የፊደራል ጉምሩክ ባለስልጣን ከትግራይ ክልል የፖሊስ ሃይል የገጠመውን እንቀፋት አስመልክቶ ከትናት በስቲያ ስብሰባ ተደርጎ ነበር። ስብሰባው ያካሄዱት የሰሜን እዝ የመከላከያ ሰራዊት አመራሮችና የትግራይ የጸጥታ አካላት ጋር ሲሆኑ በግምገማው የትግራይ ክልል ምርጫን አስመክቶ የተነሳ አንዳችም ጉዳይ አልነበረም።

ከሱዳን በሁመራ በኩል የሚገቡ ተሽከርካሪዎች በመደበኛ የጉምሩክ ኬላዎች ፍተሻ ከተደረገላቸው በሁዋላ የትግራይ ፖሊስ በየቦታው እያስቆመና የመፈተሻ ኬላ በማቋቋም ስራውን በማወኩ ጉምሩክ በተደጋጋሚ ለክልሉ ሃላፊዎች ጥያቄ ሲያቀርብ ሰንብቷል።

ከፍተኛ ጭነት የጫኑ ከባድ መኪናዎችን ጭነት በማራገፍ፣ በጉምሩክ ህጋዊ ፈቃድ በሽቦ የታሸጉ ጭነቶችን ሽቦ በመበጠስ፣ የነዳጅ ቦቴዎችን ከነ ነዳጃቸው ለፍተሻ እሽግ በመክፈት የሚያካሂደው ፍተሻ ከክልሉ ስልጣንና ሃላፊነት ውጪ በመሆኑ ነበር ጉምሩክ አቤቱታውን በየደረጃው ሲያቀርብ የነበረው። ለዛጎል መረጃውን የሰጡ እንዳሉት በስብሰባው ላይ ማስጠንቀቂያ የተሰጠ ሲሆን፣ የትግራይ ክልል የጸጥታ ሃላፊዎች ማስተካከያ እንደሚደረግ ቃል ገብተው ስብሰባው ተጠናቋል። በወቅቱም ብርበራው ሲካሄድ የነበረው በክልሉ እንደ አቋም ተይዞ ሳይሆን በተወሰኑ አካላት ትዕዛዝ መሆኑም ተጠቁም ነበር።

Related stories   አብነት ገብረመስቀል ከኮቪድ አገግመው ወደ ቢሮ ተመለሱ

የፌደራል መከላከያ ሰራዊት የኢንዶክትሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄነራል መሐመድ ተሰማ ለኢቲቪ ግመገማውን አስመክቶ የጉምሩክ ጉዳይ መነሳቱን አረጋግተዋል። አያይዘውም በተለይ በድንበር የሚካሄድ ህገወጥ የመሳሪያ የሰዎች ዝውውር ጉዳይ ልክ በሌሎች አካባቢዎች እንደሚደረገው ግምገማ የተደረገበት ጉዳይ ነው። እንዲሁም በኮቪድ 19 ዙሪያ የጸጥታ ሃይሉ ራሱን በመጠበቅ ወረሽኙን ለመከላከል እንዴት መስራት እንዳለበትም ተነስቷል።

ጄነራሉ እንዳሉት የመከላከያ የስራ ተግባር ባልሆነው የምርጫ ጉዳይ ውይይት ተደርጎ ከስምምነት ላይ እንደተደረሰ ተደርጎ በድምጸ ወያኔ የቀረበው ዜና ሆን ተብሎ የተደረገ ነው። ማስተካከያ እንዲደረግበት እንደሚጠየቅም ገልጸዋል። 

ምርጫ የመከላከያ ሰራዊትን የሚመለከት ጉዳይ እንዳልሆነ የጠቀሱት ሜጀር ጄነራል እንዳሉት በአገሪቱ የሚካሄድ ምርጫ እንደሌለ እየታወቀ የአገር መካላከያን ጠቅሶ የፈጠራ ዜና መስራቱ ደረቅ ውሸት ነው። የመከላከያ ሰራዊት የአገር ሰላም ለማስጠበቅ በከፍተኛ ሃላፊነት ላይ የሚገኝ፣ የአገር ሉዓላዊነትን ለማስከበር ሌት ተቀን የሚተጋ ተቋም እንጂ በአንድ ክልል ምርጫ ጉዳይ የሚያሳስበው አይደለም።

Related stories   Ethiopia, South Sudan signs military cooperation deal including intelligence sharing

ድምጸ ወያኔ ስብሰባው መካሄዱን ጠቅሶ የትግራይ ህዝብ ራሱን በራሱ ለማስተዳደር የሚያካሂደውን ምርጫ ለማስተጓጎል ገዢውን መንግስት ጨምሮ የጥፋት ሃይሎች የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ለመግታትና ሰላማዊ፣ ነጻ፣ እንዲሁም ዴሞክራሲያዊ ምርጫ እንዲካሄድ የትግራይ የጸጥታ አካላት ከመከላከያ ጋር አብረው ለመስራት ተስማምተዋል ሲሎ ነበር የዘገበው።

የትግራይ ክልል የጸጥታ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊን አቶ  ለፍታይ መለስን የጠቀስው ድምጸ ወያኔ የመከላከያ ሰራዊት ዋና አዛዡንና አገሪቱን በበላይነት የሚመሩትን ጠቅላይ ሚኒስትር በመቃረን እንደቆመ አድርጎ በትግርኛና በአማርኛ ያሰራጨው ዜና ጉዳዩን አስመልክቶ ከመከላከያ ወገን አስተያየት የሰጠ አካልን አላካተተም።

Related stories   ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሳይቲስት - ችግር የመፍታት አቅም እንዳለህ ከተሰማህ ፣ያንን ፍጥነት መቀነስ በእውነቱ መልካም አይደለም

በጋራ ግምገማው ላይ የሰሜን እዝ ምክትል አዝዥ፣ የክፍለጦር የተለያዩ አዛዦች የተገኙ እንደነበር ከመንግስት ሚዲያዎች በድምጽ፣ የድምጸ ወያኔ በምስል አሳይቷል። እንዲህ መስለ ስብሰባዎች ላይ የመንግስት ሚዲያዎች አለመገኘታቸው ስህተት እንደሆነ፣ ቢያንስ የመከለከያ ሚኒስቴር የሚዲያ ክፍል ተገኝቶ እንዲዘግበው ቢደረግ እንዲህ ያለው ስህተት ሊደገም እንደማይችል ዜናውን የሰሙ አስታውቀዋል።

 

Subscribe to our newsletter!

[newsletter_form type=”minimal” lists=”undefined” button_color=”undefined”]

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *