ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

በሻሸመኔ ቦምብ የወረወረ አንድ ታጣቂ እርምጃ እንደተወሰደበት ፖሊስ አስታወቀ፤ በኦሮሚያ ተጨማሪ ሰዎች ሞተዋል

NtJDO

ነዋሪነቱ አርሲ ዞን ሸርካ ወረዳ የሆነና በሻሸመኔ የጸጥታ ስራ ላይ በተሰማሩ ፖሊሶች ላይ ቦምብ ወርውሮ ሊያመልጥ ሲሞክር እርምጃ እንደተወሰደበት የሻሸመኔ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ። ጉዳት የደረሰበት ህክምና ላይ ነው።

ቦንብ የተወረወረው በሻሸመኔ ከተማ የውስጥ ለውስጥ የጸጥታ ስራን በማከወን ላይ በነበሩ ጸጥታ አስከባሪዎች ላይ ነው። ፋና ፖሊስን ጠቅሶ እንዳለው ቦምብ ወርዋሪው የኦነግ ሸኔ አባል ላይ እርምጃ ተወስዷል።

ዛሬ ከጠዋቱ አንድ ሰአት ተኩል አከባቢ በሻሸመኔ ከተማ 01 ወይም አዋሾ ቀበሌ አካባቢ የጸጥታ ሀይሎች አካባቢያዊ ዳሳሳ ቅኝት ሲያደርጉ ነው ከድር ቱሌ የተባለ ግለሰብ የእጅ ቦምብ ወርውሮ ሊያመልጥ ሲል እርምጃ የተወሰደበት።

Related stories   አውሮፓ ህብረት እየተሽኮረመመ ታዛቢ ሊልክ ነው

በዚህም የተጠርጣሪው ህይወት ሲያልፍ ቦምብ ከተወረወረባቸው የጸጥታ ሀይሎች መካከል በአንዱ ላይ ጉዳት ደርሶ በመልክ ኦዳ ሆስፒፕታል ክትትል እየተደረገለት መሆኑ ተገልጿል።

የሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፀው፥ ከተጠርጣሪው እጅ ተጨማሪ የጦር መሳሪያ ተገኝቷል።

ከድር ቱሌ የተባለው ይህ ተጠርጣሪ መታወቂያው የአርሲ ዞን ሸርካ ወረዳ ነዋሪ እንደሆነ የሚያሳይ ሲሆን፥ ሁለት ሞባይል፣ ገንዘብ እና ትጥቅ መያዣ ቀበቶ ይዞ ነበር።

Related stories   "የአውሮፓ ህብረት ታዛቢዎችን ላለመላክ የወሰነው የማይታዘዝና የማያጎበድድ መንግሥት ይመጣል የሚል ስጋት ነው"አንዳርጋቸው ፅጌ

የከተማው ፖሊስ መምሪያ ከኦሮሚያ ክልል ልዩ ሀይል እንዲሁም ከፌደራል ፖሊስና ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በጥምረት እየሰራ መሆኑንም ነው ያስታወቀው።

የሻሸመኔ ከተማ አሁን ላይ ወደ ቀድሞ ሰላማዊ እንቅስቃሴዋ እየተመለሰች ሲሆን፥ ከዚህቀደም ለወደሙና ጉዳት ለደረሰባቸው ድጋፍ የማድረጉ ተግባርም ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

የከተማዋ ነዋሪ ከጸጥታ አካሉ ጋር ተናቦ እየሰራ ባለው ስራ በርካታ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ያለው ፖሊስ የተዘረፉ ንብረቶችም እየተመለሱ መሆኑንም ፋና አስታውቋል፡፡

Related stories   በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ከተሞች የሽብር ጥቃት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የሽብር ቡድን በቁጥጥር ስር ዋለ- ትህነግ “ክብሪት” የተባለ ገዳይ ቡድን ማቋቋሙ ታወቀ፣

በሌላ ዜና በኦሮሚያ ክልል የሃረርጌ ዞኖች፣ በምዕራብ አርሲ ዞን እና በድሬዳዋ ከተማ ባጋጠሙ ግጭቶች ቢያንስ 4 ሰዎች መገደላቸውን እና በርካቶች መቁሰላቸውን ፖሊስ፣ የሆስፒታል ምንጮች እና የየአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። የአቶ ጃዋር መሐመድ ጤና ታውኳል የሚለው ዜና መሰማቱን ተከትሎ ነው ሰዎች መመሪያ ጥሰው አደባባይ በመውጣት መንገድ ለመዝጋትና ሰላማዊ ዜጎችን ለመተናኮል በማሰባቸው ነው ተብሏል።

ጃዋር በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኝ መንግስት ማስታወቁ ይታወሳል።