሪያዎቻቸው በቁጥጥር ስር አዋለ፤

የኦነግ ሸኔ ሰራዊት ዜና በተቀዛቀዘበትና በኦሮሚያ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ የሚጠይቅ 12.12.12 የሚባል የአድማ ” አዋጅ” በታወጀበት ዕለት ሰላሳ ሁለት የኦነግ ሸኔ የሰራዊት አባላት እጅ መስጠታቸውን የመንግስት ሚዲያዎች ይፋ አድርገዋል።

ኦነግ ሸኔ አባላቱ እጅ ስለመስጠታቸውም ሆነ ዜናው ስላስተላለፈው መልዕክት ይህ እስከታተመ ድረስ ይፋዊ መግለጫ አልሰጠም። ወይም በተለምዶ አሉበት ድረስ ደውለው በሚያገኙዋቸው ሚዲያዎች አላስተባበለም። ዜናው በምስል የተደገፈና እጅ የሰጡት ታጣቂዎች ቃላቸው የሰፈረበት ነው።

የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ስፍራ ለመቀየር ሲሞክሩ ድንገት ተከበው ጥቃት የደረሰባቸው ሲልሆን ከሃምሳ በላይ የሚጠጉ መማረካቸውን ለጉዳይ ቅርብ የሆኑ አመልክተዋል። ዜናው በምስል ተደግፎ በቅርቡ ሃይሉ ለምን ስፍራ ለመቀየር እንደፈለገ ከነ ሙሉ መረጃው ይፋ እንደሚሆን ግምታቸውን ሰጥተዋል። እጃቸውን ሰጡ ስለተባሉት ሰላሳ ሁለቱ የኦነግ ሸኔ አባላት ኢዜአ የሚከተለውን ዘግቧል


የጥፋት ተልእኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 32 የኦነግ ሸኔ አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው በምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ እጃቸውን ለመንግሥት መስጠታቸው ተገለጸ።
ኦሮሞን ነጻ እናውጣ በሚል ሽፋን ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናትን የመግደል፣ የሕዳሴውን ግድብን የማደናቀፍና ሌሎች የመሠረተ ልማት ተቋማትን የማጥቃት ተልእኮ ተቀብለው እንደነበርም ገልጸዋል፡፡
እጃቸውን ከሰጡ የኦነግ ሸኔ አባላት መካከል አቶ ገልማ ቡሌ በትግል ስም ‘ዲና ራሳ’ የተባሉት የጥፋት ተልእኮውን ለማሳካት ወታደራዊ ስልጠና መውሰዳቸውን ተናግረዋል፡፡
የጥፋት መንገድን በመከተል የክልሉን ሕዝብ ነጻ ማውጣት እንደማይቻል በመገንዘብ፣ ችግርም ካለም በውይይት እና በድርድር በመፍታት በሰላማዊ መንገድ ለመታገል እጃቸውን እንደሰጡም ገልጸዋል፡፡
ሌላው አበበ ጂሎ በትግል ስም ‘አብዲ ሰባ’ የተባለው ደግሞ “ኦሮሞ ተበድሏል” በሚል ተታልሎ እና ወታደራዊ ስልጠና ወስዶ ለጥፋት ተልእኮ ኦነግ ሸኔን እንደተቀላቀለ ተናግሯል፡፡ “የኦነግ ሸኔ ዓላማ የሰው ሕይወት ማጥፋት፣ መዝረፍና በመሰረተ ልማት ላይ ጉዳት ማድረስ በመሆኑ በዚህ ተግባር መቀጠል ስላልፈለኩ እጄን ለመንግስት ሰጥቻለሁ” ብሏል፡፡
ሌላው አጋ አረቦ በትግል ስም ‘ቄራንሶ ሰባ’ የኦነግ ሸኔ የትግል ስልት እና ዓላማ ከኦሮሞ ባህላዊ ስርዓት ያፈነገጠና የክልሉን ህዝብ የማይመጥን በመሆኑ ወደ ሰላማዊ ሕይወት ተመልሻለሁ ብሏል፡፡
የሰው ሕይወት እያጠፉና የመሰረተ ልማትን እያወደሙ ለኦሮሞ ህዝብ እታገላለሁ ማለት እራስን ማታለል ስለሆነ ከዚህ በኋላ ዳግም እንደማይሳሳትና እንደማይቀበለውም ገልጿል።
የኦሮሞ አባ ገዳዎች እና ቃሉዎች ኦነግ ሸኔ ሰላማዊ የትግል አማራጭ እንዲከተል ጥያቄ አቅርበው እንደነበርም አስታውሷል፡፡
የምዕራብ ጉጂ ዞን አሰተዳደሪ አቶ ተፈሪ ወንድይፍራው በኦሮሞ ህዝብ ስም ጫካ መሽጎ የሰው ሕይወት የሚያጠፋ፣ ንብረት የሚዘርፍና የመሰረተ ልማት ላይ ጉዳት የሚያደርስን ኃይል አንታገስም ብለዋል፡፡
በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በኦነግ ሸኔ ተመልምለው በህዝብ ላይ ጥፋት ሲፈጽሙ የነበሩ ወገኖች ዓላማው ሲገባቸው ወደ ሰላማዊ ሕይወት መመለስ መጀመራቸውንም ገልጸዋል፡፡
ከኦነግ ሸኔ የጥፋት አጀንዳ ተቀብለው የሚሰማሩ የጥፋት ኃይሎችን የዞኑ ህዝብ በየቀኑ እያጋለጠና አሳልፎ እየሰጠ እንደሚገኝም አስረድተዋል።

Related stories   "የአውሮፓ ህብረት ታዛቢዎችን ላለመላክ የወሰነው የማይታዘዝና የማያጎበድድ መንግሥት ይመጣል የሚል ስጋት ነው"አንዳርጋቸው ፅጌ

Subscribe to our newsletter!

[newsletter_form type=”minimal” lists=”undefined” button_color=”undefined”]

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *