በተከታታይ በፋና ቴሌቪዥን አነጋጋሪ፣ አስገራሚና ስሜት የሚነካ ቃለ ምልልስ እያካሄዱ ያሉት የህወሃት የቀድሞ የድህንነት ሹም አቶ ሊላይ ሃይለማሪያም አበበ ገላውን ስሙን በመጥራት ለፕሮፌሰር ሞት ተጠያቂ አድርገውታል። አበበ ገላው በበኩሉ እሳቸው ባሉት መልኩ የመኢአድ አባል መሆን ቀርቶ እሳቸውን በአካል እንደማያውቅ ገልጾ በፌስቡኩክ ገጹ ማብራሪያ እንዲታከል ጠይቋል።

በፋና ቃለ ምልልስ ላይ አቶ ሊላይ በኢትዮጵያዊያን ልብ ውስጥ ዘወትር ታትመው የሚኖሩትን ፕሮፌሰር አስራትን አስመክቶ ስለአሟሟታቸው የሚያውቁትን እንዲናገሩ ተጠይቀው ሲመልሱ አበበ ገላው ከህወሃት የድህንነት ተቋም መመሪያ ወስዶ ለሞታቸው ምክንያት መሆኑንን ነበር ያነሱት።

“አንደኛ እኔ ተናጋሪ፣ ሁለተኛ ፕሮፌሰር አስራት በህይወት የሉም፤ ሶሰተኛ አበበ ገላው ያቃጠረውና አሁን ውጪ አገር ያለ፤ አራተኛ ወሬውን የተቀበለው የድህንነት መስሪያ ቤቱ ዛሬም በህይወት ያለ። እሱ ይናገር”

ይህ ዜና ከተሰማ ጀምሮ ሰፊ መወያያ በመሆኑ አሃዱ ሬዲዮ ከቃለ ምልልሳቸው በሁዋላ በዚሁ ጉዳይ ላይ በዝርዝር አቶ ሊላይን አነጋግሯቸው ነበር። ሲመልሱ በጥቅሉ ያሉት አራት ነገሮች / elements አሉ ካሉ በሁዋላ። አራቱን ነገሮች አስረዱ።

Related stories   የ80ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን በአዲስ አበባ ተከበረ

“አንደኛ እኔ ተናጋሪ፣ ሁለተኛ ፕሮፌሰር አስራት በህይወት የሉም፤ ሶሰተኛ አበበ ገላው ያቃጠረውና አሁን ውጪ አገር ያለ፤ አራተኛ ወሬውን የተቀበለው የድህንነት መስሪያ ቤቱ ዛሬም በህይወት ያለ። እሱ ይናገር” በማለት ለሰጡት መረጃ ትክክለኛነት እንደማይጠራጠሩ አመልክተዋል።

የዜናውን መሰማት ተከትሎ አበበ ገላው መገረሙን፣ የማያውቀው ታሪክ መሆኑንን፣ ጭራሽ መኢአድን በአባልነት ተቀላቅሎ እንደማያውቅ፣ የብሄር ፖለቲካን የሚጠየፍና ፕሮፌሰርን ከማድነቅ ውጪ አንድም ቀን በአካል እንኳ አይቷቸው እንደማያውቅ ገልጾ በመጨረሻም ” ይህንን እውነታ የሚጻረር ታሪክ ፈጽሞ ኖሮኝ አያውቅም። ፋና ቴሌቪዥን እንዲሁም ግለሰቡ በዚህ ጉዳይ ላይ ወይ ማስተካከያ ካልሆነም ተጨማሪ መረጃ እንዲያወጡ ለመጠየቅ እወዳለሁ” ብሏል።

አበባ ገላው በፊስ ቡክ ገጹ የሰጠው ሙሉ ምላሽ
አቶ ሊላይ ኃይለማሪያም የተባለ የቀድሞ የህወሃት አባል የነበረ ሰው ፋና ቴለቪዥን ላይ ቀርቦ ስሜን ጠቅሶ ከዚህ በፊት ሰምቼው የማላውቀው አስገራሚ ታሪክ ሲያወራ በመገረም ሰማሁ። እንደ አቶ ሊላይ አባባል ፕሮፈሰር አስራት ወልደየስን ለወያኔ መረጃ በማቀብል ለእስር የዳረኳቸው እኔ ነበርኩ።
ግለስቡ እንዳለው ሳይሆን እኔ ፈጽሞ የመአህድ አባል ሆኘ አላውቅም። ከዚያም በላይ ፕሮፈሰር አስራትን በዝና ከማድነቅ ባሻገር በአካል አግኝቻቸው አላውቅም። ከተማሪነቴ ጀምሮ እስካሁን ለፖለቲካ አላማ በዘር መደራጀት አያዋጣም ባይ ነኝ። ይህም አቋሜ የጸና መስረት ያለው በምርምርና ጥናት ላይ የተመሰረት ነው።
አቶ ሊላይ የማያውቀው ጉዳይ እኔ በወቅቱ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪ በነበርኩ ጊዜ ፕሮፈሰሩን ጨምሮ 42 መምህራን በአቶ መለስ ዜናዊ ህገወጥ ውሳኔ መባረራቸውን በመቃወም የተደረገውን የተማሪዎች እንቅስቃሴ በመምራቴና በማስተባበሬ ለእስርና ለመከራ ከመዳረጌም በላይ ለአንድ አመት ከትምህርቴ ታግጄ በከፍተኛ ችግር ነው የጨረስኩት።
ይህንን እውነታ የሚጻረር ታሪክ ፈጽሞ ኖሮኝ አያውቅም። ፋና ቴሌቪዥን እንዲሁም ግለሰቡ በዚህ ጉዳይ ላይ ወይ ማስተካከያ ካልሆነም ተጨማሪ መረጃ እንዲያወጡ ለመጠየቅ እወዳለሁ።

Subscribe to our newsletter!

[newsletter_form type=”minimal” lists=”undefined” button_color=”undefined”]

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *